Тёмный
No video :(

"ሳልደክምባችሁ ተጠቀሙብኝ! እኔው ላስተምር አልኩ። 'እህ' ያለኝ የለም!!" ዶ/ር ትምክህት ተፈራ part 2 

Debo Media
Подписаться 2,6 тыс.
Просмотров 41
50% 1

የታዋቂውና የቀደምቶቹ ቀደምት ፒያኒስት፣ ተፈራ መኮንን (ነፍስ ይማር) የመጀመሪያ ልጅ ናት። እሷም የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ምሩቅ ናት። ፒያኖ ስትጫወት ለ"ጉድ" ናት፤ ክራር ስትደረድርም "አጃኢብ" ታሰኛለች።
ትምክህት በዚሁ በሙዚቃው ዘርፍ (በሀገረ ጀርመን) የዶክትሬት ዲግሪ አግኝታለች። ሊያውም ከአንድም ሁለት ዶክትሬት ዲግሪ። እኛም ከዶክተር ትምክህት ተፈራ ጋር ስለሙያዋ ጥቂት አውግተናል። ዕውቀቷን በሀገሯ ለመዝራት፣ ለሀገሯ ሰዎች ለማስተላለፍ ያደረገችው ጥረት እንደምን እንደከሸፈ ትነግረናለች።
"ለሀገሬ ያለኋት አንድ እኔ ነኝ! አንድ እኔ! ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም፤ አፍሪካ ውስጥ በእኔ ደረጀ የሚጠቀሱ የዘርፉ ምሁራን (ሴቶች) የሉም፤ ...አንድ! አንድ እኔው ነኝ ያለሁት። ሳልደክምባችሁ ተጠቀሙብኝ! እኔው ላስተምር አልኩ። 'እህ' ያለኝ የለም!
...ውጪ ሀገር እኮ መአት ዩኒቨርስቲዎች ይጋብዙኛል፤ External previewer ነኝ። Book reviewer ነኝ። ከማሌዥያ፣ ከቻይና ሻንጋይ እና ከሌሎች ሀገር ዩኒቨርስቲዎች ጋር እሰራለሁ እኮ። ... የበለጠ መስራት የምፈልገው ግን በሀገሬ በኢትዮጵያ ነው። ...ለምን እንደሆነ አላውቅም የሀገሬ ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ክፍሉን አላቋቋሙም። ይጀምሩና ይተውታል። ያሳዝናል!" ትላለች ዶ/ር ትምክህት። ደቦ ሚዲያ ቃለምልልሱን እነሆኝ ይላችኋል፦

Опубликовано:

 

27 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
А ВЫ УМЕЕТЕ ПЛАВАТЬ?? #shorts
00:21
Просмотров 1,7 млн