Тёмный
No video :(

ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር ክፍል - 2 / Kidus Aba Yohannes Hatsir Part - 2 

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Подписаться 174 тыс.
Просмотров 217 тыс.
50% 1

ይህን መንፈሳዊ ፊልም አዘጋጅተው ላቀረቡልን ሁሉ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
+" ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር "+
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም "ዮሐንስ ሐጺር - አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል::
+ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::
+ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር::
+ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::
+አባ ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::
+አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል::
+ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው::
+ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ::
+በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም::
+ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
+መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
+መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
+አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ (ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ::
+"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል::
+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
+በ825 ዓ/ም ግን በአባ ዮሐንስ ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል::
+ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን የፌስቡክ ገጽ
/ %e1%8b%9d%e1%8a%ad%e1%...

Опубликовано:

 

29 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 634   
@user-ef4fw6mt3h
@user-ef4fw6mt3h Месяц назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረደት በረከት ምልጃና ፀሎታችው አይለየን
@Hrhg-sq2vs
@Hrhg-sq2vs Месяц назад
የአባታችን የቅድሱ ዮሐንስ እረደኤት በረከት አይለየን አሜን አሜን አሜን ❤❤❤
@fatmaman2519
@fatmaman2519 4 месяца назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን እረዴኤት በረከታቸው አይለየን🙏🙏🙏😢😢😢😢❤️❤️❤️❤️
@Ggg-vs1iy
@Ggg-vs1iy 2 месяца назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረደት በረከት መልጃና ፀሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን😢😢💚💚💛💛❤❤⛪👏🙏
@kokobeworku1232
@kokobeworku1232 День назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ ሀጺር ረድኤት በረከት ይደርብን❤
@user-me3ld7eu6l
@user-me3ld7eu6l 9 дней назад
የአባታችን ቅዱስ ዮሐንስ በረከታቸው ይድረሰን ብዙ ተምረንበታል አቤቱ ትህትናና ትእግስታቸው
@geneteshetu-iz1lm
@geneteshetu-iz1lm Месяц назад
የአባታችን የአባ ይኋኒስ በረከት ይደርብን
@mekdi9983
@mekdi9983 Год назад
አባቴ ቅዱስ ዮሀንስ አፂር በረከተህ ምልጃህ አይለኝ በረከትህ በእውነት ይሁን ይደረግልን
@user-vx7vc8fq9y
@user-vx7vc8fq9y 2 месяца назад
አሜን ያባታችን ዩሃንስ ሀፂር በረከት ይደርብን
@user-bd1rt3hd1g
@user-bd1rt3hd1g 4 года назад
የቅዱስ ዮሐንስ አባታችን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን
@Lena-bw6ml
@Lena-bw6ml 4 года назад
አሜን፣አሜን፣የአባታችን፣አባይዃንስ፣በረከታቸዉይደርብንአሜንንንንን፣የአባቶቻችንአምላክ፣ልኡልእግዚአቤር፣ለዘላለምየተመሰገነይሁንአሜን
@AliSaleh-kb1hg
@AliSaleh-kb1hg 4 года назад
የቅድሰ አባ ዮሐንስ በረከት ያደሪብን አሜን አሜን አሜን እደዝ አያነት ምህረት ምነኛ መታደል ነው አምላክ ሆይ አደዝ ምረትሂን ላክልን አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን 💒💒🙏🙏
@teduadaayal2841
@teduadaayal2841 3 года назад
የአባታችን ቅዱስ የኋኒስ በረከት ይደርብን🙏🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
@hanagosaye4686
@hanagosaye4686 2 года назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሀንስ በረከት ረድኤት ይደርብን 🙏🙏🙏
@ahmelahmel1485
@ahmelahmel1485 4 года назад
የአባታችን የቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር እረድኤት በረከት አይለየን አሜን አሜን አሜን
@hanichoyemariyamliji8102
@hanichoyemariyamliji8102 4 года назад
አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን ለቅድሳን አባቶች በርከት ይድረስን
@SamsungA-om7vz
@SamsungA-om7vz 8 месяцев назад
የቅዱሣን አምላክ ልኡል እግዚያብሔር ይመሥገን የቅዱሣኑ በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን❤❤❤
@hanagosaye8136
@hanagosaye8136 3 года назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሀንስ በረከት ረድኤት ይደርብን
@kokob5829
@kokob5829 2 года назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ አጺር በረከታቸው ይደርብን
@user-eg3bh6ox9n
@user-eg3bh6ox9n Год назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ ረደት በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@user-vo3pl4zu6y
@user-vo3pl4zu6y 2 месяца назад
የአባታችን የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ረደት በረከት መልጃና ፀሎት አይለየን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏
@habitam
@habitam Год назад
አምላኬ ሆይ ትግስት አድለኝ 🙏🙏🙏ያባቶቻችን እረደት በረከታቸው ይድረስብን 🙏🙏🙏♥♥♥♥
@user-om5or6jj6j
@user-om5or6jj6j 2 года назад
በረከታቹሁ አይለየን ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ፀጥታ ትኑር ተመሠገን 💒💒💒👈❤️❤️❤️
@user-hd4sn2wk3f
@user-hd4sn2wk3f 5 лет назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አለማዊውን ትተን ወደ መንፈሳዊ የሚመራ ልቦና ይሰጠን የቅዱሳን አምላክ ይጠብቀን
@adebabaygoshe5779
@adebabaygoshe5779 5 лет назад
Amen amen amen
@user-kp7bd2wj4c
@user-kp7bd2wj4c 5 лет назад
ያኣባታችን የቅዱሳን የዉሃንስ ፆሎት በረከት ከኛ ጋር ዩሁን
@dabritutefera4938
@dabritutefera4938 4 года назад
በእውነቱ ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በፀፀጋ ያቆይልን አሜን፫ የቅዱሰ አባ ዮሐንሰ አጺር በርከታች እርዴታችው ይድርብን አሜን
@user-lz9wr9uq1o
@user-lz9wr9uq1o Год назад
በረከታቸው ከሁልም ህዝበ ክርስቲያን ይሁን አሜንንን🙏
@saraworku8256
@saraworku8256 5 лет назад
የቅዱሳን አምላክ የእኛም አምላ ኤየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይድረሰው ይቅዱሳኑ ኤረደኤት በረክት በኛላይ ይኑር ለዘላለም አሜንንንንንንንን
@user-ef6qc2wh4t
@user-ef6qc2wh4t 3 года назад
አቤቱ ጌታዬ ሆይ እኔ ሃጥተኛህን ባሪያህ ነኝ አስበኝ
@user-sc6pf7mu4p
@user-sc6pf7mu4p Год назад
አሜን አሜን አሜን የአባታቺን አባዮሕንስ በረከት በሁላቺንምላይ ይደርብን ቃልህይወት ያሰማልን አቤቱ ጌታሆይ እምነትን ጨምርልን
@user-qf2vo6nt8t
@user-qf2vo6nt8t 3 года назад
በእውነት ቃለህይወት ያሰማልን የአባ ዮሐንስ ሐጺር እራድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን አሜን ፫
@barqibarqi4327
@barqibarqi4327 2 года назад
የአባቶቻችን የቅዱሳን ሠማእታት በረከት ይደርብን
@user-tb5qp5fr5w
@user-tb5qp5fr5w 4 года назад
አሜን አባታችን በረከተዎ ታግኘን ይልቁንም ሀጥዕ ወለተ ኢየሱስን
@bataleabrham2671
@bataleabrham2671 4 года назад
የቅዶስ አባ ዬሐንስ ሀጼር በረከታችው ይደርብን አሜን👏
@MmMm-ls9iy
@MmMm-ls9iy 6 месяцев назад
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏💙😢😢
@user-zf3qj9kp8d
@user-zf3qj9kp8d 3 года назад
አሜን አሜን አሜን ፆሎቶምን ረዲአቶምን ምስ ኩላትና ህዝበ ክርስትያን ይኩን አሜን አሜን አሜን
@user-kn9yd8rv3y
@user-kn9yd8rv3y 6 лет назад
የቅዱሳን በረከት ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን
@muluabrha8601
@muluabrha8601 5 лет назад
የቅዱስ አባ ዮሃንስ በረከትና ረዴታቸው አይለየን
@betyabera9644
@betyabera9644 Год назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱስ አባ ዮሐንስ አፂር እረዴት በረከታቸዉ ይደርብን ፀሎታቸዉ ያስምረን አሜን
@senaitgebremedhin7460
@senaitgebremedhin7460 2 года назад
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን (3) ቃለ ሂወት ያሰማልን የጻዲቁ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ ሓጺር በረከታቸው ይደርብን
@egziabherymesgen1481
@egziabherymesgen1481 11 месяцев назад
ኣሜን ቃል ህይወት ያሰማልን የኣባታችን ቅዱስ የውሃንስ በረከት ይደርብን
@hanadigafie6197
@hanadigafie6197 4 года назад
የአባታችን በረከት ረድኤት ፀሎት ልመናቸው ይደርብን
@astatekushima3539
@astatekushima3539 4 года назад
የአባታችን፡የአባ፡ዮሐንስ፡በረከት፡አይለየን፡አሜን።
@titiyoutub6254
@titiyoutub6254 4 года назад
ይንን መንፍሣውዊ ታሪክ የአባች የቅዲሣን ታሪክ እርደት በርከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን አሜን የክርሥትና እምነት ተከታዮች ሁሉ በእመነቱ ያጵናን
@enewaenewaenewa6885
@enewaenewaenewa6885 5 лет назад
ቃለህይወት ያሰማልን የአባታችን እረዴት በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@aberaalemu8209
@aberaalemu8209 Год назад
እግዚአብሔር ይመሰገን ለኛም የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን አሜን🤲🤲🤲
@user-en1gr4ge2h
@user-en1gr4ge2h Год назад
እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደርብን አሜን/፫/
@user-vi2zj9ps9b
@user-vi2zj9ps9b 5 лет назад
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን እግዚአብሄር በቅዱሳን ላይ ስራው ግሩም ነው የቅዱሳን ረድአት በርከት አይለየን አሜን
@user-mt8gf6eh6i
@user-mt8gf6eh6i Год назад
ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን ❤❤❤
@makilu1679
@makilu1679 2 года назад
ስለሁሉ ነገር ለኡል እግዚአብሄር የተመሰገን ይሁን የቅዱሳን አባቶቻችን በረከትና ረዲኤት ይደርብን!!
@kestedemena-qm4uu
@kestedemena-qm4uu 6 месяцев назад
የሕይወት ቃል ያሰማን በእውነት እየንን የአባታችንን ታርክ ገድል አስተርጉማች ለቀረባቹት
@cellmobile1238
@cellmobile1238 3 года назад
ያባታችን የአባ ይሐንስ ፆለት ይደረብን አሜን አሜን አሜን
@user-vj8fm3ev5o
@user-vj8fm3ev5o 4 года назад
አሜን ቅዱስ አባ ዩሀንስ በረከታቸው ይደርብን አይለየን በእውነት ለምታዘጋጁልን እግዚአብሔር ያክብርልን
@xcbh_hi
@xcbh_hi 2 года назад
አሜን አሜን አሜን የአባታቺን በርከቱ ከሁላቺንጋር ይሁን ❤😥🙏🙏🙏🙏
@user-kg3jx5ne9k
@user-kg3jx5ne9k 4 года назад
ክብር ምስጋና ለእግዛብሔር ኣምላክ ይሁን የሀ ትምህርት የምታቀርቡት እግዛብሔር ይባርካቹ ለዘለኣለም ይመስግን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@enyewdegaga3207
@enyewdegaga3207 Год назад
አሜን የቅዱስ አባታችን በረከታቸው ይደርብን 🙏
@gemillamohammad5598
@gemillamohammad5598 4 года назад
አሜን አሜን አሜን የአባታችን ቅድስ ዪሀንስ ረዴቱ አይለየን
@user-sj9ll4rf1d
@user-sj9ll4rf1d 10 месяцев назад
በእውነት ቃለህይወትን ያሰማልን ላሰማችሁ ያባቶችበረከትይደርብን🤲🤲🤲❤
@user-vo4nr5gr7l
@user-vo4nr5gr7l 4 года назад
የቅዱሳን እረደየት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን እናተን ድካማችሁን እግዚአብሔር ይክፈላችሁ ፀጋውን ያብዛላችሁ
@jrresadleedas8876
@jrresadleedas8876 2 месяца назад
በውነቱ የአባታችን ቅዱስ ዮሐንስ በረከታቸው ይደርብን በፀሎታችው አምላከ ቅድስ እግዚአብሔር ይማረን አሜን❤ እዲሁም ፊልሙን ተርጉማችሁ ላቀረባችሁልን የክርስቶስ ቤተሰቤቶ ክበረለልን እናመሰግናለን በርቱ እግዚአብሔር ከናተጋር ይሁን አሜን❤❤❤
@user-om5or6jj6j
@user-om5or6jj6j 2 года назад
የአባቶቻችን በርከት እረዴት ይደርብን አሜን
@muzamuza4351
@muzamuza4351 4 года назад
የአባቱቸንበርክታችውይድርብን፣አሚንአሚንአሚን
@hanaalamu9871
@hanaalamu9871 3 года назад
የቅዱሳን በረከታችዉ ይደርብን አባታችን ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር በረከቱ ይደርብን አቤቱ ሰለቅዱሳን ሰትል እራድን የቅዱሳን አምላክ እኔስ በደለኝ ነኝ አቤቱ ኀጤያቴ 😭😭 አቤቱ ቸሩ መድኃኔዓለም ይቅር በለኝ
@rjgdugfbhddjemfbhddjemg1176
እግዚአብሔር ይመሰገን በቅዱሰን ላይ አዴሮ ያሰትምርናን የአብታች ብርክታችው ይድርብን አሜን አሜን አሜን በእውነት
@poptika6979
@poptika6979 3 года назад
ያባቶቻቺን በረከት ከእጋ ጋር የሁን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😘😘😘😘😘😘😘💒💒💒💚💛❤
@user-dx2fy1rh4v
@user-dx2fy1rh4v 3 года назад
የቅድሳን በርከት በኛላይ ይእደርብን አሜን
@fntrggboy19
@fntrggboy19 3 года назад
አሜን የአባታችን የቅድስ ይሆንስ በረከት በኛ ላይ ይደር
@tayechmelese4493
@tayechmelese4493 4 года назад
ቅዱስ አበ ዮሐንስ በረቀት ይድርልን አሜን
@BettyEtty
@BettyEtty 6 лет назад
Amen amen amen abatach kdus yohans atsir bereketachew mljachew tselotachew ytebken le anbabiyochm kale hywetn yasemaln yasemaln tesfa mengste semayatn yawarsln amen💒💒💒❤
@user-vu1sc3oy7v
@user-vu1sc3oy7v 2 года назад
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አይይ የኔሳ እምነቴ ሙሉ እሚሆነው መቸ ይሁን አምላኬ ሆይ እርዳኝ እኔስ ደካማ ሁኛለሁ
@alenezayda
@alenezayda 4 года назад
አሜን አሜን አሜን ያባታችን ቅዱስ ዬሀንስ በረከት ይደርብን
@lklkblklk1144
@lklkblklk1144 6 лет назад
amen yekdusan abatochachin bereket ayileyeng abat hoy እኔን የማልጠቅም ባርያህን በቅድስናው ተራራ እምላለስ ዘንድ እርዳኝ አሜን
@DigafeAsigelil-pt6ie
@DigafeAsigelil-pt6ie 10 месяцев назад
አሜን ምልጃና ፀሎታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን !!!
@user-rt6tz2qi4w
@user-rt6tz2qi4w 4 года назад
አሜን አሜን አሜን ያባታችን በረከት ከሁላችን ላይ ይደር
@user-cr5cu2my8c
@user-cr5cu2my8c 4 года назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱስ አባታችን በረከት ይደርብን
@user-bi1nx1wr3y
@user-bi1nx1wr3y 5 лет назад
አሜን አሜን አሜን የአባቱቻቺ በረከት አይለይን በእወነት የዚህን በረከተ ተካፋይ እንዲንሆን ያደረጋቺሁ ቤተሰብቸ ቃለ ሂወት ያሰማልንንንን
@user-me2zc5ep8l
@user-me2zc5ep8l 3 года назад
ቅዱሣን አባቶቻችን በረከታችሁ ይደረብን ላቀረባችሁልን ቃለህይወት ያሠማልን
@adebabaygoshe5779
@adebabaygoshe5779 5 лет назад
Amen Amen Amen yekidus yehanis emnetachew ena berektachew yderbin amen amen amen
@melonatesfaye4057
@melonatesfaye4057 2 года назад
አሜን በረከታቸው ይደርብን ላቀረብከልንም ቃለ ህይወት ያሰማልን
@user-nt3gt4cz7f
@user-nt3gt4cz7f 9 месяцев назад
አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን በረከታቸው አይለየን ተርጉማችሁ እኛ በምነታችን እንድንፀና ላደርጋችሁን አባት እናቶች እህት ወንድሞቻችን በእግዚያብሔር ስም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏❤❤❤
@senaittsegay6335
@senaittsegay6335 6 лет назад
Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen
@molomulu.tesefaye6112
@molomulu.tesefaye6112 4 года назад
AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲 AMEN 🤲🤲
@primepkus4390
@primepkus4390 4 года назад
አሜንንንን ቃለህይወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን
@user-zy9kg5nd6f
@user-zy9kg5nd6f 6 лет назад
ጌታዬክብርእናምስጋናላንተይሁንአሜን
@genzebeegirmaa2874
@genzebeegirmaa2874 4 года назад
አቤቱ አባቴ ሆይ እጅግ አፅይተኝ ልጂክ ነኝ እናም ይቂር በለኝ ረዴት በረከታችሁ አይለየኝ
@brtukanleake1591
@brtukanleake1591 Год назад
ቃል ሂዎት ያሰማልን እግዚአብሄር ያከብራቹ✝️⛪️✝️❤❤❤
@kodiyishukoor3584
@kodiyishukoor3584 10 месяцев назад
ቃለህይወት ያሰማልን እናመሰግናለን ለተረጎማችሁልንም ፀጋውን ያብዛላችሁ❤❤
@ayuamanu6229
@ayuamanu6229 4 года назад
Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen
@MuMu-ls4fx
@MuMu-ls4fx 10 месяцев назад
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏
@user-rv7ol5ih7e
@user-rv7ol5ih7e 5 лет назад
የቅዱሳን በረክታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@haleluyatube19
@haleluyatube19 6 лет назад
አሜን የአባታችን ረድኤት በረከት ይደርብን
@meronmeron1294
@meronmeron1294 5 лет назад
Amen Amen yaqdusanan abatoch barkat yidarben Amen
@elsabettube3582
@elsabettube3582 6 лет назад
Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen Amen kalehiwot yasemalin Egzabere beidme betna yakoyilin Amen
@fasikameshesha8249
@fasikameshesha8249 6 лет назад
ወንድማችን በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን
@lulatesfay4937
@lulatesfay4937 4 года назад
በረከቶ ይደርብን ለኣዘጋጆች መንግስተ ሰማያት ያድልልን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@user-xj1yi4zd4p
@user-xj1yi4zd4p Год назад
በእውነት ቃለይሆትያሰማልንየአባቶቻችንበረከትይደርብን
@user-xg3tw6uv4z
@user-xg3tw6uv4z 3 года назад
በርከታችሁ ይድርሰን የአባታችን ቅዱሥ ዮሀንስ በርከቱ ይደርብን
@abebabilatu9510
@abebabilatu9510 Год назад
አሜን አሜን አሜን በረከታቸው ይደርብን እግዚአብሔር ይስጥልን
@zulugelseminatkokobzuzugel8527
Amen Amen Amen ye Abetachetachen berakit yederaben Amen Amen Amen
@biskutzele4534
@biskutzele4534 4 года назад
Amen Amen Amen YABATACHIN BERKET ayileyen kalewtin yasemalin
Далее
New Dyna Skin is OP🥵🔥 | Brawl Stars
00:16
Просмотров 566 тыс.
ወንጌል የዉሃንስ
2:06:36
Просмотров 1,2 млн