Тёмный

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል እየተካሄደ ነው ያለውን “የዘፈቀደ የጅምላ እስር” በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቀ |amnesty |Ethiopiainsider 

Подписаться
Просмотров 322
% 26

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአማራ ክልል እየተፈጸመ የሚገኘውን “የዘፈቀደ የጅምላ እስር” በአፋጣኝ እንዲያቆሙ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። በክልሉ ባሉ ትልልቅ ከተሞች የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እያካሄዱት ባለው ዘመቻ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መታሰራቸውንም ተቋሙ አስታውቋል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ባወጣው መግለጫ፤ በሰሞኑ ዘመቻ ለእስራት ከተዳረጉት ሰዎች መካከል በክልሉ ባሉ የፌደራል ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ ምሁራን እንደሚገኙበት አመልክቷል። የዓይን እማኞች ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደተናገሩት፤ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ሲቪል ሰዎች የታሰሩት ባለስልጣናት ይዘው የመጡትን “የስም ዝርዝር” መሰረት በማድረግ ነው።
ሆኖም እነዚህ ባለስልጣናት የብርበራም ሆነ የእስር ትዕዛዝ እንዳላቀረቡ ድርጅቱ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ በትላንቱ መግለጫው አስፍሯል። የተወሰኑት እስራት የተከናወኑት በምሽት እንደነበር እማኞቹ መግለጻቸውንም ድርጅቱ አክሏል። በእነዚህ እስራት ከፖሊስ አባላት ሌላ ወታደሮች ጭምር መሳተፋቸውንም የዓይን እማኞቹን ዋቢ አድርጎ ድርጅቱ ገልጿል።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ተጨማሪውን ለማንበብ ይሄን ሊንክ ይጫኑ ethiopiainsider.com/2024/14242/
-------------------------------------------------------------------------------------------
የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider.com​
ፌስቡክ ፦ ethiopiainsider
ትዊተር (ኤክስ) ፦ ethiopiainsider
ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaInsiderNews
ቲክቶክ፦ www.tiktok.com/@ethiopiainsider

Опубликовано:

 

2 окт 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 1   
@cliojojo
@cliojojo 6 дней назад
በርቱ አሪፍ ሚዲያ ነው