Тёмный
Gospel of Grace Channel-2
Gospel of Grace Channel-2
Gospel of Grace Channel-2
Подписаться
በዚህ ቻናል #አራቱ_ወንጌላት (የማቴዎስ፣ የማርቆስ፣ የሉቃስ እና የዮሐንስ ወንጌል ተከታታይ የቪዲዮ ትምህርት ሙሉ ምዕራፎችን በተብራራ መልኩ የሚቀርብበት ሲሆን ከብሉይና ከሐዲስ ኪዳን መጻህፍት በማጣቀስ ቀርቧል። ስለዚህ በቅደም ተከተል ወይም የሚፈልጉትን ምእራፍ እንንዲያጠኑ ላቸውን #በጌታ #ፍቅር እንጋብዝዎታለን፡፡
ማንኛም #ጥያቄ ወይም #አስተያየት ካለዎት Comment ላይ ይፃፉልን!!
#Like, #Share በማድረግ #ለሌሎች #ወገኖች #እንዲዳረስ #የበኩልዎን #ይወጡ!!
በተጨማሪም በሚከተሉት ሊንኮች በመጠቀም ለንባብ እና ተለያዩ አገልግሎቶች ይጠቀሙባቸው፡፡
Facebook:- facebook.com/groups/1955471598090940/
Website :- www.ewnetone.com/BTM_PAGES/Doctrine0.php
You Tube Pages
Gospel of Grace Channel 1:- ru-vid.com/show-UC6ZObGNbcGm91Xeql_kgEqQ?view_as= #የማቴዎስ_ወንጌል #gospel_of_mathew

👉 የማቴዎስ ወንጌልን በቴሌግራም ቻናል መከታተል ከፈለጉ እነሆ:
t.me/Gospel_of_Grace_Matthew
የጸጋ ወንጌል   ክፍል 75
27:21
14 дней назад
የሉቃስ ወንጌል      ክፍል  74
27:59
14 дней назад
የሉቃስ ወንጌል  ክፍል 73
27:44
21 день назад
የሉቃስ ወንጌል      ክፍል 72
26:50
28 дней назад
የሉቃስ ወንጌል  ክፍል 68
27:48
Месяц назад
የሉቃስ ወንጌል ክፍል 67
26:48
Месяц назад
የሉቃስ ወንጌል ክፍል 66
27:30
Месяц назад
የሉቃስ ወንጌል   ክፍል 65
27:50
2 месяца назад
የሉቃስ ወንጌል  / ክፍል 64/
27:38
2 месяца назад
የሉቃስ ወንጌል    /ክፍል 63/
27:58
2 месяца назад
የሉቃስ   ወንጌል    /ክፍል  48/
27:30
5 месяцев назад
Комментарии
@SisYoha-wm1of
@SisYoha-wm1of 2 дня назад
❤❤❤ ተባረክ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 9 дней назад
ቅድስታ ቅዱሰን መለት ምን መለት ነዉ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 9 дней назад
በስጋ የወለዱን አበቶቸችንንስ አበት መለት አንችልም?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 9 дней назад
በምድር ለይ መንም አበት አይሁንለቹ ስል አልገበኝም ግን መለቴ በፍት አገልግሎ ያለፉትን የእምነት አበቶች ቢለን እየጠረን ያሌነዉ ስዕተት ነዉ መለት ነዉ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
አሜን አሜን በጌታ ስምና ስልጠን በመከከለችን ለይ ያሌዉን ኢየሱስን መመን መስተነገድ ይሁንልን
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
ቡዱኖች ነቻዉ ወይስ ዘር ነዉ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
ፈርሰዉያን እና እና ሰዱቀዉያን ፀሐፎች እነዝ የረሰቻዉ ስም ነዉ ወይስ የዘረቻዉ ስም ነዉ አልገበኝም
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
እነዚህ ስሞች የዘራቸው ሳይሆን የእምነት መለያየት የፈጠሩት ቡድን ነው። ሰዱቃውያን የሚታወቁት ትንሣዔ ሙታን የለም፣ መላእክት የሉም ህይወት በዚህ ምድር አስክንሞት ብቻ ነው ብለው ያምናሉ። ፈሪሳውያን ግን በትንሳኤ እና በመላእክት ያምናሉ። ጸሐፎች የሚባሉት መጽሐፎችን በእጃቸው የሚጽፉ የሚያባዙ ናቸው። ሁላቸውም እስራኤላውያን ናቸው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
ጉድሺ መለት ምን አይነት ሰዎች ነቻዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
ጉንድሽ ማለት አካል ጉዳተኛ ወይም እጁ ወይም እግሩ የተቆረጠ ማለት ነው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
እች ሴት ግን በጌታ አምና ድኅነትን አገኛች ወይስ ልጇ ከገኔን በሺታ እንድድንለት ቢቻ ነዉ ያመነችሁ
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
ጌታ በዚህ ሰዓት እየሰበከ ያለው የመንግስት ወንጌል እንደመሆኑ ኢየሱስን እንደመሲህ መቀበሏ የእምነቷንም ጀረጃ ታላቅ እንደሆነ መስክሯል። ነገር ግን ጌታ ከተሰቀለ በኋላ የሀጢአታችን ዋጋ በመስቀል ከተከፈለ በኋላ ስላለው እምነቷ የተገለጸ ነገር የለም። የዘላለም ህይወት የሚገኘው መስቀል ላይ ተሠራው ስለሆነ። ነገር ግን በእሱ በእውነት ያመነች ስለሆነ ከተሰቀለ በኋላም ታምነዋለች ትከተለዋለች ብለን መገመት እንችላለን። የ እምነቷ ታላቅነት ያበጌታ ተመስክሯል እና። ብዙዎች ግን ለጊዜው ብቻ ተጠቅመው ሄደዋል። ጸጋ ይብዛልሽ እህት ምህረት ቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ ብንጠቀም በጣም ጥሩ ነዉ,። +251 911772186 ወንድም ግርሜ +251911504802 ደረጀ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 28 дней назад
ተበረኩ ገሼ ፀጋ ይቢዘሎት
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 16 дней назад
አሜን የጸጋ ሁሉ አምላክ ስሙ ይባረክ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 29 дней назад
ወንድሙ በሕይወት እያሌ ነዉ ወይስ መቶ ነዉ ሄሮድስ የወንድሙን ምስት ያገበት?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
ወንድሙ በህይወት ባይኖርም ሄሮድስ የአይሁድን እምነት የሚከተል በመሆኑ የህግ መጻህፍትን ማክበር ይጠበቅበታል። በመሆኑም በህግ የተቀመጠው የወንድሙን ሚስት ማግባት የሚቻለው ወንድሙ ዘር ሳያገኝ የሞተ እንደሆነ ብቻ ነው። ይህን ሕግ በመተላለፍ የሄሮድያዳን እናት (የወንድሙን ሚስት) ማግባቱን ዮሐንስ ስለወቀሰው ነው ለእስር የዳረገው ከዚያም ገደለው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
አሜን አሜን በከበረ ዋጋ ተገኝተን በተዎረደ ስፍረ እንደንገኝ እግዚአብሔር ይጠቢቀን ተበረኩ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
በዉስጦት ለይ ስለሌዉ ፀጋ ጌታ ይበረክ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
እንቁ ግን ምንድነዉ? መለቴ ልዩ ትርጉም አሌዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
ዕንቁ በጣም ውድ የሆኑ ከባህር ወይም ከመሬት ውስጥ የሚገኙ ለውድ ጌጣጌጥ መስሪያ የሚውል እና በጥንት ዘመን ገንዘብ ሆኖ ያገለግል ነበር። የውድ ነገር መግለጫ ሲሆን ጌታ በዚህ ቦታ የተጠቀመበት የእሱ ውድ የሆነችውን ዕንቁ 👉ቤተክርስቲያንን ለማግኘት የከፈለውን ዋጋ በምሳሌነት ለማሳየት ነው። ተባረኪ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ግን ጌታችን ኢየሱስ ያንን ምሰሌ ለምንድነዉ የታጠቀመዉ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ስለ እርሾ ያቢረሩልን መቢረሬያ በጠም ግልፅ ነዉ ተበረኩ
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 28 дней назад
በቅድሚያ ስለ እርሾ መጽሐፍ ሐሳብ ምንድን ነው? 1. “ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን #እርሾውን ከቤቶቻችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን #እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።” - ዘጸአት 12፥15 👉 2. ዘጸአት 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁹ ሰባት ቀን በቤታችሁ #እርሾ አይገኝ፤ #እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገር ልጁ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይጥፋ። ²⁰ #እርሾ ያለበትን ምንም አትብሉ፥ በቤቶቻችሁም ሁሉ ውስጥ ቂጣ እንጀራ ብሉ። 👉3. “ኢየሱስም፦ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።” - ማቴዎስ 16፥6 👉4. ማቴዎስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉምን? ¹² እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ። 👉5. 1ኛ ቆሮንቶስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን? ⁷ እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ ⁸ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም። 👉 እርሾ በመጽሐፍ ቅዱስ ያለው ሐሳብ 👉 አሮጌ ፣ ሌላውን የሚያበላሽ መልካም የሆነውን ዱቄት የሚያቦካ የሚያኮመጥጥ መልካም ነገርን የሚያበላሽ ነገር ሆኖ እናገኘዋለን። 👉 በዚህ ማቴ 13: “ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።” - ማቴዎስ 13፥33 በዚህ ክፍል ጌታ መናገር የፈለገው ከላይ በመልካሙ የስንዴ እርሻ ያለውን እንክርዳድ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ምሳሌውም መልካም በሆነ ነገር ውስጥ ትንሽ እርሾ ሲገባ እንደሚበላሽ እና ዛሬ የጌታ በሆነች ቤተክርስቲያን የምናየው በርካታ ስህተት ና መከፋፈል እርሾ ሆኖ የገባ መሆኑን እንረዳለን። 👉ባጠቃላይ ለብዙ ዱቄት ጥቂት እርሾ እንዲበቃ ትንሽ የሚመስሉ ስህተቶችን ቸል ማለት እንደሌለብን እንማራለን። ባጠቃላይ #እርሾ የአሮጌ ነገር የሐጢአት ምሳሌ የመጥፎ ነገር መገለጫ ነው። በተለይም ትነሽ መስሎን የምንተወው ሃጢአት።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ጌታ ፀጋን በሙለት ይጨምርሎት ገሼ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
የሰነፍንጪ ቅንጠት ግን ምንድነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
ሰናፍጭ (ሙስታርድ) በብዛት እንደ ቅመም የምንጠቀመው ሲሆን መጠኗ ትንሽ የሆነች ልክ እንደ ጎመን ዘር ፍሬዋ ትነሽ የሆነች ማለት ነው።
@YomifGemechu-v9i
@YomifGemechu-v9i Месяц назад
my Jesus
@YomifGemechu-v9i
@YomifGemechu-v9i Месяц назад
tebarek wendimachin iyandandun kifil iyetebareknibet new
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ቢቻ እግዚአብሔር ይበርኮት የስልክ ቁጡሮትን ፈልጌ ነበረ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
+251 911772186 ወንድም ግርማ በቀለ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ሸክሜ ልዝቢ ስል ቀለል ነዉ መለቱ ነዉ ወይስ ሌለ ፍች አሌበት ?? ሌለ ደሞ ቀንበሬም ቀልል ነዉ ስል ቀለል ነዉ አይከቢድም እያሌ ነዉ???
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
ማቴዎስ 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁹ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ³⁰ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። ልክ ነሽ። ቀላል መሆኑ ከምን አንጻር ነወ? የሚለውን ስናይ ሰዎች በራሳቸው ስራና ጥረት ድካም የእግዚአብሔርን መንግስት መግባት አልቻሉም። ስለዚህ ጌታ በጸጋ የምንድንበትን አዲስ ኪዳን ሰጠን ይህ ነው ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀላል ያረገልን ከጌታ እንጂ ከእኛ ከይደለም። ስለዚህ መጽሐፍ እንዲህ አለ 👉 ሮሜ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና። ²¹ አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ ²² እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ 👉 ²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉና፤
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
እግዚአብሔር ዘመኖትን ጨርሶ ይበርክ የእዉነት በጠም እግዚአብሔር እያስተመረኝ ነዉ እርሶን በመጠቀም
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
አንበጠ ግን በዝ በኛ ዘመንም ይበለል ወይስ መጥመቁ ዮሐንስ ቢቻ ነዉ የበለዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
እንደየ አከባቢው ቢለያይም አንበጣን የሚመገቡ ሰዎች አሁንም አሉ።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
@@GospelofGrace4gospels አንበጠ ግን ምን ነበረ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
@@GospelofGrace4gospels ሌለኛዉ ዎሰኝ ጥያቄ ፈርሰዉያን ቢዙም ግዜ ከኢየሱስ ገረ የመይስመሙት ከመጀመሬያዉም ክፉኦች ነቻዉ ወይስ ኢየሱስ ከመጠ ቧሀለ ነዉ ክፉኦች የሆኑት?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
@@mihretmamo3408 አንበጠ ማለት (locust) በኛ ከፌንጣ ጋር የሚመሳሰል ቅጠሎችን የሚመገብ ነፍሳት ነው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
@@GospelofGrace4gospels አመሰግናለሁ እሺ ስለ ፈርሰዉያን ጥያቄ ጠይቄ ነበረ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ኢየሱስ ለምንድነዉ ዮሐንስን ከዘች ከሌበት መከረ ደርሶ ያለዎጠዉ እና እስክሞት ድረስም ዝም ያሌዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
የዮሐንስ አገልግሎት ለጌታ መንገደ ማስተካከል ከጌታ አገልግሎተ በፊት ሰዎችን ወደንስሐ መመለስ እና ለንጉሡ (ለኢየሱስ) የሰዎችን ልብ መመለስ ነው። “የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።” - ኢሳይያስ 40፥3 ነገር ግን በእስራኤል ያንያህል ተቀባይነት ሳያገኝ መንገዱን የሚያስተካክልለት መሲህ (ኢየሱስ) አገልግሎቱን ጀመረ። ዮሐንስ በሄሮድስ እጅ ተይዞ ሳለ ወደጌታ መልእክተኛ ልኮ ነበር። የተሰጠው መልስ ኢየሱስ እያደረጋቸው የነበሩትን ድንቆችን እንዲነግሩት ነው ጌታ መልስ የሰጠው። የዮሐንስ አገልግሎት ተጠናቋል። ሥራው በኢየሱስ ተተክቷል። ይሁን እንጂ እስራኤል በሙላት አልተቀበለችም። ከሶስት አመት አገልግሎት በኋላ ደግሞ ኢየሱስ ያለምንም ጥፋት በመስቀል ላይ በመከራ እንዲሞት ሆነ። ለኛ መዳን ቢሆንልንም ዮሐንስን የገደሉት ኢየሱስንም ገለውታል። የዮሐንስ የተላከበትን ሥራ ሲጨርስ ሞተ። ኢየሱስም የተላከበትን ሥራ ሲጨርስ ሞቷል። ዋናው ምክንያት እሰስራኤል አልተቀበለችም አላመነችም። መድሐኒቷን አዳኟን ገፋች። ከዛም ሐዋርያትንም ገደሉ እስካሁን ድረስ ሰዎች ስለኢየሱስ ይሰደዳሉ። ይገደላሉ። ጌታ እስኪመጣ ድረስ ይቀጥላል። ነገርግን በአንድ ቃል እንጽናናለን። “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።” - ማቴዎስ 10፥28
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
በወንጌለት ለይ ቀድሞ የተፀፈዉ የመነዉ?? በሁሌተኛ የተፀፈዉ የመነዉ? በሶስታኛ የተፀፈዉ የመነዉ? በአረተኛስ የተፀፈ የትኛዉ ነዉ መለቴ ወንጌለት??
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
በመጻህፍቱ የአጻጻፍ ቅደም ተከተል በመጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የተጻፈ ባይኖርም ከመጽሐፎቹ ይዘት አኳያ አሁን ያለው የአራቱ ወንጌላት አቀማመጥ (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ) ወንጌል ብዙ የጥንት አባቶች ይስማማሉ። ዋናው ስለወንጌል መጽሐፍት ማወቅ ያለብን ነገር የመጽሐፎቹ ጸሐፊዎች እና የመጽሐፉ ይዘት ነው። 👉የማቴዎስ ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስን ለእስራኤል የሚመጣው ንጉሥ አድርጎ የትውልድ ሐረጉን ከንጉሥ ዳዊት በመጀመር በነቢያት የተነገረውን የአይሁድ ንጉሥን በማስተዋወቅ ከአይሁድ ለሆኑት በሐዋርያው ማቴዎስ የተጻፈ ነው። 👉 “ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።” - ማቴዎስ 2፥1-2 “ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።” - ማቴዎስ 27፥37 👉 የማርቆስ ወንጌል የጌታ ኢየሱስን አገልጋይነት እንደ ባሪያ አጉልቶ የሚያቀርብ ሲሆን ጸሐፊው ማርቆስ የተባለ ከሐዋርያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስ እግር ስር ያደገ ሰው ነው። 👉 የሉቃስ ወንጌል ደግሞ ኢየሱስን የሰው ልጅ ወይም ሥጋ የለበሰ አምላክ አድርጎ የሚያቀርብ ሲሆነ የኢየሱስን ልደት እና የትውልድ ሐረግ በእናቱ በኩል እስከ አዳም በመቁጠር የሚጀምርና የአየሱስን የሰው ልጅ አድርጎ በማጉላት ሉቃስ በተባለ ከአህዛብ ወገን በሆነ የተማረ እና ባለመድኃኒቱ ሉቃስ ሲሆን ከጳውሎስ ጋር ብዙ የሰራ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍንም የጻፈ ነው። 👉 የዮሐንስ ወንጌል በሐዋርያው ዮሐንስ የተጻፈ ሲሆን ከሶስቱ ወንጌላት ለየት ባለ መልኩ የኢየሱስን መለኮታዊ ማንነቱን አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ሶስት መልእክታት እና የራእይ መጽሐፍን ጽፏል። በተጨማሪ የአዲስ ኪዳን መጻህፍትን በተመለከተ የዚህ ተከታታይ ትምህርት ሲጀመር የተሰጡ 6 ተከታታይ ትምህርቶችን ብታይው በጣም ይጠቅምሻል። በተረፈ በርቺ በዋትስአፕ የተሻለ መጻጻፍ እንችላለን። ጸጋ ይብዛልሽ። ru-vid.com/group/PLKCdy0KEwU7BblINMMQcO6DSHlphTe6fQ&si=KSM9e0wVStaCX-uL
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
መጥመቁ ዮሐንስ ወዴ ኢየሱስ የለከቻዉ ሁሌቱ ደቀ መዘሙርት የረሱ ደቀ መዘሙርት ነቻዉ ወይስ የኢየሱስ ደቀ መዘሙርት ነቻዉ???
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
“ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ።” - ማቴዎስ 11፥1 ጌታ የራሱን ደቀመዛሙርት ለወንጌል አገልግሎት ካዘዛቸው በኋላ የዮሐንስ ሁለቱን ላከ። እነዚህ ሁለት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ የራሱ ናቸው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ምህረፍ አስር ለይ አንድ ያልገበኝ ቦታ አሌ ጠሼ ማቴዎስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁴ በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ³⁵ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ³⁶ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። ምን መለት ነዉ?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
ጥያቄ ይመለስልኝ
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
ማቴዎስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁷ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ³⁸ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። ³⁹ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። 👉ሉቃስ 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤ ¹⁷ በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። ¹⁸ ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤ 👉👉 በትምህርቱ እንደተገለጠው በዚህ ክፍል ጌታ ሰለ ሰላም የተናገረው እኛ ጌታን ስንቀበል እና የእሱን መንገድ ስንጀምር ከቅርብ ወዳጆች ከቤተሰብም እናት አባት ወንድም እህት እኛን ለሚያሳድዱን አሳልፈው እንደሚሰጡን በወንጌል በማመናችን በዚህች አለም ብዙ ጠላት እንደሚበዛብን እና በመከራውም ጌታን አክብረን እንድንኖር እንጂ ፈርተን ወደኋላ እንዳንመለስ ከነዚህ ጌታን ከማይቀበሉ ጋር ህብረት ሊኖረን እንደማይገባን፤ ለዘመድ ወዳጅ ብለን ጌታን መተው እንደሌለብን፤ ለማስረዳት ጌታ የተጠቀመበት ትምህርት ነው። ከማያምኑ ጋር ግልጽ ልዩነት መኖሩን እንረዳለን። 👉“ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?” - 2ኛ ቆሮ 6፥14 ጌታ እዚህ ላይ ያነሳው ሐሳብ በአማኝ ላይ ከሚነሳው ተቃውሞ አንጻር ሲሆን 👉ጌታ የሰላም አምላክ፣ ንጉሥ፣ አለቃ ነው እኛም ምንም እንኳ ብንገፋም ቢጠሉንም የሰላም ሰባኪዎች ሆነን መገለጥ ይኖርብናል። ጌታ ሰላማችን ነው። “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥” - ኤፌሶን 2፥14-15 እህቴ ግልጽ ካልሆነ እንደገና እናየዋለን። ስለዘገየሁ ይቅርታ። በርቺ!
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ድንቢጦች የምለዉ ምንድነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
ድንቢጥ በጣም ትንሿ ወፍ ስትሆን ብዙ ጊዜ በግቢ ውስጥ ትገኛለች።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
@@GospelofGrace4gospels እሺ እንዴዘ ያሌዉ እና በሱ የመሰለዉ ምን ለመለት ነዉ
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
በወቅቱ የድንቢጦች እንኳ ዋጋ አላቸው እናንተ ግን ከድንቢጥ ትበልጣላችሁ ለማለት ያቀረበው ምሳሌ ሲሆን ጌታ ሲያስተምር ምሣሌዎች የሚጠቀምበት ሁኔታ የሰሚዎቹን የመረዳት አቅም በመረዳት ነው። ጌታ እናንተ ከድንቢጦች ትበልጣላችሁ በማለት ያጽናናበት ምሣሌ ነዉ። 👉 ማቴዎስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁹ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። ³⁰ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። 👉 ³¹ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ሰመዕተት መለት ምን መለት ነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
ሰማዕት ማለት በወንጌል ምክንያት መገደል ማለት ነው ዋናው ሐሳብ። (“የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።”) - ሐዋርያት 12፥2
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
@@GospelofGrace4gospels ok መገደል የመለት ሌለ ትርጉሙ ነዉ ስማዕት መለት።?
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ok ያ ለደቀ መዘሙርቶቹ የተነገረቻዉ ነገሮች ሁሉ ያ መከረ ሁሉ በነርሱ ዘመን መለቴ ያኔ በነበሩት ደቀ መዘሙርት ግዜ ያልተፈፀመ ለወዴፍት የምፈፀም መከረ ነዉ መለት ነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
ልክ ነሽ ያው የወንጌል አገልግሎት ሁሌም መከራ ይበዛዋል። 👉“በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” - ዮሐንስ 16፥33 የክርስቲያኖች ኑሮ በብዙ መከራ የታጀበ ነገርግን በጌታ አሸናፊዎች ነን። በዚያን ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረው ዛሬም በእኛ ድረስ አለ። ❤የጌታ ጸጋ እና ሰላም ይብዛልሽ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 Месяц назад
@@GospelofGrace4gospels አሜን አሜን አሜን ተበረኩልኝ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
እሺ አበት እግዚአብሔር ይበርኮት እና ጌታችን የቅሰርን ለቅሰር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ ስል ለእግዚአብሔር የምሰጠዉ የምን ምስል ያሌበት ነዉ?? መለቴ የቅሰር ምስል ያሌዉን ለቅሰር ስለሌ ነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels Месяц назад
የሄ አገላለጽ ከጠያቂዎቹ ፍላጎት አንጻር ስናየው ወቅቱ እስራኤል በሮም መንግስት አስተዳደር ስለነበረች አይሁዶች ተገደው ይተዳደሩ ነበር። ስለዚህ ለሮም መንግስት ግብር መክፈል ወይም መተባበርን እንደ ነውር ስለሚቆጠር በጌታ ላይ የመክሰሻ ምክንያት ለቄሳር ግብር መክፈል ይቻላል ወይስ አይቻልም? ይህም ለቄሳር ይከፈል ቢል በአይሁድ ሊከሱት፤ አይከፈልም ቢል በመንግስት (ቄሳር) ሊከሱት ፈልገው ነበር። ጌታ ልባቸውን ስለሚያውቅ በዚህ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ አለ። በሣንቲሙ ላይ ያለውን መልክ እንደምሳሌ ተጠቀመው እንጂ ለቄሳር ም የሚሰጠው በወቅቱ የገንዘብ ነው ያው ሀእግዚአብሔርም የሚሰጠው የዚያው ጊዜ የሚገበያዪበትን ሣንቲም ነው የሚሰጠው እንጂ የተለየ ሣንቲም አይደለም። አባባሉ ለቄሳርም ግብር ክፈሉ የጌታንም መባ ወይም በዚያ ዘመን አሥራት ስጡ ለማለት ነው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
እግዚአብሔር ዘመኖትን ጨርሶ ይበርክ ሌለ ግልጠትን ይጨምርሎት አበቴ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
እግዚአብሔር ይበርኮት አበቴ ታበረኩ እና ቦአርኔጌር የምለዉ የነጓድጓድ ልጆች ያሌዉ ኢየሱስ ከመከከለቻዉ የተዎሰኑ ሰዎችን ነዉ ወይስ 12ቱንም ነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
የነጎድጓድ ልጆች የሚባሉት ሁለቱ ዮሐንስና ያዕቆብ ብቻ ናቸው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
@@GospelofGrace4gospels ልዩ ስም የተሰጠለቻዉ ለምንድነዉ? መለቴ ለያት የምአደርገቻዉ ነገር አሌ
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
@@GospelofGrace4gospels የነጓድጓድ ልጆችስ ለምለዉ ቀል ሌለ ፍች አሌ መለቴ ለመለት የፈለገዉ ምንድነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በዚህ ቦታ ብቻ ስለሆነ ሰፋ ያለ ፍቺ ማግኘት አይቻልም። ነገር ግን በዚህ ቦታ በተገለጸበት ሁኔታ የሁለቱ ወንድማማቾች የአገልግሎት ጠባይ የሚያሳይ ነው። ለምሣሌ ከ12ቱ ሐዋርያት ያዕቆብ የመጀመሪያው ሰማዕት ሲሆን (“የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።” ሐዋርያት 12፥2) ዮሐንስ ደግሞ አስከ ራዕይ መጽሐፍ ፍጻሜ ድረስ የቆየ ምናልባትም በህይወት የቆየው የመጨረሻው ሐዋርያ ነው። በዚህ ምዕራፍ ሐዋርያትን ሁለት ሁለት አድርጎ ወንጌል እንዲሰብኩ ሲልካቸው "የነጎድጓድ ልጆች" ብሎ መሰየሙ፤ ለወንጌል ስራ ያላቸውን ከፍተኛ ተነሳሽነት አውቆ እንደሆነ "ቦአኔርጌስ" ከሚለው የቃሉ ፍቺ መረዳት ይቻላል። ሀይለኛ እና ተጽእንኖ ፈጣሪ የሆነ ስብከታቸው ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። (zealous and vigorous nature of James And John ) የነጎድጓድ ልጆች ሲል 👉ነጎድጓድ የሚለው ስም የወላጅ አባታቸው ተለዋጭ ስም ሳይሆን ጌታ ራሱ የሰየመው ስም መሆኑ ከላይ የገለጽኩልሽን ትርጉም የበለጠ ይገልጸዋል።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
@@GospelofGrace4gospels ወዉ በጠም ደስ በምል አገለለፅ ነዉ የገለፁልኝ ከልቤ አመሰግናለሁ ዘመኖት ይለመልም ተበረኩ ግን ለበለጠዉዉ መረደት የዋትሰፒ ቁጥር ቢኖርና ቢሰጡኝ ደስ ይለኝ ነበረ ምክንያቱም ለ12 ሰዎች ሆነን ማቴዎስን እያጠነን ነበረ ቢዙ ያልገቡልን አሰቦች ስለሉ ልንጠይቆት እንፈልገሌን
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ንደድ ግን ምን ነበረ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
በቅድሚያ እንኳን ደህና መጣሽልን❤ ንዳድ ማለት የወባ የሚመስል በጣም የሚያተኩስ ህመም ነመ፡
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
“በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።” - ማቴዎስ 7፥6 እሄ ቦታ ምን ለመለት ነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
ይህ አይነት አገላለጽ ፈጽሞ ለወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች የምንነግራቸውን ቃል ከማመን ይልቅ ለሰድብና ሌሎችም እንዳይሰሙ ስለሚያደርጉ ስለማይጠቅማቸው የተወሰነ ምስክርነት ከሰጠናቸው በኋላ ብዙ ክርክር አለማድረግ የሚሰሙትን ቃል ሁሉ ለክፋት ስለሚያውሉት ከእንደዚህ አይነት ሰዎች እንራቅ ምንም ጥሩ ነገር ብናቀርብላቸው ተመልሰው ከፌዝና ስድብ አይወጡም። ማቴዎስ 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁶ እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። ⁵⁷ ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። ⁵⁸ በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ግን ኢየሱስ በተለያዩ ቦተኦች ስፈዉሰቻዉ ለመንም አተሰይ ተጠንቀቅ ቢሎ ስነገርም የተፈዎሱት የደኑት ግን ዎጥቶ ስነገሩና ስመሰክሩ እነያሌን??
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
እነዚህ በስጋቸው ያለ በሽታ የተፈወሰላቸው ሁሉ እውነተኛ አማኞች አይደሉም። ኢየሱስ ለማንም አታሳዩ የሚልበት ምክንያት ነገሮችን በራሱ ጊዜ መግለጥ ስለሚፈልግ እና ለማይገባቸው የጊዜው ሰዎች ውስጣቸውን ስለሚያውቅ እንዲየውም ፈውሱን ሊከሱበት እንደመረጃ ለሚሠበስቡ የጊዜው የሀይማኖት መሪዎች ፍርድ ሲሆን እነሱን ራሳቸውንም የሚፈትንበት መንገድ ነው።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ቢዙ ጥያቄኦች አሉኝ እና ዋትሰፒ ቁጡር ከአሌ ቢትልኩልኝ በጠም አርፍ ነዉ
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
ተባረኪ እህቴ እንልክልሻለን።
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
በመቀጠል በማቴዎስ በምህረፍ 6፥3/4 ለይ ለምፀሙን ፈዉሶ ቧሀለ ለመንም እንደትነገር ቢሎ ያስጠነቀቀ ለምንድነዉ?
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 2 месяца назад
ጌታ የሁሉን ልባቸውን ስለሚያውቅ በምልክቶች ብቻ የሚየመደንቁ እንጂ በምልክቶቹ የማያምኑ ስለሆነ ለሚመለከታቸው ካህናት ብቻ አሣይ አለው። የዚህ አይነት ሐሳቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ቦተዎች ላይ አለ። እያዩ ለማያምኑት ፍርድ ነው። የልባቸውን የሚያውቅ ጌታ ለማይገባቸው ሰዎች አትንገር አለው፥ ቢነግራቸውም አይጠቅማቸውምና ነው። ዋናው ሐሳብ ፍርድን ያመለክታል
@mihretmamo3408
@mihretmamo3408 2 месяца назад
ሰለምና ፀጋ በእጥፍ ይቢዘሎት የተከበሩ የእግዚአብሔር አገልገይ ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይበርኮት
@GgHh-bt9cs
@GgHh-bt9cs 3 месяца назад
❤🎉www ooww
@danieldangiso8642
@danieldangiso8642 3 месяца назад
Ameen!!
@meazakassa9899
@meazakassa9899 4 месяца назад
31 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። 32 በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 4 месяца назад
@highlite
@RealBiblerevelation
@RealBiblerevelation 4 месяца назад
❤#10ቱ_ቆነጃጅቶች_እነማን_ናቸው?❤ ================================= ✍️ብዙ ሰባኪዎች በማቴዎስ 25፡1-13 ያለውን ክፍል በማንሳት እውነተኛ አማኞችን እንደሚመለከት አድርጎ በማስተማር ቅዱሳንን ከየትኞች ናችሁ ከሰነፎች ወይስ ከብልሆች ወዮላችሁ በማለት ክፍሉን ያለቦታው በመጥቀስ ቅዱሳንን ግራ አጋብተዋል። ከዚህም የተነሳ ክፍሉም በአማኞች ውስጥ ግራ መጋባትን የፈጠረ ክፍል ሆኖ ይገኛል። ✍️ጥያቄ በመጠየቅ እንጀምር፦ ----------------------- 📌በማቴዎስ 25 ላይ የተጠቀሱት ቆነጃጅቶች እነማን ናቸው?? 📌እውነት ክፍሉ ቤተክርስቲያንን(አማኞችን) ይመለከታል?? 📖 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል፦ ======================= ✍️ይህ ክፍል ሐዋርያቶች በጠየቁት ጥያቄ መሠረት ጌታ ኢየሱስ በምሳሌ ከመለሳቸው መልሶች አንዱ ነው። 📌ማቴዎስ 24 (Matthew) 3፤ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፡- ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት። ✍️መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን(ቅዱሳንን ሁሉ) ይዞ ሲሄድ የቤተክርስቲያን መነጠቅ ይሆናል። ከዛም በኃላ በምድር የ7 ዓመት የመከራ ዘመን ይሆናል። የመጀመሪያው ሶስት አመት ተኩል በማቴዎስ 24 መሠረት የምጥ ጣር መጀመሪያ ይባላል። በሁለተኛው ሶስት አመት ተኩል በማቴዎስ 25 መሠረት ታላቁ የያዕቆብ (የእስራኤል) መከራ የሚባለው ይሆናል። ✍️ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለመንገስ ከመምጣቱ በፊት በ7 ዓመቱ የመከራው ዘመን ስለ መሲሁ የሚመሰክሩ ሁለቱ ወይራዎች የሚባሉ አሉ ራዕ 11:4 ። እነዚህ ሰዎች በሙሴና በኤልያስ መንፈስ የሚያገለግሉ ሲሆኑ የሚሰብኩትም የመንግስት ወንጌል ነው። ይህ የመንግስት ወንጌል ሰዎችን በዋናነትም እስራኤላውያንን ለንጉሱ ለኢየሱስ የሚያዘጋጅ ወንጌል ነው። በእነዚህ ሰዎች ስብከት ወደ 144,000 ሺ የሚሆኑ ወጣቶች ተለውጠው የመንግስት ወንጌልን እስከምድር ዳርቻ ይሰብካሉ ራዕ 7:4 በዛ ሰዓት እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በተመለከተ ለአባቶቻቸው በማለላቸው መሃላ መሰረት ኢየሱስ በዳዊት ዙፋን ላይ በመቀመጥና መናገሻ ከተማውን ኢየሩሳሌም በማድረግ ምድርን ለ1ሺ ዓመት ይገዛል:: (የሺ አመት መንግስት የሚባለው ነው) ✍️ በመከራው ዘመን ይህን የመንግስት ወንጌል ሰምተው የሚያምኑ ሰዎች በማቴዎስ ቋንቋ ብልሆች(በጎች) ሲባሉ የመንግስት ወንጌልን የማያምኑ ሰዎች ደግሞ ሰነፎች(ፍየሎች) ተብለዋል። ✍️በመንግስት ወንጌል ያመኑት ብልሆች(በጎች) ይባላሉ። ኢየሱስ እንዳለው አለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ ይላቸዋል ይህም መንግስት የሺህ ዓመት መንግስት የሚባለው ነው። በመንግስት ወንጌል ያላመኑትን ሰነፎች (ፍየሎች) ይላቸዋል። መጨረሻቸው ለሰይጣንና ለአጋንንቶች ወደተዘጋጀው የእሳት ባህር ይጣላሉ። ማቴ 25:31-46 ✍️ ልናስተውል የሚገባና እውነት ክርስቲያኖች ከብልሆችም ከሰነፎችም ከበጎችም ከፍየሎችም.... የሉበትም። 📌 ቅዱሳን ልብ ሊሉት የሚገባ ነገር ============================== 1) ይህ የሚፈጸመው የቤተክርስቲያን መነጠቅ ከሆነ በኃላ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል። 2) ቤተክርስቲያን ባሏን በናፍቆት የምትጠብቅ ሙሽሪት እንጂ ዘይት ለመግዛት የምትሮጥ ቆነጃጅት አይደለችም። 3) መጥምቁ ዮሐንስ እንደመሠከረው እኛ ሁላችን ሚዜዎች ነን ሙሽሪት ያለችው እሱ ሙሽራው ነው በማለት ሚዜ መሆናቸውንና ስለ ሙሽሮች ስለ ክርስቶስ እና ስለቤተክርስቲያን መስክሯል። 4) አሁን በዚህ ዘመን የሚሰበከው የጸጋ እና የክብር ወንጌል ሲሆን ቤተክርስቲያን ከተነጠቀች በኃላ ባለው 7 የመከራ ዓመታት የሚሰበከው የመንግስት ወንጌል መሆኑን ልብ ልንል ይገባል። 5) የመንግስት ወንጌል ዋነኛ አላማው እስራኤላውያንን ለንጉሱ ለኢየሱስ ማዘጋጀት ነው ኢየሱስም በያዕቆብ ቤት በዳዊት ዙፋን ላይ ለሺ ዓመት በምድር ላይ ይነግሳልና። 6) ይህ የሺ አመት መንግስት ደግሞ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀ መሆኑን ልብ ይበሉ። ለእኛ ለክርስቲያኖች ግን ምድርን ሳይሆን ዘላለማዊ መንግሥቱንና ክብሩን ከሁሉ በላይ ራሱን ነው ያዘጋጀልን። 1ጴጥ 1:3-5 ✍️1 ተሰሎንቄ 5 (1 Thessalonians) 1፤ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ 2፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 3፤ ሰላምና ደኅንነት ነው #ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት #ይመጣባቸዋል ከቶም #አያመልጡም። 4፤ #እናንተ_ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ #በጨለማ_አይደላችሁም፥ 5፤ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤ ✍️1 ተሰሎንቄ 5 9፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። ✍️ 2 ቆሮንቶስ 13፡14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
@RealBiblerevelation
@RealBiblerevelation 4 месяца назад
ይህ ክፍል ስለ ቤተክርስቲያን ነውን? በእውኑ ቤተክርስቲያን አምስት ወይም አስር ቆነጃጅቶች ናት ?ወይስ አንዲት ሙሽራ ናት ? ደግሞ አምስቱ ዘይት አሊያዙም አምስቱ ይዘው ነበር በለዋል ታዲያ መጀመሪያ ሳይኖራቸው እንዴት ዘይቱ አለቀባቸው ዘይት=መንፈስ ቅዱስ ይሁን እሽ ግን ከየት ነው ዘይቱ ሚገዛው ገዙ ስለሚል። መምህር ፀጋ ይብዛሎት ግን ነገሩ እንደዚህ አይመስለኝም በቀጣይ 10ቱ እነማናቸው ሚሉትን ጽሑፍ እስቲ ያንብቡልኝ ከእርሷ በላውቅም።
@GospelofGrace4gospels
@GospelofGrace4gospels 4 месяца назад
ማቴዎስ 25 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። ² ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ³ ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ⁴ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ⁵ ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። ⁶ እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። ⁷ በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ⁸ ሰነፎቹም ልባሞቹን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ⁹ ልባሞቹ ግን መልሰው፦ ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው። ¹⁰ ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ። ¹¹ በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና፦ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ። ¹² እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ። ¹³ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
@Wudeeee
@Wudeeee 5 месяцев назад
❤❤❤❤
@Eluuser-dx5ui5uk3f
@Eluuser-dx5ui5uk3f 5 месяцев назад
ameen ✅️
@Wudeeee
@Wudeeee 5 месяцев назад
እንደዝ ያለ እውቀት ያላቸው ሰዎች ግን ለምንድነ የመይታወቁት እግዚአብሔር ይበርኮት
@messengerofjesus-sw9yp
@messengerofjesus-sw9yp 6 месяцев назад
🙏🙏🙏