#mezmur #protestant #amharic #ethiopia #ጴንጤ #መዝሙር #ግጥም #KaleabTeseaye #jesus
Artist: Kaleab Tsegaye
Song: Masreshiyayie
Album: Endihem Ale
ማስረሺያዬ : ዘማሪ ቃልአብ ፀጋዬ
ሙሉ ግጥም
ሃዘኔን ፡ የረሳሁብህ
ይዤህ ፡ ወጥቼ ፡ ያላፈርኩብህ
ለቅሶዬን ፡ የረሳሁብህ
ይዤህ ፡ ወጥቼ ፡ ያላፈርኩብህ
ማስረሺያዬ...3x
ማስረሺያዬ...3x
ማስረሺያዬ...3x
እናት
ከእናትም ፡ በላይ ፡ ነው
አባት
ከአባትም ፡ በላይ ፡ ነው
ማን ፡ ልበለው ፡ ኧረ ፡ ማን...2x
ኧረ ፡ ማን ፡ ልበለው ፡ ኧረ ፡ ማን...2x
ወንድም ፡ ጋሼ ፡ አልኩት
መከታዬ ፡ አልኩት
ተመቸኛ ፡ ኢየሱስ
የነገሥታት ፡ ንጉሥ
(ሳለቅስ ፡ የደረሰ
እንባዬን ፡ የአበሰ
ሰዎች ፡ ሲርቁኝ
እኔ ፡ አለሁልህ ፡ ያለኝ
ጉድጓዱን ፡ አሻገረኝ )...2x
(ከመንገድ ፡ ላይ ፡ አነሳኀኝ
ያለእድሜዬ ፡ አከበርከኝ ፡ ሰው ፡ አደረከኝ
ከትልልቅ ፡ ሰዎች ፡ ጋራ ፡ አደባለከኝ)...2x
እድሜዬ ፡ አይፈቅድልኝ
ጊዜም ፡ አይፈቅድልኝ
ሁኔታው ፡ አይፈቅድልኝ
ዕውቀቴ ፡ አይፈቅድልኝ
ሰው ፡ ያደረከኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሰው ፡ ያደረከኝ...4x
እድሜዬ ፡ አይፈቅድልኝ
ጊዜም ፡ አይፈቅድልኝ
ሁኔታው ፡ አይፈቅድልኝ
ዕውቀቴ ፡ አይፈቅድልኝ
(ምን ፡ እላለሁ ፡ ምን ፡ እላለሁ
አመሰግናለሁ )...2x
3 окт 2024