Тёмный

🔆 የጻድቅ ሰው ሥራ 🔆 መዝሙር በልጆቻችን 🔆  

ልጆቻችን Lejochachen
Подписаться 20 тыс.
Просмотров 20 тыс.
50% 1

🟨 ይህ መዝሙር ለልጆቻችን 6ቱ ቃላተ ወንጌልን ለማስጠናት በእጅጉ ያግዘናል።
🟨 እነዚህ ቃላት በትንሣኤ ዘጉባዔ በፍርድ ቀን በጌታችን ፊት የምንጠየቃቸው እንደሆኑ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 25 ከቁጥር 31 እስከ ፍጻሜው ተመዝግቦልናል። ይህንንም መጽሐፉን ገልጣችሁ በጋራ አንብቡት።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓመት 2 ጊዜ በደብረዘይት (እኩለ ጾም) እና በጳጉሜን ስለዚህች ዕለት አብዝታ ታስተምራለች።
🟨 በመጨረሻው ሰዓት የታዘዝነውን ፈጽመን፣ ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን ብርሃን ለብሰው በቀኙ ከሚቆሙት እንዲያደርገን ልጆቻችንንም ነጭ ለብሰው አመስግነዋል።
🟨 ልብ አድርጉ! 6ቱ ቃላተ ወንጌልና 6ቱ ሕግጋተ ወንጌል ይለያያሉ።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ብቻ መሥራት (በሥራ ብቻ) መጽደቅ ይቻላል ብላ አታስተምርም።
🟨 እነዚህ በጽድቅ መንገድ ለመጓዝ ግን ያግዛሉ። ለመጽደቅ ግን እምነትን ከምግባር አስተባብሮ መያዝ እንደሚገባ ልጆቻችንን ማስተማር እንዳትረሱ።
የመዝሙሩ ግጥም
የጻድቅ ሰው ሥራ (የጽድቅ ሥራ፣ የጻድቅ ሥራ)
የተራቡትን ብንመግብ የተጠሙትን ብናጠጣ
እንግዶችንም ብንቀበል ለታረዙት ልብስ ብናወጣ
እስረኞችን ብንጎበኝ ሕሙማንን ብንጠይቅ
ይኼ ነው የሚያሰኘን በጌታችን ፊት ጻድቅ
በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ እረኛው
ገበሬውም በመንሹ እንክርዳዱን ከስንዴው
ጻድቅን ከኀጥኡ ጌታም ሲለይ በፍርዱ
በቀኙ እንዲያቆመን እንሒድ በመንገዱ
የተራቡትን ...
አምላካችን ሲመጣ በክብር ሲገለጥ
ለሁሉም እንደሥራው ክፍያውን ሲሰጥ
ያዘዘንን ፈፅመን ቢያገኘን በዕለቱ
በሉ ግቡ ይለናል ወደ ሰማይ መንግሥቱ
የተራቡትን ...
እጆቻችን ይዘርጉ ቤታችንም ይከፈት
እግሮቻችን ይሒዱ በረከት ወዳለበት
ከታናናሾች ለአንዱ ራርቶ ለሚያደርግ ሰው
ጌታችን ይቆጥረዋል ለእርሱ እንዳደረገው
የተራቡትን ...
#መዝሙር #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #songs #አብረንእናሳድጋቸው #ተዋሕዶ #orthodox #youtubevideo #ethiopianyoutubers

Опубликовано:

 

4 апр 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
Мама ударила дочь #shorts #iribaby
00:17
I need your help..
00:28
Просмотров 4,5 млн
Ade, kleines Schweinchen | Janoschs Traumstunde
16:09
Мама ударила дочь #shorts #iribaby
00:17