Тёмный

🎯 ራስህ ላይ አተኩር ! |🎯 ለዓላማህ እቅድ አስቀምጥ ! | 🎯 አሁን ጀምር ! | 🎯 ስንፍናን ማሸነፍ | dawit dreams | inspire Ethiopia| 

  Lifestyle Ethiopia
Подписаться 57 тыс.
Просмотров 4,8 тыс.
50% 1

የ 'Online' ስልጠናችንን መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ስልክ መደወል ወይም ቴሌግራም ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ትችላላችሁ ።☎️+251977333377
የሶስት ወራት S.M.A.R.T፣ እቅድ አቅድ ||
ሕይወትህ ላይ የምር አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮችህ ላይ ለማተኮር የሚረዳህ መንገድ S.M.A.R.T እቅድን ማቀድ ነው፡፡ S.M.A.R.T እቅድ በየሶስት ወሩ እንደ አዲስ የሚታቀድ እቅድ ነው። ለአዲሱ አመት ይህን አደርጋለሁ ብለህ ለአመት ከማቀድ አመቱን በአራት መንፈቆች መክፈል የተሻለ ውጤትን ያመጣል፡፡
S.M.A.R.T ምን ማለት እንደሆነ አብራርተን እንጀምር፡
S.M.A.R.T ማቀጃ መንገድን በነሃሴ 1981 በማኔጅመንት ሪቪው መጽሄት ላይ ጆርጅ ዶራን አስተዋወቀው፡፡
ሲተነተንም፣
Specific (ውስን)
Measurable (የሚለካ)
Attainable (ሊደረስበት የሚችል)
Relevant (አስፈላጊ)
time-bound (በጊዜ የተገደበ)
እንዴት እንደሚሰራ እንመልከት፡
specific (ውስን)
ውስን እቅድ ስድስቱን ጥያቄዎች ይመልስልሃል (ማን፣ ምን፣ የት፣ መቼ፣ የቱ እና ለምን?)
ስድስቱንም ጥያቄዎች ስትለይ ግብህን ለማሳካት ምን አይነ ተግባራት እንደሚያስፈልጉህ ትለያለህ
ማን፤ ተሳታፊው ማን ነው? (እቅድህ ውስጥ አንተን ጨምሮ ማን ይሳተፍበታል? ቤተሰብ፣ ሚስትህ ወይም የስራ ባልደረቦችህ?) ምን፤ ምን ማሳካት ትፈልጋለህ? የት፤ እቅድህን የት ነው የምትተገብረው? (ቦታ) መቼ፤ መቼ ልታደርገው አቅደሃል?
የቱ፤ ግብህን ለማሳካት የትኞቹን መንገዶች ትጠቀማለህ? የትኞቹስ ችግሮች በመንገድህ ይጋረጣሉ? ችግሮቹን ለመቅረፍስ የትኞቹን መፍትሄዎች ትጠቀማለህ? ለምን፤ ለምን ታደርገዋለህ? እቅዶችህን መወሰን እጅግ በጣም ጠቃሚ ተግባር ነው። ምክንያቱም በጊዜ፣ በቦታ እና በግብህ የት ላይ እንደደረስክ (ልክ እንደመንገድ ላይ ኪሎ ሜትር አመልካች ድንጋዮች) ያመላክትሃል። ግብህንም ስታሳካም ይታወቅሃል።
M easurable (የሚለካ)
የሚለካ ግብ፤ በጊዜ፣ በመጠን ወይም በሌሎች መለኪያ መንገዶች ግልጽ ሆኖ መቀመጥ አለበት - ወደ ግብህ የሚያደርስህን ማንኛውንም መንገድ አፈጻጸሙን መለካት አለብህ።
የሚለካ ግብን ማስቀመጥ ከሀ ወደ ለ ምን ያህል መንገድን እንደተጓዝክ ግልጽ ያደርግልሃል፡ የሚለካ ግብ በትክክለኛው አቅጣጫ እየሄድክ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ይነግርሃል። በአጠቃላይ የሚለካ ግብ “እንዴት” እና “ምን ያህል?” የሚሉ ጥያቄዎችን ይመልስልሃል፡
A ttinabl (ሊደረስበት የሚችል)
ሊደረስባቸው የሚችሉ ግቦች የአንተን የመጨረሻ አቅም ለመፈጸም የሚቻሉም ናቸው፡፡ ሊደረስበት የሚችል ግብ ለማቀድ ዋነኛው ቁልፉ አሁን ያለህበትን ሁኔታ መመልከት እና ከአቅምህ አንጻር ልትደርስባቸው የሚችሉ እቅዶችን ማስቀመጥ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ፈተናዎች እና መሰናክሎች ስለሚበዙብህ፣ ከቻልክ ከአቅምህ ትንሽ ከፍ ያለ ግብን አቅድ፤ ብትወድቅ እንኳ የሆነ ነገርን አሳክተህ ትወድቃለህ።
R elevant (አስፈላጊ)
አስፈላጊ ግቦች የምር የምትፈልጋቸው ስኬቶችህ ላይ ያተኩራሉ። ትርፍ እና የቅንጦት አይደሉም᎓᎓ የሚመሰረቱትም በአንተ መሰረታዊ ፍላጎቶች ዙሪያ ነው፡፡ ከስራ ስኬትህ እስከ የምትወዳቸው ሰዎች ደስታ እና ሌላም ለሕይወቴ ስኬት ናቸዉ ብለህ የምታስባቸውን ነገሮች በሙሉ ያጠቃልላል::
Time-bound (በጊዜ የተገደበ) በጊዜ የተገደቡ ግቦች የማለቂያ ቀን አላቸው፡፡ ከዛችም ቀን በፊት የግድ ግብሀን መምታት አለብህ። በጊዜ የተገደቡ ግቦች አድካሚ እና አዳጋች ናቸው፡፡ እቅድህን በዛሬ ወይም ለአንድ ሳምንት ለሶስት ወር ወይም ለአምስት አመት ልትገድበው ትችላለህ:: ወይም በጊዜ የተገደበ ግብን ለማስቀመጥ ቀላሉ መንገድ ከመጨረሻው ቀን ጀምረህ ወደ መጀመሪያው ቀን ማቀድ ነው።
S.M.A.R.T እቅዶች ግልጽ እና በደንብ የተብራሩ ናቸው መጨረሻው ቀን ላይም ግብህን በከፊል ወይም በሙሉ እንዳሳካ ወይም ጭራሽኑ እንዳልተሳካልህ በእርግጠኝነት ታውቃለህ፡፡ እንደምሳሌ ከዚህ በፊት ባነሳናቸው ሰባቱ ከባቢዎች ዙሪያ S.M.A.R.T. ግብን እንዴት እንደምታስቀምጥ እንመልከት፡
• ስራ፤ “በሁለት ወራት ውስጥ የካፌ ቤት ስራዬን የሚያሳድጉ የማስታወቂያ ስራዎችን እሰራለሁ፡፡ በሶሻል ሚዲያ የማስታወቂያ ዘመቻ እጀምራለሁ፤ በራዲዮ እና በቴሌቪዥን ማስታወቂያ አስነግራለሁ፤ ከአራት በላይ ሆነው ለሚመጡ ደንበኞች የ25% የዋጋ ቅናሽ አደርጋለሁ፡፡'
• ቤተሰብ፤ “ከቤተሰቦቼ ጋር ያለኝን ግንኙነት የበለጠ አጠናክራለሁ። በየስድስት ወርም ለሽርሽር ወደ ታሪካዊ ቦታዎች ይዣቸው _ እሄዳለሁ፡፡ በየወሩ መጨረሻም ስለጉዟችን ለአንድ ሰዓት ያህል እቅድ እናወጣለን፡፡"
ጋብቻ/የፍቅር ግንኙነት፤ “አርብ ምሽት ላይ ከሚስቴ ጋር እራት እበላለሁ፤ ስለ እራት ፕሮግራማችንም ማክሰኞ እለት ላይ ለሰላሳ ደቂቃ አቅዳለሁ።''
• መንፈሳዊነት፤ “በየቀኑ ለአምስት ደቂቃዎች ስለተደረገልኝ መልካም ነገር እና ገና ስለሚሆኑልኝ ነገሮች ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ፡፡ ይህንንም ልማዴን ሁሌም ከቁርሴ በፊት አደርገዋለሁ”
መዝናኛ፤ “በሳምንት ለሁለት ሰዓታት ስዕልን መሳል እለማመዳለሁ። ይህም ጭንቀቶቼን እና ውጥረቶቼን በስዕል ለማውጣት ይጠቅመኛል፡፡”
• የሕይወት መመሪያ፤ “በየወሩ ከማገኘው ገቢ 10% እቆጥባለሁ፤ በሚቀጥለው አዲስ አመትም አዳዲስ የቤት እቃዎችን እገዛለሁ”
• ጤና፤ “እስከ ነሃሴ 30 ድረስ በቀን ለሰላሳ ደቂቃ፣ በሳምንት ለሶስት ቀናት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እሰራለሁ፡፡”
መልካም ቀን || t.me/Lifestyle... #Lifestyleethiopia #አስተያየት_ካሎት251977333377ይደውሉልን #Ethiopia #AddisAbaba #comedy #ethiopiantiktok #Motivation #dawitdreams #etiopianmotivetion #personaldevelopment #EthiopianMotivationalspeaker #inspiration #morningmotivetion #motivation #motivationalquotes #success #successquotes #successmindset #successful #positivevibes #positivity #positivequotes #positivethinking #life #quotes #quoteoftheday #quotestoliveby #quotesaboutlife #lawofattraction #lawofattractionquotes #truesayings #truequotes #wisequotes #bestquotes#Harmet#Harmetmidea#Dorze#arbaminchdorzevileg#maya#ebc#travler #thesuccesselite #dawit #ethiopiannew #newyear #newevent #newclassye #habesha #ethiopia #habesha #africa #ethiopian #addisababa #ethiopianwomen #eritrea #habeshabeauty #ethio #ethiopianfood #habeshawedding #habeshastyle #habeshakemis #habeshafashion #eritrean #habeshadress #ethiopians #amharic #rastafari #habeshaqueens #ethiopiancoffee #ethiopianmusic #addisabeba #habeshagirl #love #oromo #reviewethio #habeshamemes #african #rasta#photography #habeshabrides #kenya #tigray #ethiopianculture #culture #eritreanwomen #ethiopianbeauty #habeshas #fashion #ethiofollow #habeshacomedy

Опубликовано:

 

28 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 32   
@zenebechkefeni9822
@zenebechkefeni9822 2 года назад
በመጀመሪያ ይህን ጥበብና ማስተዋል የሰጠህ ፈጣሪ ሰሙ ይክበር ።እኔ ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነቱን የሕወት ለውጦችን ለመጀመር አስብ ነበር አሁን ግን ሕይወትን አንድ ብዬ እንድጀምር ይህ ትም/ት ቁርጠኝነትና አቅም ሰቶኛል ከእግ/ር ጋር በጣም ውጤታማ እንደምሆንበት አልጠራጠርም አምላክ ሁለንተናህን አብዝቶ ይባርክ
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን🙏 zenebech " ከቻልሽ ከቀን አንድ ጀምሮ በማስተዋል እንትከታተይ እናበረታታሻለን, ያልተረዳሻቸው ሃሳቦች ካሉ . መጠየቅ ትችያለሽ በተጨማሪም ቴሌግራም ላይ መቀላቀል ትችያለሽ @LifestyleEthiopia ብለሽ 🙏❤
@zenebechkefeni9822
@zenebechkefeni9822 2 года назад
@@lifestyleethiopia አመሠግናለሁ ከቀን አንድ ጀምሬ የተወሰኑትን ዳውሎድ አድርጌአለሁ ቤት ስገባ ማስታወሻ እያዝኩነው የምከታተልህ ስራ ቦታ ሆኜ ስለሆነ አይመችም ቴሌግራም ላይም ለመግባት ሞክራለሁ ትም/ቱን በጣም ነው የወደድኩት።ተባረኩ
@ሁሉምነገርለበጎነው-ጘ6ኘ
🎁🎁👍👍
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤❤
@hailaygebrelibanosngusehai1007
@hailaygebrelibanosngusehai1007 2 года назад
1
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን 🙏❤
@tsahayfantoo2373
@tsahayfantoo2373 Год назад
በጣም ደስ ይላል ፍርዬ
@tesfamariamteklu6434
@tesfamariamteklu6434 2 года назад
እጅግ በጣም ጠቃሚ ት/ት ነው የሰጠኼን እግዚአብሔር ከነቤተሰብህ ዕድሜና ጤና ይስጥህ። ነገር ግን አልፎ- አልፎ የምትጠቀማቸው ኃይለ ቃሎችን ማሰወገድ/ባትጠቀም የሚል የግል አስተያየት አለኝ።
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤🙏🙏
@ZedoVlogs
@ZedoVlogs 2 года назад
ጠፋህብን ፍርየ Zoom lay ነው ስልጠናው እንደት ነው መሰልጠን የምፈልገው
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
ሠላም zedo ቴሌግራም ላይ ነው @LifestyleEthiopia ብለ ግባ 🙏❤
@ZedoVlogs
@ZedoVlogs 2 года назад
@@lifestyleethiopia esh Amesegnalehu
@ሁሉምነገርለበጎነው-ጘ6ኘ
ይህን የማሰለው ውብ ትምህርት የሚካታተል ሰው አለማኖሩ የሰዝናልም የሰፍረል ወገኖች ሼር አድርጉት ሌሎችም ይጣቀሙበት ወላሂ እኔ ዩቱብ ተጠቃሚ ብሆን አንድም ሰአት ሰልቆይ ሼር አደርገው ነበር
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤🙏
@grumieayele2022
@grumieayele2022 Год назад
1
@adanechtegegne8559
@adanechtegegne8559 2 года назад
0
@salamnahoom2664
@salamnahoom2664 2 года назад
እግዚአብሔር ይክብርልኝ
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia Год назад
እናመሠግናለን🙏❤
@netsanetspiritualtube6118
@netsanetspiritualtube6118 2 года назад
ሙዚቃው ይረብሻል
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤🙏
@melatzerihun6468
@melatzerihun6468 Год назад
Thank you
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia Год назад
Thanks for watching
@nardostadesse453
@nardostadesse453 Год назад
1
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia Год назад
እናመሠግናለን 🙏❤
@remli112
@remli112 2 года назад
እናመሰግናለን ይህ ት!ት የት ነው የሚሰጠው????
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
online ላይ 🙏❤ እናመሠግናለን❤🙏
@ሳባዘርአይ
@ሳባዘርአይ 2 года назад
እጅግ በጣም ነው ማመሰግንህ ዋው
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤🙏
@enewaenewaenewa6885
@enewaenewaenewa6885 2 года назад
ሰላማችሁ ይብዛ ከልብ እናመሰግናለን ኑሩልን
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
ሠላም ሠላም❤🙏 በርቺ
@enewaenewaenewa6885
@enewaenewaenewa6885 2 года назад
@@lifestyleethiopia እሽ እየበረታሁ ነው ምርጦችየ ሰላም ሁኑልኝ አምላክ የሰጠኝ ስጦታየ ናችሁ ቃላት የለኝም ብዙ ለውጥ አምጥቻለሁ የናንተው ትምህርት ለየት የሚያደርገው በደንብ አብራርታችሁ የምታስተምሩት ሽ አመት ኑርልን ቅዱስ ህያው እግዚአብሔር ብሩህ አይምሮ ሰጥታችኃልና ይጨምርላችሁ በማያልቀው ስጦታው አሜን።።።።።።።።።።።።።።።።
Далее
ራስህ ላይ አተኩር!
17:19
Просмотров 324 тыс.
Bearwolf - GODZILLA Пародия Beatrise
00:33
Просмотров 78 тыс.
Это нужно попробовать
00:42
Просмотров 234 тыс.
ራስህ ላይ ስራ!
14:34
Просмотров 366 тыс.
ጥያቄ እና መልስ 2
2:17:10
Просмотров 15 тыс.
Bearwolf - GODZILLA Пародия Beatrise
00:33
Просмотров 78 тыс.