Тёмный
ኦንሊ ጂሰስ Exposing Only Jesus
ኦንሊ ጂሰስ Exposing Only Jesus
ኦንሊ ጂሰስ Exposing Only Jesus
Подписаться
እኛ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ የምናምን፥ ኢየሱስ ራሱ አብ ራሱ ደግሞ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ነው ብለው ከሚያምኑ ኦንሊ ጂሰሶች ጋር እንደ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ውይይቶችን የምናደርግ ነን።

በዚህ ዘመን ራሳቸውን ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ብለው የሚጠሩ ፤ በጥንታዊውን መናፍቅ ሰባሊዮስ አስተምሕሮ መሰረት "ወልድ አብ ያደረበት ስጋና መገለጫ አካል እንጂ በራሱ ማንነት የሌለው ነው" በማለት ያስተምራሉ።

ሰባሊዮስ በ220 ዓ.ም የኖረ ሰው ነው። የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እና (UPCI) ልክ እንደ ሰባሊዮስ ያለ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊና በጥንታዊው ክርስትና ውስጥ እንደ አርዮስ ውግዝ የተደረገ ትምህርት ይዘው እናያለን።

ይህ ዩቲዩብ ቻናል እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ ትምህርት ፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሙግት እና ውይይቶች ይደረግበታል።

እኛም የምናምነው እውነተኛው የክርስትና ትምህርት ቀጥሎ በአጭሩ ቀርቧል::

አብ አምላክ ነው
ወልድ አምላክ ነው
መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው

ሆኖም ግን አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሶስት የተለያዩ አማልክት ሳይሆኑ አንድ አምላክ ናቸው::

በአምላክ አንድነት እናምናለን

አብ ወልድ አይደለም፤
ወልድም አብ አይደለም፤
አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤
መንፈስ ቅዱስም አብ አይደለም፤
ወልድ መንፈስ ቅዱስ አይደለም፤
መንፈስ ቅዱስም ወልድ አይደለም፤

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የየራሳቸው ቅዋሜ ማንነት ያላቸው አካላት ናቸው::

በአንድ መለኮታዊ ኑባሬና በሶስት አካላት እናምናለን።

አስተያየት መስጫ ኢሜል
📩 exposingonlyjesus@gmail.com

ቢሾፕ ደጉ ተጨንቀዋል!
35:47
Месяц назад
Комментарии