Тёмный

💧 ጠብታ ማር : ክፍል - 2 🔔 ከሰዎች ጋር ለመግባባት የሚረዱ ዋና ዋና መንገዶች 

አብሪ መፅሐፍት 🪶 Abri Books
Просмотров 61
50% 1

00:17 ከሰዎች ጋር ለመግባባት የሚረዳ ትልቅ ሚስጥር
11:52 ይህን ማድረግ የሚችል ሁሉም ሰው ይደግፈዋል
20:10 ይህን ካደረክ የትም ተቀባይነት ታገኛለህ
31:00 ከሰዎች ጋር እንዴት በቀላሉ መግባባት ይቻላል?
▶ ርዕስ - ጠብታ ማር
📝 ፀሀፊ - ዴል ካርኒጌ
📜 ዘውግ - ስነ-ልቦናዊ እራስ አገዝ
📝 ተርጓሚያን - ባሴ ሀብቴ እና ደምሴ ፅጌ
📅 የህትመት ዘመን - 1989
📖 የገፅ ብዛት - 95
🎙️ተራኪ - በአካል መንግስቱ
“በውስጤ ያሉትን ጥሩ ነገሮች ሁሉ ያገኘሁት ከመጻሕፍት ነው፡፡ በሳይንስ ወይም በቀለም ሰዎች የተጻፉ መጻሕፍትን ካላነበብን የሰውን ምንነት ለማወቅ በማንችልበት አለም ውስጥ ነው የምንኖረው::” ይላል ማክሲም ጐርኪ የመጽሐፍትን ምንነት ሲገልፅ ።
መጻሕፍት ለተለያየ አላማ ይጻፋሉ:: ለማስተማር ፣ ለማዝናናት ፣ እወቀትን ፣ ታሪክን ባህልንና ወግን ሌላውን ቅርስ ሁሉ ለትውልድ ለማስተላለፍ ይጻፋሉ ።
የልብ ወለድ ፅሁፍ አለ ልቦለድ ያልሆነም አለ። ሌላው አገር ስለብዙ ነገር ይጻፋል እንደአገራችን ሳይሆን ሳይንሱ ፣ ታሪኩ ፣ ጆግራፊው ፣ ስነ-አእምሮው ፣ አንትሮፖሎጂው ፣ ምግብ አቀቃቀሉ ፣ ልብስ አለባበሱ ፣ አተኛኘቱ ሁሉም በየዘርፉቸው ይጻፍባቸዋል። ሰውና ኑሮውን ፣ ሰውና ሰውን በተመለከተ የተጻፉትን ለመዘርዘር ወረቀትም ጊዜም አይበቃም ብቻ ስለ ሰው ብዙ ተጽፏል። እየተጻፈም ነው ።
በአውሮፓና በአሜሪካ ኑሮህን እንዲህ ኑረው የሚሉ መጻሕፍት በየቀኑ ገበያ ላይ እንደሚውሉ ይወሳል። ስለሥራ ፣ ስለጋብቻ ፣ስለወሲብ ፣ ከራስና ከሰዎች ጋር ተስማምቶ ስለመኖር የሚጻፉት አያሌ ናቸው ።
ባገራችን አልፎ አልፎ ከላይ በተጠቀሱት ርዕሶች አንዳ ንድ መጻሕፍት እንደመስቀል ወፍ ብቅ ቢሉም ስለኛ በቂ ተፅፋል ለማለት ሚያስደፍር ደረጃ ላይ አልደረስንም።
ዝናቸው በመላው አለም የናኘውና በተለያየ ቋንቋዎች በሚሊዮን ኮፒ ተራብተው የሚሸጡት የዴል ካርኒጌ መጽሐፍት በጥቅሉ በኑሮ ትግል ውስጥ እንዲሳካላቸሁ ይህን አድርጉ ያን አታድርጉ እያሉ ከሚያስተምሩና ከሚመክሩ መጻሕፍት ጐራ ነው እሚመደቡት
“ሰዎች ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ችሎታ ሙሉ በሙሉ እንዲጠቀሙበት ለማስቻል ነው የጻፍኩት” ይላሉ ካርኒጌ ስለመጻሕፎቻቸው ሲያወሱ
“እውቀት ለኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮችን አሟልቶ መገኘት ነው” ይላሉ ዶክተር ጆን ሂበን
“የትምህርት አላማ ማወቅ ሳይሆን ማድረግ ነው” ይላል የታወቀው ፈላስፋ ኸርበርት ስፔንሰር። ዴል ካርኒጌም መጽሐፎቹ ሁሉ የድርጊት መጽሐፎች” ናቸው ይላሉ። እናም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ፍርሀትን ጭንቀትንና አይን አፋራነትን አስወግደን በራሳችን ተማምነን ከሰዎች ጋር ተግባብተን የምንኖርበትን ጐዳና ነው አብርተው ሊያሳዩን የሚሞክሩት:: ሰው የማወቂያ መሳሪያውን እንጂ እውቀትን ይዞ አይደለም ከናቱ ማህፀን የሚወጣው። ሁሉንም ነገር የሚማረው በኋላ ነው። እየኖረ ይማራል እየተማረ ይኖራል ። የዴል ካርኒጌ መጽሐፍት ኑሮን እየኖርን እንዴት እንደምንማረው ነው የሚያሳዩን ።
ለመሆኑ ዴል ካርኒጌ ራሳቸው ምን አይነት ሰው ነበሩ?
ዴል ካርኒጌ ከደሀ ቤተሰብ ነበር የተወለደው። የገበሬ ልጅ ነው። በጠዋት ተነስቶ ላሞች ያልባል ፣ እንጨት ይቆርጣል ፣ አሳማዎችን ይቀልባል ይህንን ካከናወነ በኋላ ነበር ት/ቤት ለመሄድ የሚዘጋጀው:: ይህ አድካሚ ሥራ ዴል ካርኒጌን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ትምህርቱን እንዲያቋርጥ ምክንያት ሆኖ ነበር ።
እንደምንም ኮሌጅ ገባ ሆኖም አባትየው የኮሌጁን ክያፍ ሊከፍሉለት ባለመቻላቸው በቀን 62 ማይልስ በፈረስ ጀርባ መጓዝ ነበረበት።
ዘወትር ከሚለብሰው ሌላ ቅያሬ ልብስና ጫማ ስላልነበረው ከክፍል ጓደኞቹ ጐን ደፍሮ ለመቆም ጉልበቶቹ ይንቀጠቀጣሉ
ቀስ በቀስ የበታችነት ስሜት እያደረበት መጣ። ወጣቱ ካርኒጌ ፈሪና አይንአፋር በራሱ የማይተማመን ሆነ። ችሎታውን በተግባር መተርጐም እስከሚያቅተው ድረስ ወረደ
ይህንን የተገነዘቡት እናቱ በክርክር ክበቦች ውስጥ እንዲሳተፍ አበክረው ይገፋፉት ነበር። የሳቸውን ምክር ተቀብሎ ሞከረ። አልተሳካለትም የጓደኞቹ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆን አልፎ በሁለት እግሩ ሊቆም አልቻለም
በየክበቡ እየገባ ብዙ ከሞከረ ብዙ ከወደቀ በኋላ በመጨረሻው ተሳካለት። ይህ ድል ለተሳካ ኑሮ የሚያስፈልገውን በራስ መተማመንና በሚያደርጋቸው ነገሮች እርግጠኛ መሆንን አስገኘለት:: በአንድ አመት ውስጥ የተለያዩ ክርክሮችን አሸንፎ ስም ያለው ተናጋሪም ወጣው ።
ይህን ያዩ ተማሪዎችም ከሱ ምክር ለመጠየቅ ይጐርፉ ጀመር። በትግል ያገኘውን እውቀት አካፈላቸው ብዙዎቹ እንደሱ ተሳካላቸው
ዴል ካርኒጌ የደረሰበትን የበታችነት ስሜት ለማስወገድ ባደረገው ትግል ሀሳብን ለአንድ ወይም ለብዙ አድማጮች ለማስተላለፍ የሚያስፈልገው በራስ መተማመን መሆኑን ተረዳ በዚያም አላቆመ በራስ መተማመን ሰውን በየትም ቦታ ከሌሎች እኩል በሁለት እግሩ የሚያቆመው መሆኑንም ተገንዝቧል::
ሰዎች እርስ በርሳቸው የሚያደርጉትን ግንኙነት ለመረዳት መሞከር ብቻ ሳይሆን መመሪያ የሚሆኑ መጽሐፍትን ማዘጋጀት ጠቃሚ መሆኑን በመገንዘቡ How to win friends and influence people, How to stop worrying and start living, How to develop self Confidence and influence people by public speaking. የተሰኙ መጻሕፍትን ያቀረበ ሲሆን እነዚህ መጽሐፍት ዛሬ በመላው አለም በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው በሚሊዮን ኮፒዎች ተሠራጭተዋል::
የማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ ቦታዎን ይምረጡ!
Choose your right social media niche!
#አብሪመፅሐፍት #Abribooks #መፅሐፍ

Опубликовано:

 

30 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
Вопрос Ребром - Серго
43:16
Просмотров 342 тыс.
Se las dejo ahí.
00:10
Просмотров 6 млн
🪶 ጠብታ ማር - ሙሉ መፅሐፍ
3:08:51