Тёмный

#ሕልመ 

ላሜድ ሚዲያ / Lamed Media
Подписаться 720
Просмотров 3,3 тыс.
50% 1

#ሕልመ~ሌሊት
👉ምንድነው?
👉መቼ ይከሰታል?
👉 ኃጢአት ነው ወይ
#የወጣቶች_ሕይወት (ሕይወተ ወራዙት)
#ሕልመ_ለሊት_መፍትሄ_አለው ?
ብዙ ሰዎች ተግቶ ለመፀለይ ፣ ለማስቀደስና ለመቁረብ በወሰኑ ጊዜ ሕልመ ለሊት እንቅፋት እየሆነ ይፈተኑበታል። በእርግጥ መብላትና መጠጣት ሳያቆሙ ሙሉ ለሙሉ ከሕልመ ለሊት መለየት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገር አይደለም ። ስለዚህ መፍትሄዎችን እናያለን
#ሀ በመፅሐፈ መነኮሳት ላይ"በሌሊት በሕልም ከሴት ጋር የተገናኘህ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት አታስባት " ይላል ። ሕልምህን ደስ እያለህ ብታስባት ግን በተግባር ዝሙትን ወደ መፈፀም ያደርስሃል። ስለዚህ ከሕልመ ለሊት ፈተና ለመዳን አንዱ መፍትሔ ሕልምን በውን ደስ እየተሰኙ መላልሶ አለማሰብ ነው
#ለ ሕልመ ለሊት በምታይበት ጊዜ ከነቃህ ቸል ብለህ ተመልሰህ አትተኛ ። ፈጥነህ ተነሳና ተጣጥበህ ጸሎት አድርስ ። ከተቻለህ ስገድ ባይቻልህ ግን የባሕሪህን ድካም ፈጣሪ ያውቀዋልና ይቅር በለኝ ፣ አድነኝ ፣ እያልህ ወደ እግዚአብሔር ለምን
#ሐ ሌላው ከሕልመ ለሊት ለመዳን ዋነኛው መፍትሔ ውኀ በብዛት አለመጠጣት ነው ። መፅሐፈ መነኮሳትም ይሄን ሲመሰክር " እንደ ውኀ ጥም አካልን የሚያደርቅ ፣ከሕልመ ሌሊትና ከዘር መፍሰስ ፣ በቀን ሐጢአት ማሰብን የሚያጠፋ የለም " ይላል ። አንድ ሰው ምንም በጾም አመጋገቡን ቢቀንስ አብዝቶ ውኃ የሚጠጣ ከሆነ አይጠቀምም። ለምን ቢባል ሰውነቱ ስለሚለመልምና ሰይጣን እርሱን ለማሳት መንገድ ስለሚያገኝ ነው ። ስለዚህ ከሕልመ ሌሊት እፎይ ለማለት ከፈለክ "ውኃን ከልክለህ ሰውነትህን አስጨንቀው " ተብለሀል። ወንጌልም ይህን ሲያጠነክር እንዲህ ይለናል ፦ "ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ፤ አያገኝምም ። በዚያን ጊዜ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል ፣ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎ አጊጦ ያገኘዋል " (ማቴ 12-43) ይህ ጥቅስ ብዙ ትርጉሞች ቢኖሩትም ከያዝነው ሃሳብ ጋር የሚዛመደውን ብቻ እንይ ፡" ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውሃ በሌለበት ቦታ ያልፋል ። ማለት ሰይጣን መግቢያ ካገኘው ብሎ ሰውነቱን በረሃብና በጥም ወደሚያስጨንቅ ሰው ይሄዳል ማለት ነው ። ይልቁንም "ውሃ በሌለበት" ማለቱን መዘንጋት የለብንም ።"አያገኝምም "የሚለው ቃል ደሞ ሰይጣን ሰውነቱን በውሃ ጥም (በፆም) በሚያስጨንቅ ሰው ላይ ለማደር አለመቻሉን ያሳያል ።
#መ በሕልመ ለሊት በተደጋጋሚ እንዳትጠቃ ወደ ዝሙት ከሚያመራ ማናቸውም ነገር ሽሽ። በመሸ ጊዜ የምታያቸውን ፊልሞች ፣ ንባቦች ፣ ሌሎችንም ነገሮች በጥንቃቄ መርምረህ ለፍትወት የሚያጋልጡትን ሽሽ።ከዚያ ይልቅ ደጋግ መንፈሳዊ መፅሐፍትን ለማንበብ ትጋ ።
#ሠ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ከመንፈሳዊ መምህራንና ከአበው ካህናት ጋር እየተመካከሩ በሚያቀርቡት የመፍትሄ ሀሳብ መጓዝ ነው ። እዚህ ላይ ልንጠነቀቅ የሚገባን የምናማክረው ሰው ምስጢራችንን ለመጠበቅ የታመነና በምንነግረውም ነገር ራሱ ወደ ፈተና ሊገባ የማይችል በሕይወቱ ብዙ ተሞክሮ ያለው መሆን አለበት ። እንዲሁም ጥሩ መፍትሄ አለን ፡ ልፋፈ ፅድቅ እንደግማለን እያሉ ከሚያጭበረብሩ ተኩላ ባህታውያንም መጠንቀቅ
አለብን::

Опубликовано:

 

12 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 16   
@user-ce2jq4eb5i
@user-ce2jq4eb5i 5 месяцев назад
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ❤❤❤❤
@zeyedemekasha3841
@zeyedemekasha3841 2 года назад
Well done
@mahemeti3316
@mahemeti3316 2 года назад
ወቅታዊ መልእክትና እውቀት አከል ነው በርቱ
@tarikubeyene4999
@tarikubeyene4999 2 года назад
ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድሞቼ በርቱልን
@samuelamsir9
@samuelamsir9 2 года назад
በጣም ደስ ይላል እንዳታቋርጡብን በርቱ ወንድሞቼ
@biniyamsemegn2355
@biniyamsemegn2355 2 года назад
Egzabher yesetegele
@tesfishnarratives
@tesfishnarratives 2 года назад
ቃለ ህይወትን ያሰማልን ወንድሞች
@haile1236
@haile1236 2 года назад
ቃለ ሂወት ያሠማልን 🙏 ብልጭልጭ ነገር ወጣቱን እያታለለ ባለበት ወቅት ላሜድ ጥሩ ጅማሬ ነው። እባካችሁ ቀጥሉበት🙏 ለ እንደኔ አይነቱ በሀይማኖቱ መጠንከር እየፈለገ አለም ለምትጎትተው ሰው ጥሩ መነቃቃትን ይፈጥራል። please ዘኦርቶዶክስአዊ መጽሀፍትን recommend አድርገኝ 🙏
@lamedmedia5548
@lamedmedia5548 2 года назад
እሺ ቤተሰባችን አብረን እንበርታ ለማንኛውም የሐሳብ ልውውጥ የቴሌግራም አድራሻችን @Leykuna1 @Fekremike ላይ መገናኘት እንችላለን። እግዚአብሔር ያክብርልን።
@zenbiltv
@zenbiltv 2 года назад
ሰላም የላሜድ አዘጋጆች እንኩዋን በደና መጣችሁ ጥሩ አቀራረብና አዘገጃጀት እደምታደርጉበት ዝግጅታችሁ ያሳያል ጥሩ የሆኑ ስራዎችን ይዛችሁ እንደምትመጡ እምነቴነው በርቱልኝ
@lamedmedia5548
@lamedmedia5548 2 года назад
እናመሠግናለን ። ከፈጣሪ ጋር የተሻለ ስራ አብረን እንሰራለን
@SuperMan-co5pp
@SuperMan-co5pp 2 года назад
Amazing preparation....part 2 yefetenelin
@lamedmedia5548
@lamedmedia5548 2 года назад
እናመሰግናለን ።part 2 አርብ ይለቀቃል
@gelilatsegaye3718
@gelilatsegaye3718 2 года назад
Part 2
@lamedmedia5548
@lamedmedia5548 2 года назад
በቅርቡ ይለቀቃል ቤተሰባችን
@bereketbiz
@bereketbiz Год назад
ህልመ ሌሊትን የሚያመጣው አይነ ጥላ ነው።
Далее
ሕልመ ሌሊት ክፍል ሁለት#Part 2
21:23
Просмотров 1,9 тыс.
Аушев, Путин, «пощечина»
00:56
Просмотров 675 тыс.
ህልመ ለሊት
14:19
Просмотров 56 тыс.
#ኣዋጅ#ባሕረ#ሓሳብ#2017#
43:44
Просмотров 1,9 тыс.
Аушев, Путин, «пощечина»
00:56
Просмотров 675 тыс.