Тёмный

ሴት ልጅ  

Abyssinia አቢሲኒያ  3000
Подписаться 1,3 тыс.
Просмотров 7 тыс.
50% 1

_ሴት ልጅ የፈጣሪ ስጦታ ናት
_ሴት ልጅ አራት ሰው ናት?
1. እናት ትሆንሀለች
2. እህት ትሆንሀለች
3. ፍቅረኛ (የትዳር አጋር ትሆንሀለች)
4. ልጅህ ትሆንሀለች፤ ነገር ግን አንዷ ሴት 13
ገፅታ (መገለጫ) አላት
1. ስትመክር አባት ትመስላለች
2. ስታለቅስ እናት ትመስላለች
3. ስትደነግጥልህ እህት ትመስላለች
4. ስትረዳህ ወንድም ትመስላለች
5. ቤት ስታሳምር የቤቱ ብርሃን ትመስላለች
6. ቤት ውስጥ ስትቆም ምሶሶ ትመስላለች
7. ውጭ ሆና ስትናገር ጎረቤት ትመስላለች
8. ስትላክህ ልጅህን ትመስላለች
9. ምግብ አብስላ ስትሰጥህ እና አብራህ ስትተኛ
ባለቤትህ ትመስላለች
10. ስታስደስትህ ፍቅረኛ ትመስላለች
11. ስትደባብስህ ዶክተር ትመስላለች
12. ፈቷን ስትመለከት መስታወት ትመስላለች
13. ልጅ ስትወልድልህ
ወገንህ እና ደምህ ትሆናለች፤
ይሄን ሁሉ ሴት የፈጣሪ ስጦታ ስለሆነች ነው!
መካከል
ሴት😍
አብዛኛው የማህበረሰባችን ክፍል ሴትን ልጅ ቆንጆ ብቻ እንድትሆን አድርጎ ያሳድጋታል። በቁንጅናዋ ወይንም በዉጪው የሰውነት ክፍሏ ውበት ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደምትችል እያሰበች ታድጋለች።
ቆንጆ ነሽ አንድ ሀብታም ባል አታጪም፣ ቆንጆ ነሽ የሆነ ቢሮ ውስጥ የሆነ ቦታ አታጪም፣ ቆንጆ ነሽ ፊልም ሰርተሽ ታዋቂ ትሆኛለሽ ይላታል....ውበቷን የአይን ግብአት ብቻ አድርጋ እንድትጠቀመው ትደረጋለች በቀጥታም በተዘዋዋሪም ስለ ቁንጅናዋ ይነገራታል።
የኔ እህት ቁንጅና ብቻውን ደስ አይልም!
ቆንጆ ከመሆን ውጪ ብዙ መሆን አለ። ጠንካራ ሴት፣ በራሷ ገንዘብ መስራት መቻል፣ ክብሯን ለሚነካ ነገር እምቢ ማለት፣ ያወቀች የተማረች የበቃች ሴት መሆን።
~ ሴት ልጅ ስትወልዱና የጉራጊኛ ስያሜ ለሴት ልጃችሁ ስም ስትሰይሙ በተብራራ መልኩ የሴት ልጃችሁ ስያሜ ስማቸውን አውቃችሁ አሳውቁ!!
- ትኔላ ስመኝ ስጏጏ ስፈልግ ያገኘኃት ስጦታዬ ምኞቴ
- ሔኒ የሚጠቅምሽን ነገር ሁሉ ለይተሽ እወቂልኝ
- ሶያ ተፈላጋ በፈጣሪ ፍቃድ የተገኘችልኝ
- ቤቲ የሚጠቅምሽና የሚጎዳሽን ነገር ሁሉ ለይተሽ እወቂ
- ዮሪ ይህንን ሁሉ የውጣ ውረድ የመከራ የችግር መንገድ የተኬደው የተለፋው የኔ ልጅ ላንቺው ነው ባንቺ መገኘትና መለገስ! በፈጣሪም ስጦታ ለእኔ ባንቺ መሰጠት ሐሴት ለማድረግም ነው!!
- ሐና ፈጣሪ ሆይ አንተ የሰጠኸን ስጦታ ናትና አንተው እወቃት
- ቲና መልካም ነገር ሁሉ ከእኛ ጋር ይሁን
- ትኔላ ስመኛት ስፈልጋት ስጏጏላት ያገኘኃት ድንቅ ልጄ
- ሉኸና ነብሴ ሁሉ ነገሬ
- ኑናና የእኔ ልዩ የእኔ ድንቅ
- ሶያ የእኔ ልጅ ልዩ ናት እናንተም የእሷን አመሳያ ካሻችሁ በፀሎት ፈልጏት
- ቴም ሁሌም እንደ ወለላ ማር ጣፍጭልኝ
- ሽፗቸና ልጄ እኮ የእኔ ምርጥ ምርጫዬ ናት
- ቲያና ከአካል እስትንፋሴ ከእኔ ደምና ስጋ ውህድ ፈጣሪ አምሳስሎ የፈጠረልኝ
ካልበቃ እጨምራለሁ .....!!
🌿💖 ልደታ ለማርያም ማለት⛪🌿💖
🌿💖 ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር:
🌿💖 እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን:
🌿💖 አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት:
🌿💖 እርሱዋም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው::
🌿💖 እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው:
🌿💖 እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:
🌿💖 ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች::
🌿💖 ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት::
🌿💖 እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ:
🌿💖 ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች:
🌿💖 እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች:
🌿💖 እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ::
ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው:
⤴ 🌿💖 ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት:
🌿💖 ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::
🌿💖 ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው::
🌿💖 እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ:
🌿💖 ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ

Опубликовано:

 

22 май 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 8   
@Melkageremew-qs5pm
@Melkageremew-qs5pm Месяц назад
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
@TdfggfghFgffhgdketj
@TdfggfghFgffhgdketj День назад
❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@kalkal-hk3cf
@kalkal-hk3cf 19 дней назад
አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን
@Melkageremew-qs5pm
@Melkageremew-qs5pm Месяц назад
Ammenne❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤💘
Далее
Never waste PASTA SAUCE @itsQCP
00:19
Просмотров 4,3 млн
Never waste PASTA SAUCE @itsQCP
00:19
Просмотров 4,3 млн