Тёмный

📆 በ 21 ቀን ራስን መቀየር | ወስኖ ራስን መለወጥ | ያንት አመት ነው | ዶ/ር ዮናስ ዘውዴ| dawit dreams | inspire Ethiopia| 

  Lifestyle Ethiopia
Подписаться 57 тыс.
Просмотров 7 тыс.
50% 1

የ 'Online' ስልጠናችንን መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ስልክ መደወል ወይም ቴሌግራም ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ትችላላችሁ ።☎️+251977333377
መንገድ 1
ላንተ ጠቃሚ የሆነውን ለይ
ትርጉም ያለው ግብን መምታት ማለት በሁሉም የሕይወትህ ክፍሎች ስኬታማ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ግልጽ ነው፤ ቀንህን ብዙ ልታሳካቸው በምትፈልጋቸው ግቦች ከሞላኸው ጭንቅላትህ ይወጠራል። አዎ፣ ስለወደፊት ማሰብ አለብህ፤ ነገር ግን በዛው ልክ ስለአሁኑ የምትኖርበት በቂ ጊዜ ያስፈልግሃል።
ከሶስት ወይም ከአራት ያልበለጡ የሕይወት ከባቢዎችህ ላይ ብቻ ብታተኩር ተመራጭ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ያየናቸውን ሰባት የሕይወት ከባቢዎችን በማየት መጀመር ትችላለህ፡፡ ከእነሱም ውስጥ አሁን ላይ ላንተ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑትን ምረጥ፡፡ ከባቢን ከመምረጥ ጀምሮ ግብህን እስክታሳካ ድረስ ያለው መንገድም ፈታኝ እና አስደሳች ሆኖ ታገኘዋለህ።
መንገድ 2
የሶስት ወር ግብ ላይ አተኩር
ስቲቭ በተደጋጋሚ የረዥም ጊዜ እቅዶቹ ተበላሽተውበታል፤ የዛሬ ወር በማያስታውሳቸው እና የዕለት ተእለት አስቸኳይ ጉዳዮች ይራወጥ ነበር፡፡ እናም አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት ወሰነ፤ የረዥም ጊዜ እና ትላልቅ ግቦቹን በሶስት በሶስት ወራት መከፋፈል፡፡
አንተ ለምን የሶስት ወር ግብ ላይ ማተኮር አስፈለገህ?
ምክንያቱም ሕይወት በየዕለቱ _ ካሰብከው ፍጥነት በላይ ትቀያየራለች። እናም ለውጡን ለመከተል ካሰብክ የአጫጭር ጊዜ ግቦችን ማስቀመጥ አለብህ። ከሚመጣውም ተለዋዋጭነት ጋር እራስህን እያጣጣምክ፣ ጉልበትህን ሳታባክን እና ተስፋ ሳትቆርጥ እንድትጓዝ ይረዱሃል።
ስቲቭ ካሳለፈው ልምድ በመነሳት እንዲህ ይላል፦ “ከስድስት ወር በላይ የሆኑ እቅዶች ተስፋ አስቆራጭ ናቸው፤ ግብህ አንድ ወር እንደቀረው ስታስብ የሚኖርህ ተነሳሽነት እና ግብህ አንድ አመት እንደቀረው ስታስብ የሚኖረው ተነሳሽነት እጅግ በጣም ይለያያል። ለአንድ አመት የተለጠጠ እቅድ ስታስብ፣ ዛሬ መስራት ያለብህን ስራ ለሳምንት ታሸጋግራለህ፤ የሳምንቱ _ ስራህንም _ ለቀጣይ እያልክ ከእቅድህ ግማሹን እንኳ ሳትፈጽም አመትህ ያልቃል።"
እናም ነገሮችን ቀለል ለማድረግ፣ በሕይወትህ ውስጥ ካሉት ከባቢዎች ሶስት ወይም አራቱን መርጠህ የ S.M.A.R.T፣ እቅድ መንደፍያ መንገድን በመጠቀም በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ሊያበቃ የሚችልን ግብ አቅድ።
መንገድ 3
የእቅድህን አፈጻጸም በየሳምንቱ ገምግም፤ ለቀጣዩም ሳምንት አቅድ ሌላ ብዙ ስራዎች እያሉብህ የግብህን እቅዶች ሳታቋርጥ እና ከስር ከስር መከታተል ቀላል አይደለም። ቢሆንም ለዚህ ችግር ቀለል ያለ መፍትሄ አለው፤ ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናቶች የምታደርጋቸውን እና ወደ ግብህ የሚያደርሱህን ተግባራት የመርሃ ግብር ሰንጠረዥ (Schedule) አውጣላቸው::
በGetting Things Done መጽሃፉ ዴቪድ አለን ስለ አንድ ሳምንት ግምገማ አብራትቶ ጽፏል። ቀላል ነው፤ በሳምንት ውስጥ ካሉት ቀናት አንዱ ቀን ምረጥ (እሁድ ቀን ተመራጭ ነው)። ቀጣዮቹን ሰባት ቀናት ተመልከታቸው፤ በየዕለቱ ልትፈጽማቸው የምትፈልጋቸው እና ከግብህ ጋር የተያያዙ ተግባራትን መርሃ ግብር አስይዛቸው።ይህንንም በእነዚህ ሶስት መንገዶች መፈጸም ትችላለህ፡
ሶስት ጥያቄዎችን መልስ፤ ስለ ቀጣዮቹ ሰባት ቀናት እያሰብክ እነዚህን ጥያቄዎች መልስ፤ የእኔ የግል ሃላፊነቶቼ ምን ምን ናቸው? ቀዳሚ ግቦቼ ምን ምን ናቸው? ምን ያህል ጊዜ አለኝ? ለእነዚህ ጥያቄዎች የምትመልሰው መልስ የጊዜ አሸናሸንህን ይወስነዋል።
• ሳምንትህንም በመቶ ተግባሮች ማጨናነቅ የለብህም፤ ይህም በራሱ ሌላ የአእምሮ ጭንቀት እና ውጥረት ይፈጥራል። እናም በማስተዋል እና በእርጋታ ወደግብህ የሚያደርሱህን ጥቃቅን እና የማያደክሙ ተግባራትን እቅድህ ውስጥ አስገባ፡፡
• መርሃ ግብሮችህን ፕሮግራም አስይዛቸው፡፡ አንዴ ሶስቱን ጥያቄ ከመለስክ በኋላ እንደ አስፈላጊነታቸው ተግባራቶችህን ፕሮግራም አስይዛቸው።
• እቅዶችህ ላይ አዲስ ሃሳቦች ጨምርባቸው:: በየሳምንቱ የሚመጥኑህን እና እቅዴ ብጨምራቸው ግቤን ለመምታት ውስጥ ይረዱኛል የምትላቸውን ሃሳቦች ተቀበላቸው፡፡ አዳዲሶቹን ሃሳቦች ፩) ወዲያው ተግብራቸው ወይም ፪) ለቀጣይ ሳምንታት ፕሮግራም አስይዛቸው።
ይህንን ለማድረግም…
• አሁን ላይ መተግበር የሚቻል ከሆነ፣ ደረጃ በደረጃ የአፈጻጸም ሂደት አውጣለት። በቀላሉ ይህን አደርጋለሁ፣ ማክሰኞ ዘጠኝ ሰዓትም እተገብራለሁ ብለህ እቅድ አውጣ፡፡
• ሃሳቡ አሁን ላይ የማይተገበር ከሆነ… ማስታወሻ _ ደብተርህ ላይ ጻፈው እና ለመተግበር አመቺ ጊዜ ስታገኝ እቅድህ ውስጥ አካተው።
የሳምንት እቅድ ክለሳህ ግብህን ለመምታት እጅግ ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡ በየሳምንቱ ስታቅድ አስቸኳይ እና መፈጸም ያለበት እንደሆነ ታስባለህ፤ _ እናም ግብህን ባቀድከው ጊዜ ለመምታት ያስችልሃል።
መንገድ 4
ግቦችህን ወደ ተግባር ለውጥ
ያለተግባር ግብ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ግብህን ተግባር ላይ ለማዋል፣ ለእሱ ተብሎ የተዘጋጀ የብቻው ፕሮግራም ቢኖርህ ይመረጣል፡፡ ቀጣዮቹ መንገዶችም እቅድህን ለመተግበር ያስችሉሃል፡
• እቅዶችህን ከመጨረሻው ጀምረህ ወደኋላ ግለጻቸው። ልክ ___ ግብህን እንደመታህ አስበህ ከመጨረሻው ቀን ተነስ፤ እናም እቅድህን ወደጀመርክበት ቀን እስክትደርስ ተመለስ፡፡ ወደ መጨረሻው የግብህ ቀን ለመድረስ ምን ማድረግ አለብህ? የሚያስፈልጉህን ነገሮች እየዘረዘርክ ወደኋላ ተመለስ፡፡
• መርሃ-ግብሮችህ የሚያስፈልጋቸውን ጊዜ መድብላቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ተግባራቶችህ ምን ያህል ጊዜ ያስፈልግሃል?
• ከቻልክ የግብ ተግባራቶችህን በቀን - በምትሆንባቸው ሰዓታት አድርጋቸው፡፡ ብታደርጋቸው ይመረጣል።

መንገድ 5 ግቦችህን ከልስ
በሕይወትህ ላይ ምንም ነገር እንዲሳካልህ ከፈለግክ ቀጣይነት ያለው እቅድ ያስፈልግሃል፡፡ ለዛም ነው ግቦችህን ደጋግመህ መከለስ ያለብህ፡፡ እያንዳንዱ እቅድ እንዴት እየሄደ እንዳለ መገምገም አለብህ። ግምገማ የምታካሄድባቸውን ነጥቦች አዘጋጅ፤ ከነጥቦቹም አንጻር እቅዶችህ የት እንደደረሱ መዝናቸው፡፡ ከቻልክ ከዚህ በፊት እንዳየነው በየሳምንቱ ግምገማህን አካሂድ።በየቀኑም ጥልቅ ያልሆነ ግምገማ ክንውኖችን አካሂድ፡፡ ምንም ያህል እንኳ ቀንህ ቢጨናነቅ፣ የቀን ውሎህን በዳሰሳ ሳትቃኘው አትለፍ፡፡ በየዕለቱ ምን ላይ እንደደረስክ ማወቅህ ለግብህ መሳካት ታላቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡
እውነታው፣ አንዳንዴ ሕይወት ከምንሮጥበት መም (መሮጫ) ላይ አሽቀንጥራ ታስወጣናለች፡፡ እያንዳንዷን እርምጃችንን መም ውስጥ ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ይሄም ሁኔታ ግቤን ላልመታ እችላለሁ የሚል ስጋት ውስጥ ሊያስገባን ይችላል፡፡ እናም የእኛ ምክር የሚሆነው ይሄ ነው፡- በቀን ከሶስት እስከ አራት ጊዜ እቅዶችህን ቃኛቸው፡፡ እቅዶችህን ደጋግመህ ባየሃቸው ቁጥር ለጭንቅላትህ ትውስታን ትፈጥርለታለህ፡፡ ከምትሮጥበትም ወይንም ብትወጣም ቶሎ እንድትመለስ ይረዳሃል።
መንገድ 6
የሩብ አመት ግብህን ገምግም በየቀኑ ግቦችህን ለማሳካት ትጥራለህ:: እንደውም በየቀኑ እና በየሳምንቱ ትከልሳቸዋለህ፡፡ ችግሩ ምን መሰለህ? ግቦችህ ላይ ለመድረስ የምትሄድበትን መንገድ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻ ግብህንም መከለስ አለብህ፡፡ (መኪና ለመግዛት ገንዘብህን በእቅድ ከመቆጠብህ በተጨማሪ፣ መኪና ለምን መግዛት እንዳለብህ መገምገም አለብህ) ሁሌም ቢሆን በየሶስት ወሩ የምታቅዳቸውን ግቦችን ለምን ብለህ ጠይቅ፡፡ ለምን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከሌለህ ግብህን መምታት ምንም ጥቅም የለውም። ስለሆነም የሶስት ወር እቅድህን መጨረሻ ላይ ግምገማ ለማካሄድ ራስህን እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቀው፤
• የፈለግከውን ግብ መታህ?
• እዚህ ለመድረስ ከተጠቀምካቸው መንገዶች ምን አይነት መንገዶች ስኬታማ ነበሩ? ምን አይነት መንገዶችስ ስኬታማ አልነበሩም?
• እነዚህን ግቦች ለማሳካት 100% ኃይልህን ተጠቅመሃል? ካልሆነ ለምን?
• ከጥረትህ አንጻር የሚገባህን ስኬት አግኝተሃል?
• ለቀጣይ መንፈቅስ ተመሳሳይ ግቦችን ለማቀድ አስበሃል?
• ምን አይነት ግቦችን መቀየር ወይም ሙሉ ለሙሉ መተው አለብህ?
• አዳዲስ ግቦችንስ ማቀድ ትፈልጋለህ?
ይህንን መጠይቅ ለማካሄድ ሰዓታትንም ቢፈጅብህም የግዴታ በየሩብ አመቱ ማካሄድ አለብህ፡፡ ይሄ መጠይቅ በየሶስቱ ወሩ ለከፋፈልካቸው የረዥም ጊዜ እቅዶችህ መሳካት ዋስትና ይሆንሃል እናም የ S.M.A.R.T ጎል መንደፊያ መንገድ አጭር መግቢያ ብቻ ነው፡፡ አንተ በራስህ አስፍተህ እና ይሆነኛል ይመቸኛል በምትለው እና ካለህበት ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መን እቅድህን ንደፍ፡፡ በቀጣይም እቅዶች እንዴት እንደሚታቀ በምሳሌዎች እናያለን፡፡t.me/Lifestyle... #Lifestyleethiopia #አስተያየት_ካሎት251977333377ይደውሉልን #Ethiopia #AddisAbaba

Опубликовано:

 

28 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 19   
@asmaomar4820
@asmaomar4820 2 года назад
የኛ ጀግና እንኳን ደህና መጣህ
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን🙏
@ZedoVlogs
@ZedoVlogs 2 года назад
Owww በጉጉት ስጠብቅ ነበር ፍርየ
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
በርታ zedo🙏❤
@ZedoVlogs
@ZedoVlogs 2 года назад
@@lifestyleethiopia ፍርሀታችሁን ተጋፈጡ የሚለው Class Change My life Thank you☺
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
@@ZedoVlogs በርታ zedo ከቻል ከቀን አንድ ጀምሮ በማስተዋል አድምጠው ጥያቄ ካለህ ቴሊግራም ላይ አለን 🙏
@enewaenewaenewa6885
@enewaenewaenewa6885 2 года назад
ሰላም ለናንተ ይሁን ምርጦቻችን እንኳን በሰላም መጣችሁንል እንኳን አደረሳችሁ ለአዲሱ አመት ሰላማችሁ ይብዛ ምስጋናየ ከልቤ ነው ።ምስጋናየ ይድረሳችሁ ኑሩልን የሀገራችን ኩራቶች።።።።።።።።።።።።።
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን🙏
@roriroei5057
@roriroei5057 Год назад
እናመሰግናለን
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia Год назад
Thanks for watching
@ድንቁዋሴት
@ድንቁዋሴት 2 года назад
Btam inamsginaln 🙏 yikirta antn bgil mawarat flge nber?? Amsginalhu
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤( ቴሊግራም ቻናል ላይ Lifestyle Ethiopia ብለሽ ግቢ )
@efratadaniel9704
@efratadaniel9704 2 года назад
Amesegnalehu frye kef bel ybzalh wendmie
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን❤🙏
@safinalharthi6197
@safinalharthi6197 2 года назад
እናማሰግናለን
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
እናመሠግናለን ❤❤
@hanunahanuali5508
@hanunahanuali5508 2 года назад
Thank you Frye 🙏🙏
@lifestyleethiopia
@lifestyleethiopia 2 года назад
My pleasure!
@aynalemdetamo9957
@aynalemdetamo9957 2 года назад
ተባረክ
Далее
Новый вид животных Supertype
00:59
Просмотров 176 тыс.
FATAL CHASE 😳 😳
00:19
Просмотров 1,1 млн
በ 21 ቀን ራስን መቀየር
20:26
Просмотров 995 тыс.
ራስን እስከመጨረሻው መቀየር
17:38
Просмотров 284 тыс.