Тёмный

ኢትዮጵያዌያኖች የ89ኛው ቺንኩዌ ሙሊኒ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድርን አሸነፉ ( Ethiopians won CINQUE MULINI Cross Country) 

GK Sports
Подписаться 1,3 тыс.
Просмотров 55
50% 1

#athletics #running #crosscountry #iaaf #ethiopia
የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ተከታታይ የሀገር አቋራጭ ውድድር አካል የሆነው የ89ኛው ቺንኩዌ ሙሊኒ ኢንተርናሽናል የሀገር አቋራጭ ውድድር በሁለቱም ጾታ በኢትዮጵያውያን የበላይነት ለመጠናቀቅ ችሏል፡፡ንብረት መላክ በአስገራሚ የአጨራረስ ብቃት 28 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በመግባት ማሸነፍ ሲችል ፣ ኬንያዊው ሊዮናረድ ኪፕኬሞይ ቤት 28 ደቂቃ ከ 58 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሙክታር እድሪስ 28 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ ለመውጣት ችሏል፡፡ በሴቶች በተካሄደው ውድድር ጸሀይ ገመቹ 18 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ለማሸነፍ ችላለች፡፡ ኬኒያዊቷ ቢይትሬስ ቼቤት 18 ደቂቃ ከ56 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ ሌላዋ ኬንያዊት ሼላ ቼላንጋት 19 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ በመሆን ጨርሳለች፡፡ በውድደሩ ላይ አለሚቱ ታሪኩ 4ኛ አዲስዓለም በላይ 7ኛ በመሆን ጨርሰዋል፡፡
ሶስተኛ የወጣችው ኬንያዊቷ ሼላ ቼላንጋት ከውድድሩ በኋላ በመታመሟ የሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት አልቻለችም፡፡ ሽልማቱ ላይ የምትታየው አውሮፓዊት ነጭ አትሌት ኬንያዊቷን ወክላ ዋንጫውን ብቻ እንድታነሳ ተደርጎ ነው እንጂ ሶስተኛ ወጥታ አይደለም፡፡ ቪድዮው ላይ እንደምታዩት ሜዳልያ ስትሸለም አትታይም፡፡

Опубликовано:

 

10 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 2   
@siferwsetafet9887
@siferwsetafet9887 3 года назад
3ኛ ያሸነፈችው ነጭ ኬኒያዊት ናት
@gksports716
@gksports716 3 года назад
ዲስክሪፕሽኑ ላይ 3ኛ የወጣችው ኬንያዊት አትሌት ለምን እንዳልተገኘች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ከውድድሩ በኋላ በመታመሟ ነው ሽልማቱ ላይ ያልተገኘችው፡፡
Далее
How to win a argument
9:28
Просмотров 522 тыс.