Тёмный

ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ " እመ ምዑዝ " 

Biruk Tamiru Ethiopia ( ብሩክ ታምሩ)
Просмотров 953
50% 1

የካቲት 29-ባሕርን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን አገር ሄዳ ወንጌልን የሰበከችው ታላቋ ሐዋርያዊት እናታችን የእመ ምኡዟ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዕረፍቷ ነው፡፡ ለእርሷም እመቤታችን ተገልጣላት በጌታችን መከራ ሞት ምክንያት ስለደረሱባት ሀዘናት የነገረቻት፣ የፈለገችውንም ታደርግበት ዘንድ የእጇን መስቀል የሰጠቻት ሰሆን ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሄዳ ስንዴን በአንድ ቀን ብቻ ዘርታ፣ አብቅላ፣ አጭዳ፣ ፈጭታ ለምግብነት አብቅታ ከመገበቻቸው በኋላ እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን የሠራችላቸውና ቅዱስ ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ጽፋ ያስቀመጠችላቸው ሐዋርያዊት እናታችን ስትሆን በሌላም በኩል ሙታንን እያስነሣች ለዐፄ ሱስንዮስ ስለእውነት እንዲመሰክሩለት ታደርግ የነበረችና እርሷም ራሷ አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕትነትን የተቀበለችና ጌታችን ከሞት ያስነሣት ቅድስት ናት፡፡
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የከበረ አባ ቢላካርዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን የደረሰ ሲሆን ፈጽሞ እስካረጀም ድረስ አርሞኒ በምትባል አገር ላይ በኤጲስቆጶስ ተሾሞ ያገለገለ ነው፡፡ ከደረሳቸው ብዙ ድርሳናትና ተግሣጻትም ውስጥ ስለከበረች የጌታችን ልደት በዓል፣ የብርሃን እናቱ ስለሆነች ስለ እመቤታችን፣ ስለሞትና ስለ መቃብር፣ በኃጥአን ላይ ስለሚደርስባቸው ሥቃይ፣ ስለ መድኃኒታችን የረቀቀ ጥበብ፣ ስለከበሩ በዓላትና ስለሌሎችም ብዙ ምሥጢራት ሕይወት በሆኑ ትምህርቶቹ ብዙ ድርሳናትን በመጻፍና በማስተማር ብዙ ነፍሳትን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡
መልአካም በሆነው አገልግሎቱ እግዚአብሔርን እያገለገለ ሳለ ከሃድያን ተነሥተው አምልኮተ ጣዖትን ሲያስፋፉ በክርቲያኖችም ላይ ስደትና ዕልቂት በሆነ ጊዜ አባ ቢላካርዮስ በክብር ባለቤት በጌታችን ስም ደሙን አፍስሶ ሰማዕትነትን ይቀበል ዘንድ ተመኘ፡፡ ሕዝቡንም ሰብስቦ እስከመጨረሻው ድረስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መከራቸው፡፡ ነገር ግን እርሱ ለሰማዕትነት የተዘጋጀ ነውና ካሁን በኋላ በሥጋ እንደማያገኙት በመንገር ተሰናበታቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ እያዘኑና እያለቀሱ ‹‹የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ?›› እያሉ በመለመን ወደ ሰማዕትነት እንዳይሄድ ለማስቀረት ብዙ ለፉ፡፡ ነገር ግን ማስቀረት አልተቻላቸውምና አባ ቢላካርዮስ ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ወደ ከሃዲው መኮንን ዘንድ በመሄድ በፊቱ ቆሞ በጌታችን ስም ታመነ፡፡ የረከሱ የንጉሡን አማልክት በመርገም የጌታችንን ዕውነተኛ አምላክነት ጮኾ መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ብዙ አሠቃየው፡፡ ሕዝቡም ብዙ ልመናን አብዝተው በመለመን ራሱን እንዲያድንና ከከተማው እንዲወጣ ግድ አሉት፡፡ እርሱም ልባቸውን ደስ ለማሰኘት እሺ አላቸው፡፡ ነገር ግን በዚያች ሌሊት መልአክ ተገለጠለትና የተመኘውን ሰማዕትነት በድል እንዲፈጽም ነገረው፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ቢላካርዮስ በመኮንኑ ፊት ቆሞ አሁንም የረከሱ የንጉሡን አማልክት በመርገም የጌታችንን ዕውነተኛ አምላክነት መሰከረ፡፡ በዚህም ጊዜ መኮንኑ እጅግ ተቆጥቶ የአባ ቢላካርዮስን አንገት በሰይፍ እንዲቆርጡ ጨፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ አባ ቢላካርዮስም ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ለኤጲስቆጶሳት በሚገባ ክብር አክብረው ቀበሩት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፡- እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ወይም እመ-ምዑዝ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደራ ፎገራ አንበሳሜ በሚባለው ቦታ የአብርሃምና የሣራ ምግባር ካላቸው ከአባቷ ከላባ ከእናቷ ከወንጌላዊት ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን በታዘዘ መልአክ አብሳሪነት ተወለደች፡፡ በተወለደችም ጊዜ በእግሯ ቆማ ‹‹በማኅየዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል›› ብላ አምላኳን አመስግናለች፡፡ ቤተሰቦቿ ያገኙዋት በስዕለት ሲሆን ስመ ክርስትናዋም ማርያም ጸዳለ ተባለ፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የሚለው የቆብ (የምንኩስና) ስሟ ነው፡፡ ዕድሜዋ ለትምህርት እግዚአብሔር የላከው አንድ ደገኛ መነኩሴ ወደ እርሷ በመሄድ የዳዊትን መዝሙር፣ የብሉያትና የሐዲሳት መጻሕፍትንና የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ በሚገባ አስተምሯታል፡፡

Опубликовано:

 

7 мар 2022

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
ገድለ ቅድስት በርባራ ወ ዩሊያና።
1:10:03