Тёмный

የቤተክርስቲያንን ጥቃት አታሳየኝ ከቶ YeBetekristan Teqat Atasayegn Keto ዘማሪ፡ መላክ ሰላም ቀሲስ ተሾመ ጌታሁን የንስሐ መዝሙር 

Kessis Teshome Getahun
Подписаться 423
Просмотров 1,2 тыс.
50% 1

ዘማሪ፡ ዘማሪ፡ መላክ ሰላም ቀሲስ ተሾመ ጌታሁን
የቤተክርስቲያንን ጥቃት አታሳየኝ ከቶ
በአቅሌስያ ይታይ ያንተ ብርሃን ፈክቶ
ምሥጢራዊት ማኅበር የሆነች አካሌ
አምላክ ሆይ ጠብቃት ቢበዛም በደሌ
ምሥጢራዊት ማኅበር የሆነች አካሌ
ቤትህን ጠብቃት ቢበዛም በደሌ
አሐዱ አብ ቅዱስ ብሎ የቀደሰ
በመዓልት በሌሊት ስሙን ያወደሰ
የካሕኑ ደም ነው በግፍ የፈሰሰ
ይህንን ስሰማ ልቤ ተላወሰ(፪)
አዝ
በሰማዕታት ደም ስትታጠብ ኖራ
በቅዱሳኑ አጽም ቅጥሯ የተሠራ
እረፍት ያላገኘች አንዴም ከመከራ
ቤተክርስቲያን ነች የጌታ ሙሽራ(፪)
አዝ
በዮዲት ጉዲት እጅ በእሳት የነደደ
በግራኝ አሕመድ ለእምነቱ የታረደ
በዚህ ሁሉ አልፏል በተዋሕዶ ጸንቶ
ማዕተቡም አይላላ ልጅሽ ሞትን ፈርቶ(2)
አዝ
ፊደል የቀረፀች ሀገር ልታቀና
አደዋ የዘመተች ለሀገር ደጀን ሆና
ውለታዋ ተረስቶ የሚወጋት ቢበዛ
ይሄ ሁሉ ያልፋል እንደ ጠዋት ጤዛ
ስልጣንሁሉያልፋልእንደጠዋት ጤዛ
አዝ
እንደ ራሔል ዕንባ ዕንባዋ ፈሰሰ
የቤተክርስቲያን ድምጽ ከራማ ደረሰ
ተነስ አምላካችን በአንተ ነው ተስፋችን
ስምህ ነው ጋሻችንስምህነውጦራችን (2)

Опубликовано:

 

13 окт 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 13   
Далее
А я с первого раза прошла (2024)
01:00
Sematsenat
11:45
Просмотров 2,5 тыс.
Endet Beleh
6:08
Просмотров 10 тыс.
28 September 2024
6:41
Просмотров 151