Тёмный

በአዲስ አበባ ለተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት በሚሰጡ ታክሲዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ | Addis Ababa | School Transportation 

Подписаться
Просмотров 913
% 16

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ለተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት በሚሰጡ ታክሲዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ከዚህ ወር ጀምሮ ማንሳቱን አስታወቀ። ቢሮው አገልግሎቱን ለሚሰጡ ታክሲዎች ፈቃድ የመስጠት ኃላፊነቱንም ወደ ታክሲ ማህበራት አዛውሯል።
መስሪያ ቤቱ ይህን ይፋ ያደረገው፤ የትራንስፖርት ጉዳይ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ዛሬ አርብ መስከረም 3፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባው ኔክሰስ ሆቴል ባደረገው ውይይት ላይ ነው። ቢሮው የዛሬውን ውይይት የጠራው፤ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ችግር ለመፍታት ባዘጋጀው የሶስት ወር እቅድ ላይ ለመወያየት ነበር።
በተጠናቀቀው 2016 ዓ.ም. በከተማይቱ በትራንስፖርት ፍላጎት እና አቅርቦት መካከል “ከፍተኛ የሆነ አለመመጣጠን” መስተዋሉን በቢሮው የህዝብ ትራንስፖርት አደረጃጀት እና ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ስዩም ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል። የትራንስፖርት አቅሞችን “በአግባቡ እና በሙሉ አቅም አለመጠቀም” ሌላው በዘርፉ የሚታይ ችግር መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 ዝርዝሩን በጹሁፍ ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ ethiopiainsider.com/2024/14169/
--------------------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦ ethiopiainsider
ትዊተር (ኤክስ) ፦ ethiopiainsider
ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦ www.tiktok.com/@ethiopiainsider

Опубликовано:

 

13 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 1   
@ZafuZafu-kp8qf
@ZafuZafu-kp8qf 25 дней назад
በባጆጀች ላይ የተጣለው እገዳ ምን ደረሰ?
Далее