Тёмный

ዳኛቸው ወርቁ (Dagnachew Worku) ፡ አወዛጋቢው ደራሲ፡ ህይወቱና ስራዎቹ 

Sewasew Official
Подписаться 1,2 тыс.
Просмотров 2,3 тыс.
50% 1

ዳኛቸው ልክ እነደ አባቱ ተራማጅ የሚባል ሰው ነበር። የዳኛቸው አባት አቶ ወርቁ በዛብህ ገና በወጣትነት እድሜው በድሬደዋ በኩል በባቡር ወደ ጅቡቲ ተጉዞ፣ ከዛም ወደ አውሮፓ ተሻግሮ ፈረንሳይ ገብቶ፣ በአንደኛው የዓለም ጦርነት የፈረንሳይ ወታደር ሆኖ የተዋጋ! በውጊያውም የቆሰለ፣ከዚያም በማዕድን ቁፋሮና በሆቴል መስተንግዶ ኑሮውን የገፋ ሰው ነበር። አቶ ወርቁ ከስደት ኑሮ ሲመለስ ትዳር መስርቶ ጎጆ ቀልሶ መኖር ጀመረ። ልጆችም ተወለዱ። ከተወለዱት ልጆች መካከል ደግሞ አንዱ አወዛጋቢው ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ ነበር።
የዳኛቸው እናት ልጇን የተገላገለችው አገር በጣሊያን ወረራ ምጥ ተይዛ በምትሰቃይበት ዘመን ነበር። የካቲት 16 ቀን 1928 ዓ.ም። ከደብረሲና ወጣ ብላ በምትገኝ አንዲት ገጠር ውስጥ። በፈረንሳይ አገር የኖረው የዳኛቸው አባት ለትምህርት የነበረው ቦታና ግንዛቤ ላቅ ያለ ስለነበር ቤተሰቡን ይዞ ወደ ደብረሲና አቀና። በዛም ዳኛቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን እስከ ስድስተኛ ክፍል ተከታተለ። 7ኛ እና 8ኛ ክፍልን ደግሞ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ተምሮ ሊሴ ገ/ማርያም ት/ቤት ገባ። ሊሴ ግን ለዳኛቸው ባህሪ የሚመች ዓይነት ት/ት ቤት ሆኖ ስላላገኘው ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ደብረሲና ተመለሰ።
ዳኛቸው በልጅነቱ የአባቱን ባህሪ እያጠና፣ የእናቱን ተረቶች እያዳመጠና እያብሰለሰለ ነበር ያደገው። ወደ ደብረ ሲና ከተመለሰ በኋላ ግን ከአባቱ ጋር ሊጣጣሙ አልቻሉም። “ከጓደኞቼ ጋር እንደልብ ጊዜ እንዳላኣሳልፍ ጫና ታደርግብኛለህ” ብሎ ወደ ደብረ ብርሃን ኮበለለ። ድብረ ብርሃንም ብዙ አልቆየም ትምህርቱን ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ገባ። በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በትምህርት ላይ እንዳለ ዳኛቸው ከባድ የጉሮሮ ህመም አጋጠመው። ለህይወቱ ያሰጋ የጉሮሮ ህመም! ይድናል ብሎ የጠበቀም አልነበረም! ዳኛቸው ግን ለመለዓከ ሞት እጁን ሳይሰጥ ቀረ። ዳነና ከተኛበት ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ወጣ። ይህ አጋጣሚ ለዳኛቸው ቤተሰቦች የልጃቸው ዳግም ልደት ነበር።
ዳኛቸው ከጉሮሮ ህመሙ ሲያገግም ኮከበ-ጽባህ መምህርነት ገባ ። ሁለት ዓመት በኮከበ-ጽባህ አስተምሮ ሀረር ዘለቀ። በሀረር መድኃኔዓለም ት/ት ቤት እያስተማረ “ሰቀቀንሽ እሳት” የሚል ትያትር ጽፎ ለመድረክ አበቃ። በተገኘችው ገንዘብ ደግሞ በድብረ ብርሃን ከጓደኞቹ ጋር ያሳለፈውን ህይወት የምትተርከው “ሰው አለ ብዬ!” መጽሀፉ ታተመች። በሀረር እያለ ዳኛቸው በጋዜጦች ላይ ጽሁፎቹን ያስነብብ ነበር። የሚያስነብባቸው ጽሁፎች ያነበባቸው መጻህፍት ላይ ያለውን ምልከታ የሚዳስሱ ነበሩ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ለማስተማር ሲወስን ዳኛቸው ከሀረር ገስግሶ ስድስት ኪሎ ደረሰ። ከመጀመሪያዎቹ የቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችም አንዱ ለመሆን በቃ። ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱ ደግሞ ወደ ውጭ አገር አቀና። ዳኛቸው ከ Iowa state university በ ስነጥበባት (fine arts) የሁለተኛ ዲግሪውን ያገኘ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን ይኅው ዩኒቨርሲቲ ለዳኛቸው ወርቁ ከዓመታት ብኋላ Honorary fellow of the International writers workshop Association of Iowa University ክብርን ሸልሞታል።
ዳኛቸው የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ ነበር አነጋጋሪ የሆነው መጽሀፉ “አደፍርስ” የተወለደው።
አደፍርስ በወቅቱ ከተለመደው የአማርኛ ስነ-ጽሁፍ ያፈነገጠ መጽሀፍ ነበር። ታትሞ ገበያ ላይ በአምስት ብር ዋጋ ቢቀርብም፣ ሰው አደፍርስን ገዝቶ ሊያነብ አልቻለም። ዳኛቸው አከፋፋዩ ጋር ሄደና ጠየቀ ...
እንዴት ነው?
“አንባቢው ዋጋው ተወደደብኝ” አለ። ሲል መለሰ አከፋፋዪ።
“አሉ? እንግዲያው ከአሁን ጀምሮ መጽሀፉ ላይ የዋጋ ማስተካከያ አድርጊያለሁ። ካሁን በኋላ የመጽሀፉ ዋጋ 10ብር ነው።” አከፋፋዩ የሚሰማውን ማመን አቃተው። “በአምስት ብር አልሸጥ ያለ መጽሀፍ ጭራሽ አስር ብር?!” ዳኛቸው ጥሎት ወጣ።
በሌላ ጊዜ ተመለሰና እንደገና ጠየቀ። “ኸረ! በጭራሽ እየተሸጠ አይደለም” አለ አከፋፋዩ። “እንግዲያው መጽሀፉ ዋጋው 15ብር ገብቷል” አለ ዳኛቸው። 5ብር አልሸጥ ያለውን መጽሀፍ 15ብር አስገብቶት አረፈው። አከፋፋዩ ግን ፈጽሞ 15ብር አይገባውም ብሎ ተከራከረ። “እንደውም ተወው የኢትዮጵያ ህዝብ የኔን መጽሀፍ አንብቦ ለመረዳት 20 ዓመት ይፈጅበታል”….ብሎ መጽሀፍቱን እንዳለ ለቃቅሞ ቤቱ ወሰዳቸው።
አደፍርስን ቤቱ ድረስ ሄደው በ15ብር የገዙት ሰዎች ግን ነበሩ። ከነዚህ መካከል ደራሲ ሳህለ-ሥላሴ ብርሃነ ማርያም አንዱ ናቸው። በሌላ በኩል በአደፍርስ መጽሀፍ ዙሪያ የሚስተናገዱት ሂሶች ጉራማይሌ ነበሩ። አንዳንዱ አደፍርስ ድንቅ ልቦለድ ነው ብሎ ሲያዳንቅ። ሌላው ደግሞ አደፍርስ የአማርኛን ስነ-ጽሁፍ ያደፈረሰ፣ቅጣንባሩ የጠፋ፣ ቲርኪ ሚርኪ ጽሁፍ ነው ሲል አጣጣለ። እንደነ አቤ ጉበኛ ያሉት ጭራሽ አደፍርስን በአሽሙር የሚነካ መጽሀፍ እስከማሳተም ደረሱ። “ጎብላንድ አጭበርባሪው ጦጣ” የተሰኘው የአቤ ጉበኛ መጽሀፍ በቀጥታ አደፍርስን ለማንቋሸሽ ታስቦበት የተጻፈ መጽሀፍ ነበር...
ሙሉውን ፅሁፍ የሚቀጥለው ሊንክ ላይ ያገኙታል፤
am.sewasew.com...
ለተጨማሪ ፅሁፎች የሰዋስው መተግበሪያዎችን ያውርዱ ወይም ድረ ገፃችንን ይጎብኙ!
sewasew.page.l...
#Dagnachew #ዳኛቸው #ወርቁ #ስነ #ፅሁፍ ታሪክ #ኢትዮጵያ #Worku #Art #History #Ethiopia

Опубликовано:

 

9 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 1   
@user-lm5pe8xt5j
@user-lm5pe8xt5j 26 дней назад
❤❤❤
Далее
▼ЮТУБ ВСЁ, Я НА ЗАВОД 🚧⛔
30:49
Просмотров 456 тыс.
አደፍርስ ክፍል 1
40:01
Просмотров 10 тыс.