Тёмный

አሳዛኝ ዜና; ሁለት ባስ ሙሉ የደባርቅ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ታገቱ 

Muja Mercury
Подписаться 44 тыс.
Просмотров 121
50% 1

በርካታ ተማሪዎች ታግተዋል⚠️
ሰኞ እለት ተሳፍረው ወደ ቤተሰብ እየተጓዙ የነበሩ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን የዓይን እማኝ፣ የታጋች ቤተሰብና ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
አንድ ከእገታው አመለጥኩ ያለ ተማሪ ፥ ሶስት (3) አውቶብሶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እየተጓዙባቸው የነበሩ ረቡዕ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ ገብረ ጉራቻ የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ከ3 አውቶብሶች 2ቱን ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸው፣ ተሳፋሪዎቹን ካስወረዷቸው በኋላ አግተው ወደ ጫካ እንዳስገቧቸው፣ እርሱ ገለባ ውስጥ ተደብቆ እንዳመለጠ ገልጾ፣ “ የሁለቱ አውቶብስ ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተዋል ” ብሏል።
ከታጋቾቹ መካከል የሚያውቃቸው የIT ፣ የአኒሚል ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ፣ ያገቷቸው “የሸኔ ታጣቂዎች” መሆናቸውን አስረድቷል።
አንዷ የታጋች እህት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል፣ “ ረቡዕ 3 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ደወለችልኝ (እየሮጡ ነበር፣ የተኩስ ድምጽም ነበር) ‘በቃ ከአሁን ወዲህ ስልኬ አይሰራም። ላታገኝኝ ትችያለሽ በታጣቂዎች ታግተናል’ አለችኝ። መለሽ ስደውል ስልኳ አይሰራም ” ብላለች።
ቤተሰቡ ሁሉ በጣም ከፍተኛ ጭንቀት ላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ታጋቾቹን በህይወት እንዲያተርፏቸው ተማጽናለች።
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፤ የወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በበኩሉ፣ እገታው እውነት መሆኑን እንዳረጋገጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ኀብረቱ በሰጠው ቃል “ አጋቾቹ ለአንድ ተማሪ 400 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው። ‘ ገንዘቡን ካላመጣችሁ እንገድላችኋለን ’ እያሏቸው ይገኛል ” ሲል የሰማውን አስረድቷል።
የሞቱ ፣ የተጎዱ ስለመኖራቸው የደረሰው መረጃ እንደሌለ የገለጸው ማህበሩ ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ሁሉ ለማነጋገር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
በጉዳዩ ላይ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሰጠንን ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል።
©TikvahEthiopia

Опубликовано:

 

12 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
ФОКУС -СВЕТОФОР
00:32
Просмотров 336 тыс.
Cute
00:16
Просмотров 7 млн
ФОКУС -СВЕТОФОР
00:32
Просмотров 336 тыс.