Тёмный

አላህን ፈለኩት ኢየሱስን አገኘሁት ምስክርነት ||ከእስልምና ወደ ክርስትና || Nabeel Qureshi Amharic 

እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal
Подписаться 31 тыс.
Просмотров 80 тыс.
50% 1

I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated from. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌
• Seeking Allah, Finding...
መልካም ዜና
የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
- (ኢሳይያስ 53፥10)
ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
/ @dhugaanniboqachiisa
አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
t.me/BibleAndMe
Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Опубликовано:

 

28 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 422   
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
🔑አብራችሁኝ በገንዘባችሁ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆናችሁ ይህንን ሊንክ ተጫኑትና አናግሩኝ።👇 t.me/BibleAndMe
@thabangaleseng9294
@thabangaleseng9294 3 месяца назад
ok
@nehemiathebuilder1995
@nehemiathebuilder1995 3 месяца назад
ጌታ ኢየሱስ ይባርክ 🙏🙏
@TesemaDebero-wc7iw
@TesemaDebero-wc7iw 3 месяца назад
ተባራክልኝ❤❤❤❤
@KukaAmare
@KukaAmare 3 месяца назад
እስልምና ላይ ለመዝመት የገንዘብ እርዳታ መጠየቅ ባንተ አልተጀመረም፡፡ የሚገርመው ግን እየጠላችሁትም እያንቀጠቀጣችሁም ቢሆን አለምን እያጥለቀለቀው ነው፡፡ እርዳታው ከአላህ ብቻ ነው፤ እናንተ የፈለጋችሁትን ያህል ገንዘብ ሰብስባችሁ ብትዘምቱበት ጠባቂው ከላይ ነው፡፡
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
@KukaAmare 😁 ስለዚ?🤔
@HanaNa-v1c
@HanaNa-v1c 3 месяца назад
ዋው ድንቅ ነው የእግዚአብሄር ስም ይባረክ
@ayniaaynia9036
@ayniaaynia9036 3 месяца назад
ዋው ቢሞትም የህይወት ምስክርነቱ ዛሬም ብዙዎችን ይመሰክራል
@sebelleteferaminas9875
@sebelleteferaminas9875 3 месяца назад
ሞቷል እንዴ??
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ሞቶ የቀረን ነዉ የምታመልኩት? እንግዳዉስ ያልተወለደ ያልወለደ ያልሞተና የማይሞት አንድ የሆነ የማይበላ ግን የሚያበላ የማይጠጣ ግን የሚያጠጣ ቸር መሀሪ ጌታን ተቀበል 🌹🌹💞💞አላህን💟💖💗💓💞🌷🌷🌷
@sebelleteferaminas9875
@sebelleteferaminas9875 3 месяца назад
@@فاطمهاثيوبيا-ق5د ሞትን ድል አድርጎ መነሳት ያቃተው እማ ያንተ መሀመድ ነው። እየሱስ እንደተናገሩው ተነስቷአል አዎ የሰውን ስጋ ለብሶ ስለመጣ ሰው የሆነውን ሁሉ ሆኖአል ከዛ በፊት የነበረ ማንነቱን ግን ፊሊጲስዩስ ምእራፍ 2 አንብብ Philippians 2 አማ - ፊልጵስዩስ 5: በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። 6: እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ 7: ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8: በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። 9: በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ 10: ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
@@sebelleteferaminas9875 ሙሀመድማ ሰዉ ነዉ
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
@@sebelleteferaminas9875 ያልሞተዉን ሞቷል አትበሉ ኢየሱስን ከናንተ እኛ እንወደዋለን ምክናየቱም የአላህ መልእክተኛ ስለሆነ እናም ሙሀመድም የአላህ መልእክተኛ ነው አወ ሙቷል የትንሳኤ ቀንም ይነሳል
@WedeFikir-ht6bg
@WedeFikir-ht6bg 3 месяца назад
ጌታ ሆይ አንተ ምን ይሳንሀል ድንቅ ምስክርነት
@ህይወት4502
@ህይወት4502 3 месяца назад
ሙስሊሞች ልክ እንደዚህ ሰው እግዚአብሔር ይገለጥላችሁ 🙌አሜን
@አላህከሪምሀስብንአላህ
ሰማይና ምድር በውስጡ ያሉትን ያስገኘውን የፈጠረውን አምላክ ትተን በሴት መፅዳጃ አካል የወጣ ሰው እድናመልክ ነው የምትጋብዥን ላንችው ብለናል
@beletetigist9830
@beletetigist9830 3 месяца назад
​@@አላህከሪምሀስብንአላህታዲያ በሴት እንትን ቅርፅ ላለው ጥቁር ድንጋይ መካ ሄዳችሁ የምትሰግዱት ለምንድነው ? ክርስቶስ ከሰው ቢወለድ ከዘላለም ሞት የሰውን ልጅ ለማዳን ነው እግዚአብሔር ከወደደ በፈለገበት መንገድ ቢመጣ አልቀበልህም ማለት ያንተ ፋንታ ነው ለተቀበሉት በስሙ ለሚያምኑት ግን ከዘላለም ሞት ያመልጣሉ ሌላ ማምለጫ መንገድ የለም ❗❗
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
@user-ub8uh8wz8g እንደዛ ሳይሆን ያልነው፣ ፍቅሩን ሊገልጽልን ሰው የሆነውንና በኛ ፈንታ የተቀጣውን ኢየሱስን አምልክ ነው ያልንህ። የሚወድህን (የሚያፈቅርህን) አምላክ ማምለክ አትፈልግም? የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦ “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።” - ዮሐንስ 14፥1 “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” - ዮሐንስ 17፥3 “እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።” - ዮሐንስ 8፥24 ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
@አላህከሪምሀስብንአላህ
@@beletetigist9830 እራሱንም እስራኢሎች ሲሰቅሉት አላዳነም እንኳን እኔን ላድን ጥቁር ድንጋይ ላልከው እኛ ሙስሊሞች ጥቁር ድንጋይም ነብያትንም መላኢኮችንም አናመልክም እነዚህን በሙሉ የፈጠረውን አምላክ አሏህን ነው የምናመልከው
@አላህከሪምሀስብንአላህ
@@ewnetyasarfal ዩሐኒስ 17- 3 አንብበው እውነተኛ አምላክ የሆንክ አንተ የላከውን እየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይች የዘላለም ሂወት ናት ዩሐኒስ 8 40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሄር የሰማሁትን እውነት የነገርኳችሁን ሰው ልትገሉኝ ትፈልጋላችሁ አብራሀም እንድህ አላደረገም እዚህጋ ሰው የሚለው አምላክ እና ሰው አንድ ሊሆኑ አይችሉም ሰው የሚለውን አስምርበት አምላክ ይበላል ይጠጣል ሽንት ቤት ገብቶ ይፅዳዳልን መልሱን ላንተው ልተወው ወዳጀ
@ngsti277
@ngsti277 3 месяца назад
እፍፍፍፍፍ እየሱስ የምል ድምፅ በጀሮየ ስገባ እንዴት ደስስስስስስ እንደምለኝ ሰላም ይስማኛል ክብር ምስጋና ለጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ይሁን ኣሜን
@AkaluGebere-te4ys
@AkaluGebere-te4ys 3 месяца назад
Hi🙏
@ህይወቴኢየሱስነውኢየሱስጌ
እውነት ለመናገር ድሮ እኔ ኢየሱስ የሚለውን ስም በጣም ነው እምጠላው የነበር ምክንያቱም ኢየሱስ የጤንጤ ብቻ ይመስለኝ ነበር አሁን ግን አድጌ መፅሐፍ ቅዱስን ሳንበብ ወንጌል ስለ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ስረዳ ታውቂያለሽ ስሙን ብቻ ስሰማ የመጨረሻ ሰላም ይሰማኛል ኢየሱስ ስል ውስስጤ ሀሴት ያደርጋር ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ኢየሱስ ጌታ ነው።ተባረኪልኝ😊😊
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
@@ህይወቴኢየሱስነውኢየሱስጌ 🙏🙏🙏🙏 እውነት ነው ተባረኪ
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
እውነት ነው እህቴ ተባረኪ ህይወት ሰላም ፍቅር ስለሆነ ነው❤🙏🙏
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 Месяц назад
አሜን ❤🙏
@Yenenash-h1w
@Yenenash-h1w 3 месяца назад
ኢየሱስ ህይውቴ ኢየሱስ መንገዴ ኢየሱስ በር ነህ ኡፍፍፍፍፍ😭😭😭
@AbduFantaw-ij4hv
@AbduFantaw-ij4hv 3 месяца назад
እግዚአብሐር ይባርክህ እውነትን አውቃሀልና
@YahyaIsmail-b8d
@YahyaIsmail-b8d 3 месяца назад
አሜን እየሱስ ጌታ ❤❤ነዉ🙏
@EliasTedrose
@EliasTedrose 3 месяца назад
ኦው በእውነት እየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ድንቅ ምስክርነት
@aderamillo4576
@aderamillo4576 3 месяца назад
AMAZING TESTIMONY GOD BLESS YOU
@dabalebonsa1138
@dabalebonsa1138 3 месяца назад
Thank you so much brother! Get be blessed!
@YaredYassin-hp7ds
@YaredYassin-hp7ds 3 месяца назад
This ultimate joy of God is having the "Authentic Disciple of Jesus Christ". Brother, be like the Berians (Acts 17:11-12) and drenched by Holy Spirit forever more!
@HHa-q9m
@HHa-q9m 3 месяца назад
Wow amazing
@abrahambrhane3920
@abrahambrhane3920 3 месяца назад
በጌታ ማመን ለኛ ቀላል ይመስላል፡ ግን ለሌዎች ስንት ዋጋ እደማከፍላቸው በዚ ቪድዮ ኣይቻለው። ነገርግን ሁሉ ከሱ ስለ ሆነልን.. ስሙ ይባረክልን። ኢየሱስ ጌታን ኣዳኝ ኣምላክ ነው። 🙏
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
እየሱስ መላእክተኛ እንጅ አምላክ አይደለም
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ቀጥተኛዉን መንገድ ይምራችሁ
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
እውነት ነው ላስተዋለ ተባረኪ🙏
@mesk_erem
@mesk_erem 3 месяца назад
ተባረኩ❤❤❤
@negistitegafaw1491
@negistitegafaw1491 3 месяца назад
Jesus the king of king ❤
@JOHNFIKRE1
@JOHNFIKRE1 3 месяца назад
ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም አምላክ ነው። ሙስሊሞች ይሄ እውነት እንድበራላችሁ ፀሎቴም ምኞቴም ነው
@KukaAmare
@KukaAmare 3 месяца назад
እኛ እውነቱ የበራልን ነን፡፡ እውነቱን ክዳችሁ ለጨለመባችሁ ለእናንተ እናዝናለን፡፡ እየሱስ አላህን እንደዚህ ብሎ መለመኑ የእየሱስን ነብይነት እንጂ ጌታነት የማያረጋግጥ መሆኑን መረዳት ያቃተው ሰው ያሳዝነኛል፡፡ Matthew 26:39 After walking a little farther away from them, Jesus fell to the ground and prayed, “My Father, if it is possible, do not give me this cup of suffering. But do what you want, not what I want.”
@KukaAmare
@KukaAmare 3 месяца назад
በዚያች የጭንቅ ሰዓት እንደዚህ ተንበርክኮ ፈጣሪውን መጠየቁ ልብ ማለት አቅቶሃል፡፡ ለነገሩ አንድ አንድም ሦስትም እያላችሁ የምታምታቱበት እሳቤያችሁ የዚህንም አንቀጽ ትርጉም ለማጣመም ትገለገሉበታላችሁ፡፡ እንዳለውም ጽዋዋ ከእሱ አልፋለች፤ አልገደሉትም አልሰቀሉትም፤ በአላህ ፈቃድ ከነነፍሱ አርጓል፡፡
@KukaAmare
@KukaAmare 3 месяца назад
ማቲዮስ 12፤40 “ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” በማለት ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ የሰጣቸው ለምን ይመስልሃል? ዮናስ ከባህር እስከ አሳነባሪው ሆድ ሲቆይ ያለሞት እንደተረፈ ሁሉ እየሱስም ሳይሰቀል ሳይሞት 3 ቀናት በመቃብር ውስጥ ቆይቶ ወደ ፈጠረው ወደ አላህ ማረጉን ማሳያ ነው፡፡
@JOHNFIKRE1
@JOHNFIKRE1 3 месяца назад
@@KukaAmare ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ መግባቱንም ካመናችሁ ጥሩ ነው🙏 ቁርዓናችሁ ግን ይሄንንም ይክዳል ➔ሙሐመድ ሐሰተኛ ነብይ ስለመሆኑ ብዙ መሰረጃዎች አሉን‼️የአይምሮ ችግር እንዳለበትና ከጂን/ከሰይጣን ጋር ገግንኙነት እንዳለበትም ቁርዓናችሁ ይናገራል ።እንዴዚህ ባይሆን ኖር የዘጤኝ አመት ህጻንን አይደፍርም ነበረ። ሙሐመድ ከአጋንንት አንጅ ከእጎዚአብሔር አይደለም፤ ኑ ወደ ኢየሱስ ህይወትም፣እውነትም፣ መንገድም ነው ።
@masartmissoo1160
@masartmissoo1160 2 месяца назад
​@@KukaAmarewude inate quran yeallah qal now belachu taminalachu quran eko abizagnaw kifloch tashirowal kequran yetasarazu kifloch Alu okay. Indaz sehoni demo quran yefatar qal ayidelam malat now mikinaytum indet yefatar qal yisarazal woyins yanchi amilak yisasatal
@KalkidanKalkidan-tc2jy
@KalkidanKalkidan-tc2jy Месяц назад
ኢየሱስ ጌታ ነው።❤❤❤❤🙏🙏🙏
@sebelleteferaminas9875
@sebelleteferaminas9875 3 месяца назад
እየሱስ ክርስቶስ ለአመኑት ለፈለጉት ራሱን የሚገልጥ አምላክ እንጂ ተደብቆ ብቻ አምልኩኝ ያለ አይደለም ክብር ምስጋና ለዘለአለም ለሱ ይሁን አሜን አሜን አሜን❤ 1 John 5 20 የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
@tirhashagos26
@tirhashagos26 3 месяца назад
እዉነት ያድናል ብርሃን በርቶልሀል❤❤❤❤❤
@YaredYassin-hp7ds
@YaredYassin-hp7ds 3 месяца назад
Jesus answered, “I am the way and the truth and the life. No one comes to the Father except through me.
@danilee2569
@danilee2569 3 месяца назад
እየሱስ ክርስቶስ የኛ የክርስቲያኖች አምላክ ነው❤❤
@ElduErsumo
@ElduErsumo 3 месяца назад
Ye alemi huluu getaa ye huluu fatari ina amalaki new
@Best_motivate1
@Best_motivate1 3 месяца назад
@danilee2569 Ye alem hulu geta newu. Tesastehal.❤🎉🎉
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
እኛ አምላካችን እንደሆነ አምነናል ለማለት ነው። ሶስታችሁም ልክ ናችሁ።😍
@mintesnot6857
@mintesnot6857 3 месяца назад
የክርስቲያኖች ብቻ አይደለም የአለም ሁሉ አምላክ ነው።
@danilee2569
@danilee2569 3 месяца назад
@@mintesnot6857 ለሙስሊሞች ግን ነብይ ብቻነው😭😭
@NasirDari-oh2tk
@NasirDari-oh2tk 3 месяца назад
God bless you
@esmaelhayru4688
@esmaelhayru4688 3 месяца назад
አላህ ጥመታቹ ላይ ከባድ ጥመትን ጨመረላቹ አላህ ያቀናውን ማንም አያጠመውም አላህ ያጠመመውን ማንም አይመራውም
@Hesai-u3s
@Hesai-u3s 3 месяца назад
አልቀረበሽም😅😅😅😅😅
@BayuBayu-zl3xh
@BayuBayu-zl3xh 3 месяца назад
አላህ ማን ነው
@HayahuletAmanual
@HayahuletAmanual 3 месяца назад
Diyablos slehone eko nw yatememew
@Hesai-u3s
@Hesai-u3s 3 месяца назад
@@HayahuletAmanual 👀👀👀👀👀👀
@Hesai-u3s
@Hesai-u3s 3 месяца назад
@@BayuBayu-zl3xh የመካ ድጋይ😳😳😳😉
@SimeBayane
@SimeBayane 3 месяца назад
Woww amazing nw
@bezuGmelana
@bezuGmelana 2 месяца назад
Kechalam wedi beraane yemedih geta yemesegen
@hanatariku1337
@hanatariku1337 3 месяца назад
Jesus is Lord
@shalomsara9461
@shalomsara9461 3 месяца назад
Jesus is Lord ❤❤❤ Amen Amen halleluja 🙏💥
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
በእንባ ነው የሰማሁት ድንቅ ምስክርነት 😢 ተባረኩ ግን በህይወት አለ ?🙏🙏🙏
@mebrate8844
@mebrate8844 7 дней назад
Yelme 😭😭😭😭😭😭
@Alem-pk9mg
@Alem-pk9mg 3 месяца назад
Ohhh praise God Thank you Jesus
@MafiGetu-vz8wr
@MafiGetu-vz8wr 2 месяца назад
Eyesus ye getoch geta ye negesitat nigus new amen!!!
@alexassefa5430
@alexassefa5430 3 месяца назад
በርታ፣ለምን ላይፍ አታስተላልፍም፣በጣም ጎበዝ ተርጔሚ ነሕ ለብዙዎች ኝንዲደርስ ላይፍ ጀምር
@Samira-g5z4z
@Samira-g5z4z 3 месяца назад
አላህ ይምራችሁ ወደ ሀቁ ብቻ አላህ በዲናችን አኑሮ በዲናችን ይግደለን
@አዳማናዝሬትአዳማ
@አዳማናዝሬትአዳማ 2 месяца назад
ጌታ ኢየሱስ ይገለጥልሽ ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው
@meditesfaye7084
@meditesfaye7084 3 месяца назад
Amen 🙏🙏🙏
@assaa7514
@assaa7514 3 месяца назад
ኦርቶዶክስ ነው የሆነው ወይስ ፔጤ ምድነው ኮሜንቱ ሁሉ ተባረክ ተባረኩ እየሱስ ጌታ ነው ይበዛበታል
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
ምስክርነቱ ስለማን ነው አልሰማሽም እውነት ህይወት መንገድ እኔ ነኝ ስላለው ስለ ጌታ እየሱስ ነው ክብር ለስሙ ይሁን 🙏🙏🙏
@MeazaZizi
@MeazaZizi 3 месяца назад
ገና ዓለም በክርስቶስ ይጠቀለላል
@YaredYassin-hp7ds
@YaredYassin-hp7ds 3 месяца назад
f you declare with your mouth, “Jesus is Lord,” and believe in your heart that God raised him from the dead, you will be saved.
@Fasildejene-ru8yg
@Fasildejene-ru8yg 3 месяца назад
tebarek tsega yibzalh ❤❤
@abfamily9559
@abfamily9559 3 месяца назад
አሁን በሂወት የለም እንጂ ስንት ሰው ያሰተምር ነበር ❤
@coding4ethiopia
@coding4ethiopia 3 месяца назад
egziabher zarem sew alew
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
በህይወት የለም እንዴ 😢?
@AkaluGebere-te4ys
@AkaluGebere-te4ys 3 месяца назад
Hi🙏🙏🙏🙏🙏
@Mihret-yh5nv
@Mihret-yh5nv 3 месяца назад
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@HabenMulugetaHaile
@HabenMulugetaHaile 3 месяца назад
Yeasus goytanan amlaknan eyu hallelujah
@WaleytaPablous
@WaleytaPablous Месяц назад
❤❤❤
@AsnBez-cg2ld
@AsnBez-cg2ld 3 месяца назад
ወሏሂ ኢየሱስ ፈጣሪ አለመሆነ ግልፅ የሆነ ነገር ነው አላህ አልመራቹህም እየሱስ በእናቱ ሆድ ሆኖ አለምን እየመራ ነበር ልትሉ ነው አታፍሩም
@ronycell1590
@ronycell1590 3 месяца назад
❤❤❤🎉🎉🎉
@HareguaGeremew
@HareguaGeremew 3 месяца назад
Wow egzabhre yemsgene orthodox mehonee metadele new 🙏🏾🙏🏾🙏🏾
@bertukanberehanu8754
@bertukanberehanu8754 3 месяца назад
Amen 🙏
@Beluna798
@Beluna798 3 месяца назад
Amazing Vids
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ስለ እስልምና ተማር ይቀረሀል
@genetwasho3260
@genetwasho3260 3 месяца назад
👍🙏❤️
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
አላህ ይመልስ
@danyakadir5131
@danyakadir5131 3 месяца назад
Allah kenawn menged yemerak Sew le swe muto Ayawkm
@ZebibaBelay-dn4dt
@ZebibaBelay-dn4dt 3 месяца назад
@BirituSherera-rg5dh
@BirituSherera-rg5dh 3 месяца назад
❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉
@almazpasqual1120
@almazpasqual1120 3 месяца назад
የእጁ ሥራ ስለሆንሽ አሁንም ሢሠራ የሚከለክለዉ የለምና በትንሳኤዉ ሞቶ በመነሳት ከዘለአለም ሞት ታድጐ ሕይወቱን ሰጥቶናል እየሱስ ያንቺን ግኡዝ አይነጥቅም ነገር ግን በዘለአለም በደሙ ኪዳን ወዶሽ ሕይወት እንዲሆንሽና እንዲበዛልሽ በደጅ ቆሞ የልብሽን በር እንድትከፍቺለት እያንኰኰ ነዉ::
@kenozinab8884
@kenozinab8884 3 месяца назад
እየሱስ አምላክ ከሆነ ለምን ያቺን ቀን አላወቀም? ከሆነ የማያውቅ አምላክ ነው ነው ማለት new
@demesseimekonnen4475
@demesseimekonnen4475 3 месяца назад
ለትርጉሙ ትክክለኛነት የተናጋሪውን ድምፅ ማሰማት ይገባል ነተናጋርው ድምፅ በደንብ አይሰማም ።
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
ዋናውን ቪድዮ እንድታገኙ description ላይ ሊንኩን አስቀምጫለው። ዋናው ጉዳይ ግን የትርጉሙ ትክክለኝነት ሳይሆን የመልእክቱ እውነተኝነት እና ጠቃሚነት ነው። እሱ ባይናገረው እንኳን የተነገረው እውነት ከሆነ በቂ ነው።
@kenozinab8884
@kenozinab8884 3 месяца назад
Read the bible then finally you will find the truth that is the path and religion of the whole prophets which is islam!!! Come to islam you get eternal life.
@AtkiltMandefro
@AtkiltMandefro Месяц назад
ኢየሱስ አምላክ ነው
@tbeltsa9525
@tbeltsa9525 3 месяца назад
Egiziyabeher me miteraw Hulu kiribi new eyesusu kirisitosi amilakachin new abeyetu line denidanewechi melisachew
@natikindu8922
@natikindu8922 Месяц назад
Ene erasu ye esun yahal temeramre amlaken alagegnehutm
@BekiAshagre
@BekiAshagre 3 месяца назад
Berta wendime dinki new
@mehabubarashid3519
@mehabubarashid3519 3 месяца назад
Alhamdullillah Muslim lareqenq Allah ebacachu atejajalu wendemoch Lalemeberezu wastena ke Amlak yetesetew Qura'an becha yehema ene enkwan yemakewen yaacel ayakem Bedegami Allhamdullillah muslim bemehone Allah mechereshayenem muslim adrgo yegedelng Allahu Akbar hulu bemasreja islimina becha andet enkwan sehetet bemasreja maamtate alchalem. Wllahi denqe new islimina.😊
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
እኛ ሙስሊሞች በየሱስም ሆነ በወንጌል እናምናለን
@Blackbetharchane
@Blackbetharchane 3 месяца назад
በወንጌል ማመን ማለት እኮ አምላክ ስጋ ለብሶ የሰው ሀጥያት ሊያስወግድ እንደመጣ ማመን ነው የእየሱስ አምላክነት የወንጌል ጠርዝ ላይ ያለ ጉዳይ አይደለም እናንተ ሙስሊሞች ደግሞ እንኳን አምላክነቱን እና ትንሳኤውን ሞቱን እንኳን አታምኑም ታዲያ የቱ ጋር ነው በወንጌል ያመናችሁት?
@abdiregane3243
@abdiregane3243 3 месяца назад
dinqiidha baayyee
@AkaluGebere-te4ys
@AkaluGebere-te4ys 3 месяца назад
👉
@አፍያዩቱብ
@አፍያዩቱብ 3 месяца назад
ዮሀንስ ወንጌል5/30እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፣የላከኝን ፍቃድ እንጂፍቃዴ አልሻምና😮😂?? ቁርአን ኢሳ/አለሂሰላም ከጭቃ የወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ በአላህ ፍቃድ ወፍ ሁኖ ይበራል❤🎉
@africainfotec6061
@africainfotec6061 3 месяца назад
እየሱስ/ወልድ የራሱ ፍቃድ እና የራሱ ፍርድ ካለው.....🤔 አብም የራሱ ፈቃድና የራሱ ፍርድ ካለው ... ስንት አምላክ ሆኑ??? 2 አምላክ አደል????🤔 እኛ ደግሞ 2 አምላክ የለንም። የአብ ፈቃድ የወልድም የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ... የአብ ፍርድ የወልድም የመንፈስ ቅዱስም ፍርድ ነው። አንዲት ፈቃድ አንዲት ፍርድ አንድ አምላክ ነገር ግን በ3 የተለያዩ አካላት የተገለጠ 1 አምላክ። እነሱ አካላት አብ , ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ። በ3 ቱም ውስጥ ያለው ያው 1ዱ መለኮት ነው።
@አፍያዩቱብ
@አፍያዩቱብ 3 месяца назад
@@africainfotec6061 የተምታታ መልስ
@AkaluGebere-te4ys
@AkaluGebere-te4ys 3 месяца назад
Hi
@አፍያዩቱብ
@አፍያዩቱብ 3 месяца назад
ዮሃንስ ወንጌል/5/26አብ ራሱ ሕይወት እንዳለው?،እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወትእንዲኖረው ስጥቶታል??አብና ወልድ ይለያያሉ??
@africainfotec6061
@africainfotec6061 3 месяца назад
አዎ ። አብ የራሱ አካል አለው ( አባት ነው።) ወልድም የራሱ አካል አለው(ልጅ ነው። የአብ የወጣ ነው። የአብ ቃል ነው።) አብ በነበረበት ዘመን ሁሉ አብሮ ከሱጋ ኖሯል ይኖራል። አብን ከቃሉ / ከወልድ / ከልጁ መነጠል አይቻልም። የአብ መለኮት(1አምላክነት) በወልድም ውስጥ ያው 1ዱ መለኮት አለ። ይኖራል
@አፍያዩቱብ
@አፍያዩቱብ 3 месяца назад
@@africainfotec6061 ሁለት የተለያዩ ግን አንድ አምላክ እ
@jemalseid7690
@jemalseid7690 3 месяца назад
Open but impaired eyes.
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ሁለት ነገሮች የሚያስገድዱት ጌታ ሊሆን አይችሉም እነሱም መፀዳጃ ቤት የሚያስገቡ ሲሆኑ
@Blackbetharchane
@Blackbetharchane 3 месяца назад
አስተሳሰባቹ ከቤታቹ ሽንት ቤት አይሻልም ውሃ ሚያነሳ ሀሳብ እኳን ብትጽፍ ምናለበት
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
@@Blackbetharchane ጌቶቻችሁ በመንፈስ አንድ ከሆኑ ለምን መሞቱንና ከ3 ቀን በሗላ መነሳቱን እያወቀ ሲሰቀል ጌታዉን ተማፀነ?????? እርሱ ጌታ ከሆነስ ለምን ፈራ
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ምላሽ ካለዉ ጥያቈየ ትልቅ ነዉ የኛ ጌታ አይበላም አይጠጣም በአካልም ሆነ በመንፈስ አንድ ነዉ።________እየሱስ ለናንተ ሀፂያት ከተሰቀለ ለምን ለሀፂያታችሁ ንስሀ ትገባላችሁ
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
ለጥያቄ መልስ
@mesk_erem
@mesk_erem 3 месяца назад
ኦኦኦኦኦኦኦኦኦኦ JESUS እንዴት ድንቅ ምስክርነት ነው ❤ ተባረኩ
@AmanuelAlemu-m3f
@AmanuelAlemu-m3f 3 месяца назад
@DiboEf-cd5dy
@DiboEf-cd5dy 3 месяца назад
ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው ❤️❤️❤️❤️
@ወለተሰበትእናቴነሽማርያም
እግዚአቢሄር ይመስገን ስለሁሉም ነገር ክብር ለድግል ማርያም ልጂ ይሁን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
አሜን 🙏
@meaza5096
@meaza5096 3 месяца назад
ወንድም ጌታ ይባረክ በረታ በጉጉት ነው
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 3 месяца назад
አመሰግናለው🙏
@AbebaDamesa-wc7ls
@AbebaDamesa-wc7ls 3 месяца назад
Please all Christian should have support this RU-vid Without any our denomination
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
ተባረክ 🙏
@Alemtsehay777
@Alemtsehay777 3 месяца назад
አገላለፅህ ደስ ይላል ተባረክ ዋጋህ ከላይ ነዉ። ኢየሱስ ጌታ ነዉ። ኢየሱስ አምላክ ነዉ። ኢየሱስ የአለም መድሀኒት ነዉ። አሜን ሀሌሉያ
@SamiraS-g3w
@SamiraS-g3w 3 месяца назад
👎
@abenezerdawit3323
@abenezerdawit3323 2 месяца назад
አሜን 🙏🙏🙏
@FekaduShiferaw
@FekaduShiferaw 3 месяца назад
ኢየሱስ ክርስቶስ እውነት ነው።
@123e53
@123e53 3 месяца назад
❤❤
@mintesnot6857
@mintesnot6857 3 месяца назад
ፀጋው ይብዛልህ ተባረክ❤
@رقيهمولا
@رقيهمولا 3 месяца назад
የድግልማረያምልጅእግዚአብሄር❤❤❤ፍቅርነዉናይክበርይመሥገን❤❤❤❤❤❤❤❤
@natanfilimon6237
@natanfilimon6237 3 месяца назад
Ere tnsh eferu egzabhier ye dngl lj nw eski wengiel atzgu raku please.egzabhier amlak nw ye Hulu fetari eji maryam alfeterechum eshi rasuwa ersu nw yefeterat egzabhier gn😂fetari nw kerswa yetewelede ye egzabhier hasab nw ebakachu fturn admkachi fetari medenek akumu srachu yfres be eyesus sm
@genieva3909
@genieva3909 3 месяца назад
ዋው ይህ ነው ኢየሱሰ የዘላለም እይወትን ሰጪ ኢየሱሰ እርሱ ፈጣሪ ነው ሰለምሰክርነቱ ክብሩን የሚገባው ጌታ ኢየሱሰ ይውሰድ
@BaderAlbarq
@BaderAlbarq 3 месяца назад
ዋውውው ያሰደንቃል እየሱሰ የዘአለም አምላክ ነው ❤❤❤❤❤❤
@meb153
@meb153 3 месяца назад
እየሲስ አምላክ ሆኖ እያለ አምላክ መሆኑን አለማመናችን በእውነትም አምላካችን መሆኑን አይቀይረውም አምላክነቱን ባለማመናችን ግን ይፈርድብናል። ልትድኑ ብትወዱስ ግዜው አሁን ነው።በፍራቻ ሰንሰለት ታስራችሁ እስከ መቼ ትኖራላችሁ? ሱራህ 4:89 አምብባችሁ ከሆነ ጤነኛነቱ አያጠራጥርም ወይ?አልፋና ኦሜጋ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ሃሌሉያ!!
@alemalemu9939
@alemalemu9939 3 месяца назад
እግዛብሔር ይባርካችሁ በጥበብና በፍቅር ሙስሊም እድሞቻችንን እድንደርስላቸው ፀጋ ይብዛልን
@KukaAmare
@KukaAmare 3 месяца назад
እኛ እውነቱ የበራልን ነን፡፡ እውነቱን ክዳችሁ ለጨለመባችሁ ለእናንተ እናዝናለን፡፡ እየሱስ አላህን እንደዚህ ብሎ መለመኑ የእየሱስን ነብይነት እንጂ ጌታነት የማያረጋግጥ መሆኑን መረዳት ያቃተው ሰው ያሳዝነኛል፡፡ Matthew 26:39 After walking a little farther away from them, Jesus fell to the ground and prayed, “My Father, if it is possible, do not give me this cup of suffering. But do what you want, not what I want.”
@BirukEndale-b7k
@BirukEndale-b7k 3 месяца назад
እናመሰግናለን በርታ እንዳታቋርጥ እንደዚህ አይነት ብዙ ምስክርነት አሉ እየፈለፈልክ አቅርባቸው❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@harithfalah3716
@harithfalah3716 3 месяца назад
እኼው ነው አምላካችን😢❤❤❤❤❤
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
የቱ🫣
@natikindu8922
@natikindu8922 Месяц назад
​@@فاطمهاثيوبيا-ق5د wendmie yilk sayrfdb h na medan kefelek ena mecheresha lay yalewn website giba ena gudachu hn eye
@رقيهمولا
@رقيهمولا 3 месяца назад
እየሡሥክርሥቶሥእግዚአብሄርነዉአምላካችንይመሥገን❤❤❤❤❤❤
@eyorusalemeyasu4774
@eyorusalemeyasu4774 3 месяца назад
Jesus is Lord Amen Amen &God bless you ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@ElsabetAbrar
@ElsabetAbrar 3 месяца назад
ደግሜ ደጋግሜ ያየሁት ምስክርነት በትክክል ነጥሮ የወጣ የመዳንን መንገድ የማወቅ ሚስጥር እኛንም ይርዳን በተለይ ለሌሎች ተዘጋጅተን መመለስ እንድንችል ትጋት ይጨምርልን
@YeshiSahle
@YeshiSahle 3 месяца назад
ጌታ እየሱስ ለተቀበሉት ሁሉ አዳኝ ጌታነው
@TsehayTsehay-c4n
@TsehayTsehay-c4n 3 месяца назад
ዘመን ሁሉ ይባረክ ለምልምስፍብዛ ፀጋውይብዛልህ ጌታከሀንተጋርይሁን
@amlisium6189
@amlisium6189 3 месяца назад
ተባረክ ወንድሜ 🙏 ፀጋ ይብዛልህ, ዘርህ ይባረክ, 🙏🙏🙏
@nehemiathebuilder1995
@nehemiathebuilder1995 3 месяца назад
ጌታ ኢየሱስ ይባርክ 🙏🙏
@sintayehumerawi1727
@sintayehumerawi1727 3 месяца назад
የሚያስደንቅ ምስክርነት ነው ተባረኩ
@OrthodoxyStPaul
@OrthodoxyStPaul 3 месяца назад
ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ለዘለአለሙ ይክበር ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ወደ ቤተክርስቲያኑ መንግስት አፍልሶናልና 🙏 ያልዳኑትም እንዲድኑ መንገዱን ያመላክታልና
@Jesus_is_Lord_stn25
@Jesus_is_Lord_stn25 3 месяца назад
ኢየሱስ አምላካችን ነዉ።
@فاطمهاثيوبيا-ق5د
@فاطمهاثيوبيا-ق5د 3 месяца назад
አይደለም
@Jesus_is_Lord_stn25
@Jesus_is_Lord_stn25 2 месяца назад
@@فاطمهاثيوبيا-ق5د ኢየሱስ አምላክ ነዉ፤ ጌታም ነዉ።
@Jesus_is_Lord_stn25
@Jesus_is_Lord_stn25 2 месяца назад
@@فاطمهاثيوبيا-ق5د ኢየሱስ ጌታ ነዉ።
@Jesus_is_Lord_stn25
@Jesus_is_Lord_stn25 2 месяца назад
@@فاطمهاثيوبيا-ق5د ኢየሱስ ጌታ ነዉ።
@رقيهمولا
@رقيهمولا 3 месяца назад
አምላኬዬእግዚአብሄርይክበርይመሥገን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@Alemtsehay777
@Alemtsehay777 3 месяца назад
አሁን ይሄ ሰዉ በህይወት አለ? እንኳን ጌታ ኢየሱስ ረዳዉ።
@sarasolomon-y4r
@sarasolomon-y4r 3 месяца назад
He was died 2017. RIP brother
@masartmissoo1160
@masartmissoo1160 2 месяца назад
Wishat now ale geta yiqr tilalachu ahun min tatarfalek tatarfalesh indaz fatfo Nagar selatamagnayilk
Далее
С какого года вы со мной?
00:13
Просмотров 199 тыс.