Тёмный
No video :(

ቅዱስ አባ ጳውሊ ወ አባ እንጦንስ | Antony the Great and St Paul the first Hermit 

የቅዱሳን ታሪክ / Yekidusan Tarik
Подписаться 173 тыс.
Просмотров 366 тыс.
50% 1

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ ††† የካቲት ፪
ምንጭ፡- ዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church (Facebook Page)
††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።
ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።
ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።
ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።
ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።
ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።
እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።
አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ (የመነኮሳት ሁሉ አባት) እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም (የሚበልጥ) ሰው ይኖር ይሆን?"
ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።
"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።
ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት (ዋሻ) በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ (ቆፈቆፈ)። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።
ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።
ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ (በጸጋ አውቆት) "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።
ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣
የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
የመጀመሪያው ባሕታዊ (ገዳማዊ) ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።
ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።
ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ (ጳውሊ) መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።
ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።
በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።
በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። (አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።) ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።
ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።
††† ጻድቅ፣ ቡሩክ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!
††† አባ ለንጊኖስ †††
††† ጻድቁ ከኪልቅያ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ግብጽ ድረስ በተጋድሎ የተጓዙ አባት ናቸው። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም የደብረ ዝጋግ (ግብጽ፤ እስክንድርያ) አበ ምኔት ሆነው አገልግለዋል።
ሙታንን አስነስተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከድንቅ ነገራቸው ሰይጣን የእርሳቸውን የምንኩስና ቆብ ዐይቶ ደንግጦ መሸሹን እንጠቅሳለን።
"ኀበ ኢኀሎከ ሶበ ቆብዓከ ርዕየ
ሰይጣን ተኃፊሮ እፎኑመ ጐየ።" እንዲል።
(አርኬ)
††† አምላክ በበረከታቸው ይባርከን።
የካቲት ፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (የባሕታውያን ሁሉ አባት)
፪.ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት (ደብረ ዝጋግ)
፫.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (የሃይማኖት ጠበቃ)
፬.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ
††† "የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ። ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ። በድንጋይ ተወግረው ሞቱ። ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። ሁሉን እያጡ፣ መከራን እየተቀበሉ፣ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ።" †††
(ዕብ ፲፩፥፴፭-፴፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Опубликовано:

 

28 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 674   
@Ggg-vs1iy
@Ggg-vs1iy 3 месяца назад
አሜን የአባ ጳውሊ የአባ እንጦስ እድሁም አብረው ያሉትም መነኮሳት ረደት በረከት ምልጃና ፀሎት አይለየን አሜን💚💚💚💛💛💛❤❤❤😢😢
@AsefuMeseleui9no
@AsefuMeseleui9no 2 месяца назад
Amen Amen Amen
@senusamrawit9070
@senusamrawit9070 3 года назад
እግዚአብሔር ይመስገን የቅዱሳን የአባቶቻችን ፆሎታቸው በረከታቸው ይደርብን ቃለ ህይወት ያሰማልን እሰይ እሰይ እሰይ እንደ ዛሬ ቀን በጣም ደስ ይላል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሆን እኮራለው
@alemneshalemu1666
@alemneshalemu1666 3 года назад
We
@almaayerga6339
@almaayerga6339 2 года назад
Amen Amen Amen
@abrehamtakel9002
@abrehamtakel9002 Год назад
@@alemneshalemu1666 Ĺp⁰
@zomaasefa5196
@zomaasefa5196 8 месяцев назад
​@@alemneshalemu1666❤
@saabcell8668
@saabcell8668 3 месяца назад
እውነት ነው ቃለህይወትን ያሰማልን 💕🙏💕
@user-vh2sx5kh5s
@user-vh2sx5kh5s 3 года назад
❤""ውይ እንዴት ደስ ይላል የፃድቃን በረከታቸው ይደርብን❤❤❤
@aynalemeshete5491
@aynalemeshete5491 2 года назад
ቃል ህይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን
@user-gq6sf3dk8k
@user-gq6sf3dk8k 2 года назад
አሜን አሜን አሜን
@user-ie3mz9tf6r
@user-ie3mz9tf6r 6 месяцев назад
አሜን አሜን አሜን❤❤
@user-to4ws2pi2h
@user-to4ws2pi2h 4 года назад
የቅዱሳን በረከታቸዉ ይደርብን 🙏🙏🙏
@AZGZ-nh4dk
@AZGZ-nh4dk 3 года назад
አሜንንን።🙏
@makdsm8979
@makdsm8979 3 года назад
Amen Amen Amen
@yabu857
@yabu857 3 года назад
Amen Amen Amen
@samsungsung7412
@samsungsung7412 3 года назад
amen amen
@samsungsung7412
@samsungsung7412 3 года назад
Amen amen amen
@tvfreedomofspeech9358
@tvfreedomofspeech9358 4 года назад
ናይ ኣባ ጳውሊ በረከቶምን ጸሎቶምን ምስ ኩላትና ህዝቤ ክርስታይን ይኩን ሙቁራተይ💞💞💞
@user-nh9bc3xk8i
@user-nh9bc3xk8i 3 года назад
የባቶቻችን በረከታቸዉ ከኛጋር ይሁልን ኣሜን ፫ ቃለሂዉት ያሰማልን
@user-er3ry5hy4u
@user-er3ry5hy4u Год назад
አሜን፫
@deesdoos6676
@deesdoos6676 3 года назад
ስለ ቅዱስ ቃሉ የቃሉ ባሌቤት የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የቅዱስ ጳውሊ በረከት ረድኤት ይደርብን አሜን
@user-cw4co7ct7s
@user-cw4co7ct7s 3 года назад
አሜን ቃለሂወት የስመአና
@user-vz8ov4sv7j
@user-vz8ov4sv7j 2 года назад
በህይወት መንፈሳው ፍልም አይቼ እንደ ዛሬ አልቅሻ አላቅም የአባቶቻችን በረከት አማላድነት አይለየን👏👏👏👏👏
@onelove1703
@onelove1703 Год назад
ግብፃዊዋ ማርያም ብለሽ እይ እሱም ያስተምራል
@adina.6549
@adina.6549 3 года назад
በረከታቸው ይድረሰን😾🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
@letmehaveyourwill1552
@letmehaveyourwill1552 4 года назад
የቅዱሳን በረከት እረዴታቸው በኛ በደካሞች ላይ ይሁን አሜን ፫ የተዋህዶ ልጆች እባካችሁ ተመልከቱ በረከታቸውንም ተካፍሉ ይሄኔ 1ዘፍን ወይ ፊልም ቢሆን ስትሽቀዳደሙ ትገኙ ነበር በእውነት እናሳዝናለን
@abarsheabarshe6538
@abarsheabarshe6538 4 года назад
አሜን፫
@genet1236
@genet1236 4 года назад
እውነት ነው እግዚአብሔር አምላክ ልቦናችንን ይመልስልን ለኛ ለደካሞቹ በረከታቸው ይደርብን
@selamtube7356
@selamtube7356 3 года назад
አሜን አሜን አሜን
@user-mo2so5xu2j
@user-mo2so5xu2j 3 года назад
እውነት ነው እህታችን ቃለ ህይወት ያአሰማልን የቅዱሳን በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደረብብን አሜን እግዚአብሔር ማሰተዋሉን ያአድለን
@AliAli-it6fb
@AliAli-it6fb 3 года назад
እዉነት ነዉ
@witnessam6592
@witnessam6592 3 года назад
የቅዱሳኑ በረከታቸው ይደርብን አሜን ኦርቶዶክስ መሆን መመረጥ ነው ።
@helenhaftom1525
@helenhaftom1525 3 года назад
ቃለ ሂወት ያሰማልን በረከታቸው ይደርብን አባቶቻችን መታደል ነው። 😢😢😢
@rabehcall1332
@rabehcall1332 2 года назад
የቅዱሣን በረከታ ቸው ይደርብን
@FgFh-uj4eu
@FgFh-uj4eu 3 дня назад
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይዎት ያሠማልን አባታችን በረከትሕ ይደርብን🙏🙏🙏⛪️⛪️⛪️🕯🕯🕯:
@sara_mandefro
@sara_mandefro 4 года назад
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከታቸው ይድረሰን 😢😢😢😢
@nolawieyasu4599
@nolawieyasu4599 3 года назад
9+9=
@user-rg4ho5xc8v
@user-rg4ho5xc8v 3 года назад
አሜን፫
@AbdiiDabaluu
@AbdiiDabaluu 17 дней назад
አሜን።የታላቁ አባታችን አባ ጳዉሊ በረከቱ ይደርብን🙏🙏🙏።
@AzmeraTizazu
@AzmeraTizazu Месяц назад
"የጳውሊ አምላክ ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን " እናንተም እግዚያብሄር ይባርካቹ! ሁሌ ስሰማዉ ያረጋጋኛል!!!
@selamjejo2271
@selamjejo2271 3 года назад
አሜን ተመስገን አምላኬ ሆይ እሂን እዳይ ስለፈቀድክልይ ክብር ምስጋና ይግባህ አሜን
@meaziroyal8914
@meaziroyal8914 3 года назад
_የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው እረድኤት አማላጅነታቸው ይደርብን አሜን_
@matiyasalemayew4100
@matiyasalemayew4100 3 года назад
ያባታችን በረከት አይለየን
@musammadmusammad4092
@musammadmusammad4092 3 года назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱሣን በረከት እሰድኤት ይደርብን አሜን
@dinatube6757
@dinatube6757 3 года назад
በእውነት እንደ አባ ጿውሊ መሆን ፈለኩ 😭😭👏👏👏
@astereshetu2926
@astereshetu2926 3 года назад
የቅዱሰንበረክታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@user-xg4hj4eg4y
@user-xg4hj4eg4y 18 дней назад
አሜን አሜን አሜን እግዛቢሄር የተመሰገነ ይሁን የፃዲቅ በረከት ይደርብን❤❤❤
@enewaenewaenewa6885
@enewaenewaenewa6885 3 года назад
የአባቶችን እረዴት በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን።።።።
@user-pf9zb1zc6y
@user-pf9zb1zc6y 3 года назад
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከት አይለየን አሜን
@amaamm4692
@amaamm4692 Год назад
አሜን አሜን አሜን።🤲🤲🤲🙏🙏🙏
@seblieyobawyt990
@seblieyobawyt990 4 года назад
አሜን የባቶቻችን በረከት በሁላችላይ ይደር ❤❤❤🙏🙏🙏
@mekdestessema4611
@mekdestessema4611 4 года назад
Amen amen 🤲🙏🤲🙏
@asafuyared7772
@asafuyared7772 3 года назад
@@mekdestessema4611 አሜን አሜን አሜን
@mulumuluyes1731
@mulumuluyes1731 3 года назад
AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN Ye Kedusanu Eredete Bereketachew Yedereben AMEN AMEN AMEN
@user-cw4co7ct7s
@user-cw4co7ct7s 3 года назад
አሜን ቃለሂወትየስመአና
@user-rr3js3qc1t
@user-rr3js3qc1t 4 года назад
ጌታ ሆይ ተመሰገን እንዳይ ለረዳህኝ።በርከታችሁ ይድርሰኝ ደካማ ነኝ
@user-ef8cz5rl4k
@user-ef8cz5rl4k 3 года назад
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን
@user-rn4zw6sb2m
@user-rn4zw6sb2m 4 года назад
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ሂወት ያሰማልን የ ሁልምቁድሳን ፀሎት እና በረከት ኣይለየን ኣሜን የኣባታችን የኣባ ጳውልይእና እንጦንስ ፀሎት እና በረከት ኣይለየን እኛም በስደት ያለን ልጆችህ ይቅር በለን እናም ለንሳሃ ምት ኣብቃን መዘሙረ ዳውት 119(120) በጨነቀን እና በጠበበን ጊዜ እግዚአብሔር ኣልተለየንም እና የክብር ክብር ምስጋናይግባው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ምልጃሽ እና ፀሎትሽን አይለየን ም እና ክብር ምስግና ይግባሽ መጨረሻችንን ኣሳምርልን ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@ayehutgashaw8953
@ayehutgashaw8953 4 года назад
አሜን ግን ለምንድነው እግዚአብሄር የሚለውን ፊደል ሙሉውን የማንፅፈው እ/ር ማለት ምን ማለት ነው?
@ttigistttigist2200
@ttigistttigist2200 3 года назад
አሜንከሜንአሜንንን
@user-rn4zw6sb2m
@user-rn4zw6sb2m 3 года назад
ኣመስግናለሁ ውድ እህቴ እግዚአብሔር ይጠብቅሽ እግዚአብሔር ማለት ጌታ፣ፍጣርይ፣ገዢ፣የፍጥረት ሁሉ ፍጣሪ፣ እግዚ_አብ_ሔር ጌታ እየሱስ( እግዚአብሔር ወልድ) ፣እግዝኣብሔር ኣብ( ጌታ ኣብ) ስጪ፣ርሁሩህ፣ቸር፣ናዛዚ ፣ እግዚአብሔር መንፍስ ቁድስ ማለት ነው ኣልፍ ና ኦሜጋ ቅድመ ዓለም የነበር ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማለት ነው የክብር ክብር ምስጋና ይግባው ለቅዱስ ኣምላካችን ጌታችን መድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ኣሜን ለሱ ላገኝችልን ለቅድስት ቁድሳ ኣዛኝ እናታችን ድንግል ማርያም ለዘለእለሙ ምስጋና፣ውዳሴ፣ስግደት፣ይግባት ኣሜን ኣሜን ኣሜን 🙏🙏🙏
@user-ys7uu4ov1j
@user-ys7uu4ov1j 3 года назад
አሜን ፫
@user-vo9mk9vx4j
@user-vo9mk9vx4j 3 года назад
ኣሜን ኣሜን ኣሜን
@user-me3ld7eu6l
@user-me3ld7eu6l 13 дней назад
በስመ አብ ግሩምና ድንቅ ነው የአባቶቻችን በረከት ይድረሰን አሜን አሜን አሜን
@Helina-xi9ph
@Helina-xi9ph 3 года назад
አስተማሪ መንፈሳዊ ፊልም ነው የቅዱሳን አባቶች በረከታቸው ይደርብን
@MaryMary-rg4qw
@MaryMary-rg4qw 3 года назад
አሜን አሜን አሜን በረከታችሁይደርብን
@Hana-ul9xi
@Hana-ul9xi Месяц назад
እግዛብሄር ይመስገን የቅዱሳን የአባቶቻችን ፆሎታቸው በረከታቸው ይደረብብን ቃለሂወት ያሰማልን ❤❤❤❤❤አሜን (፫)
@user-vo9mk9vx4j
@user-vo9mk9vx4j 3 года назад
የኣባቶቻችን የቅዳሳን በረከት ይደርብን ፀሎታቸውና ምልጃቸው ይርዳን ኣሜን
@user-nd8zm3ip9v
@user-nd8zm3ip9v 3 года назад
አቤቱ ጌታ ሆይ ለንስሀ ሞት አብቃኝ አባት ሆይ የቅድሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜንን
@abdulhashibassamindia7038
@abdulhashibassamindia7038 Год назад
ተመስገን ፈጣሪ ነዚ ክርኢ ዝፈቀድኻለይ አቦታተይ ልሓጥያተኛ ጋልኹም ፆሎትኹም ፀጋኹም ይሕደረኒ ሰለኩሉ ነገር ክበር ተመስገን አምላከይ
@meskeremteshome-iv2sk
@meskeremteshome-iv2sk 2 месяца назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን ጸሎት በረከታቸው ይደርብን🙏
@user-me2zc5ep8l
@user-me2zc5ep8l 3 года назад
አሜን ቅዱሣን አባቶቼ በረከታችሁ ይደርብን
@lulatesfay4937
@lulatesfay4937 4 года назад
የኣባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን ኣሜን ኣሜን ኣሜን 🙏🙏🙏
@betibeti72
@betibeti72 2 года назад
የአባቶቻን በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን 🥰🥰😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
@zemarimikiyastube5856
@zemarimikiyastube5856 3 года назад
በረከታቸዉ ይደርብን የቅዱሳን አባቶቻችን ምልጃ አይለየን
@user-ns6ub2jw8o
@user-ns6ub2jw8o 4 года назад
አሜን አሜን አሜን የአባቶቻችን በረከት በኛ በልጆቻቸው ሁሉ ላይ አድሮ ይኑር
@nolawieyasu4599
@nolawieyasu4599 3 года назад
Ll
@MeronGetablo
@MeronGetablo Месяц назад
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን በእውነት ❤❤❤
@user-ez4zp5pt5x
@user-ez4zp5pt5x 4 года назад
እግዚአብሔር አማላክ የፖውሊን ልብ ይስጠን ስለ ቅድሳን ብለክ ማረን አቤቱ ቅድስ ቃልክንም ለሚያስሙን እድሜና ጤና ስጣቸው
@user-ez4zp5pt5x
@user-ez4zp5pt5x 4 года назад
እግዚአብሔር ሆይ እንዴት ደስ የሚል ትምህርት ነው ልብን ይማርካል ተመስገን በረከታቸው ይደርብን
@dawitbrother9355
@dawitbrother9355 3 года назад
የእውነት እንደዚህ ተመሰጬ አድምጬ አላውቅም የቅዱሳኑ በረከት ከኛጋር ይሁን አሜን አሜን
@user-es7ki9wp1c
@user-es7ki9wp1c 4 года назад
የቅደሰን በረክትቸው ረደአትቸው አምልጀንትቸው ከህልቸይን ግረ ይህን አሜን አሜን አሜን
@user-mo2so5xu2j
@user-mo2so5xu2j 3 года назад
እግዚአብሔር ይመስገን ሰለማይናገር ስጦታው ህይወት የሆነውን ፊልም እንዳይ ለእረዳኝ ለሰራዊት ጌታ የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቹሁን ይደረብብን አሜን የተጠሩት ብዙ ናቸው ከሚድኑት ያአድርገን
@zekitube2212
@zekitube2212 Год назад
እግዚአብሔር በረከታቸውን ያሳድርብን
@user-nd8cj5sg6g
@user-nd8cj5sg6g 8 месяцев назад
ኡፍፍፍፍ እንዴት እንዳስለቀሰኝ የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን የአባ ጳውሊ እና የአባ እንጦስ በረከታቸው የደርብን
@azuaksumawit2513
@azuaksumawit2513 3 года назад
ኣምላክ ቅዱሳን የቅዱሳን በረከታቸው ያሳድርብን
@user-ys7uu4ov1j
@user-ys7uu4ov1j 3 года назад
የእግዚአብሔር ስሙ ዘውትር የተመሰገነ ይሁን የቁዱሳን በረከት ይደርበን👏⛪💞
@modayadi7956
@modayadi7956 3 года назад
አሜን፫ በርከታችሁ ይደርብን አባቶቻችን😭😭❤❤⛪➕🙏
@naahileetdirribaa1143
@naahileetdirribaa1143 Месяц назад
እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የቅዱሳን የሰማዕታት በረከት ረድኤታቸው ይደርብን ይባርከን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ኦርቶዶክስ ለዘለዓለም ትኑር ❤❤ ተመስገን
@user-dc5ir2wn1g
@user-dc5ir2wn1g 3 года назад
ኣሜንኣሜንኣሞን ቃል ህውት የስመልን።
@youshiindala9948
@youshiindala9948 3 года назад
የቅዱሳን በረከት ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@user-ip9th5gl3s
@user-ip9th5gl3s 3 года назад
የቅዱሳን ረድኤት በረከታቸዉ በኛ በደካሞቹላይ ይደር አሜን
@sebleseble5930
@sebleseble5930 4 года назад
የቅድሳን አባቶቻችን በረከቱ ይደርብን
@ttigistttigist2200
@ttigistttigist2200 3 года назад
አሜንአሜንአሜንን
@betibeti72
@betibeti72 2 года назад
የቅድሳን አባታችን ጳወሎሰ በረከቱ ይደርብን 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭🙏🙏
@user-hx4yp8bt8d
@user-hx4yp8bt8d 3 года назад
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን
@user-cv5du9gh5u
@user-cv5du9gh5u 3 года назад
በእውነት የቅዱሳን በረለታቸው ይደርብን አሜን
@meirimekell2140
@meirimekell2140 4 года назад
ኡፍፍፍ ፅናታቸው ኦ ጎይታ በዋሻ ላሉ የቅዱሳን በረከት እና ፀለታቸው ከኛ ይሁን
@user-qz8rc3sv5v
@user-qz8rc3sv5v 3 года назад
አሜን በረከታቸው ይድረሰን ለምታሰጋጁ ለምትልኩልንም ሁሉ ዎጋ ሰማያዊ ይስጥልን አሜን
@hanamintesinot8492
@hanamintesinot8492 3 года назад
የቅዱሳን አባቶቻችን በረከት ይደረብን 😢😢😢😢😢🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@user-jp2rj1kf5h
@user-jp2rj1kf5h 4 года назад
ቃለሂወት ያሰማኝ እልልል መፈሴ ይታደሳል
@asmertasmert783
@asmertasmert783 3 года назад
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃለ ህይወት የስመዐልና በረከቶምን ረድኤቶምን ናይ ቅዱሳን ኣቦታትና ምስ ኩላትና ህዝበ ክርስትያን ይኹን ኣሜን💒
@SamsungaA-ow1gv
@SamsungaA-ow1gv 3 года назад
አሜን ፫ የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን
@user-sd6nh3ri2n
@user-sd6nh3ri2n 3 года назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱስ ጳውሊ እና አባታችን ቅዱስ እንጦንዮስ በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን👐💠
@hannasalam672
@hannasalam672 Год назад
አሜን አሜን አሜን❤❤❤
@asssykhan3509
@asssykhan3509 3 года назад
የቅዱሳን በረከታችውእረደታቸው አይለየን አሜን (3(
@user-mr4zv9vz1j
@user-mr4zv9vz1j Год назад
የአባቶች በረከት ረድኤት ይደርብን አሜን
@mebratiabbas217
@mebratiabbas217 4 года назад
የቅዱሱኑ እረደይት በረከትን ይደርብን አሜን ፫
@user-pm9gb2uc8d
@user-pm9gb2uc8d 3 года назад
የቅዱሳን እረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደር
@ergoergo5945
@ergoergo5945 4 года назад
AMEN AMEN AMEN berektachew yderbn
@user-pi5hh7gf1l
@user-pi5hh7gf1l 4 года назад
በእውነት የቅዱሳን በረከት የድንግል ማርያም ምልጃ ፆለት ይደርብን
@user-dk7km1kq8z
@user-dk7km1kq8z 4 года назад
በረከታቸው ይደርብን አሜን የህንን ላቀረባችሁልን እረጅም እድሜ ይስጥልን አሜን የሰማነውን በልቦናችን አሳድርብን
@user-ln4bh5zw9p
@user-ln4bh5zw9p 3 года назад
የቅዱሳኑ በረከት ይደርብን
@alemalemgtgh8282
@alemalemgtgh8282 5 месяцев назад
የባቴቻችን በረከት በሁላችላይደር አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤
@user-do2hx6xi6o
@user-do2hx6xi6o 7 месяцев назад
የአባቶቻችን በረከት ከኛጋ ይሁንልን ❤❤❤
@user-ph8rl9yn2s
@user-ph8rl9yn2s 5 месяцев назад
.እግዛአቤሔርየመሰገን.የአባቶቸችን.በረከታቸዉየደረበን❤❤❤❤❤❤
@user-de8jl7bc6o
@user-de8jl7bc6o 3 года назад
የክዱሳን በረከት አሁላችጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን
@haymanothaymanot9209
@haymanothaymanot9209 4 года назад
አሜን አሜን አሜን እረዴታችሁ በረከተችሁ ፍቅርራችሁ ሰላማችሁ ለኛም ያብዛልን እግዚአብሔር
@user-jc2po6kv7u
@user-jc2po6kv7u Месяц назад
ቃል ህይዉት ያሰማልን በረኩታችዉ ይደርብን አባቶቻችን ፫ ❤
@ahmelahmel1485
@ahmelahmel1485 4 года назад
የቅዱሳን አባቶቻችን እረድኤት በረከት ይደርብን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን ቃለሕይወት ያሰማልን አሜን አሜን አሜን
@BuraqMob-vf4me
@BuraqMob-vf4me 18 дней назад
አሜን አሜን የቅዱሳን በረከት ይደርብን
@Rippedsad
@Rippedsad 3 года назад
በጣም፡ደስ፡የሚል፡በታሬካዊ፡የተመሠረተ የክርስቶስ፡አገልጋዮች፡ትምሕርተ፡ታሬክ አብዝቶ፣አብዝቶ፣አብዝቶ፣ይባርካችሁ።
@user-mo9qd3nm3e
@user-mo9qd3nm3e 3 года назад
የቅዱሳን በርከታችው ይደርብን 🙏🙏🙏
@selamtilahun8793
@selamtilahun8793 3 года назад
አሜን የቅዱሳን አባቶችና እናቶች ረደት በረከት አይለየን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን አሜን ፫
@guzguzgebeyawu9108
@guzguzgebeyawu9108 5 месяцев назад
እግዚአብሔር አምልክ የፓዉሊን ልብ ይስጠን ስለ ቅድሳን ብለክ ማረን አቤቱ ቅድስ ቃልክንም ለሚያስሙን እድሜና ጤኔ ሰጣቸዉ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@elsawendesen9253
@elsawendesen9253 3 года назад
አሜን አሜን አሜን ንንን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አንተ ጠብቀን ወኝቱ ከመቅርት ለንሰሀሞት አብቃን ያቅር በለን
@MmMm-ls9iy
@MmMm-ls9iy 6 месяцев назад
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን🙏🙏🙏❤❤❤❤🙌💖
@tigitube1665
@tigitube1665 3 года назад
የቅዱሳኑ በረከት ረድኤታቸዉ ይደርብን አሜን።
@DhJ-nk5wf
@DhJ-nk5wf 11 месяцев назад
እግዚአብሔርይመስገን የቅሳን አባቶቻችን በረከታችው ይደረብን አሜን አሜን አሜን
@As-nl5qi
@As-nl5qi 3 года назад
ጌታ ሆይ ይህን የቅዱሳን ታሪክ እንዳይ ሥለ ረዳህኝ ምሥጋና ይድረሥህ የቅዱሳን በረከት ይደርብኝ አሜን ፫
@user-ci5zn8lz3d
@user-ci5zn8lz3d 3 года назад
እደዛሬው ልቤ በደሰታ ተሞልታ አታቅም ክርሰቲያን መሆን ምንኛ መታደል ነው አምላኬ ሆይ ጥሩ ሰራ እድሠራ ትረዳኝ ዘድ እማፀንሀለሁ ያባቶቻችን በረከት ይደርብን 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
@nolawieyasu4599
@nolawieyasu4599 3 года назад
231+221=
@nolawieyasu4599
@nolawieyasu4599 3 года назад
Watching
@nolawieyasu4599
@nolawieyasu4599 3 года назад
M
@dabritutefera4938
@dabritutefera4938 4 года назад
አሜን፫ ቃለ ህይወት ያሰማልን የአባቶቻችን እርዴት በርከታችው ይደርብን
@user-yl4wn8qx9q
@user-yl4wn8qx9q 3 года назад
አሜን አሜን አሜን የቅዱሳን እረዲት በርኪት ይደርብን
@hsjjhjf3440
@hsjjhjf3440 3 года назад
የአባታችን የቅዱሳን ፆለት በኞላይ ይደሪ አሜን አሜን አሜን
@user-mt8gf6eh6i
@user-mt8gf6eh6i Год назад
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን አሜን አሜን
@rahelmamo4970
@rahelmamo4970 3 года назад
በረከታቸው ይደርብን በረከታቸው ይደርብን በረከታቸው ይደርብን
@zahra...9789
@zahra...9789 4 года назад
ቃለሕይወት ያሠማልን አሜን በኡነት2 ደገምሁት ቢያዩት አይጠገብም በረከታቸው ይድረሠን አሜን
@AliAli-it6fb
@AliAli-it6fb 3 года назад
የቅዱሳን በፀጋው በረከታቸዉ ይድረስልን
@Kw-mh8je
@Kw-mh8je 4 года назад
የቅዱሳን በረከታቸዉ ይድረሰን
@user-eq4lg5wf4l
@user-eq4lg5wf4l 4 года назад
የቅዱሳን በረከታቸዉ ይድርብን አሜን አሜን አሜን
Далее
娜美这是在浪费食物 #路飞#海贼王
00:20
Просмотров 4,8 млн
Can You Bend This Bar?
01:00
Просмотров 4,5 млн
የያዕቆብ ታሪክ/The story of jacob
41:25
Просмотров 179 тыс.
የጌታ ወዳጅ አባ ቢሾይ / Aba Bishoy
1:35:44
የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ታሪክ
1:42:34