Тёмный

#እራስንመቀበል 

SAK Training & Consultancy
Подписаться 2,3 тыс.
Просмотров 604
50% 1

እራስን መቀበል ወይም self-esteem ማለት ስለእራሳችን ያለን እይታ ወይም እምነት ነው፡፡ እራስን መቀበል ማለት ስለእራሳችን ያለን ግምት ወይም ዋጋ ነው፡፡ ስለእራሳችን ያለን ዋጋ የሚወሰነው ስናድግ እና ካደግንም በኃላ በቤተሰባችን፣ በመምህራን፣ በጓደኞቻችን እና በስራ አለቆቻችን ስለእኛ ሲሰጡ የነበሩት አስተያየቶች ፣ትችቶች ወይም ማበረታቻዎች ላይ የሚመሰረት ነው፡፡ እራስን መቀበል እኛ ስለ እራሳችን ያለን እምነት እና ስሜት ነው፡፡
የተሰጠን ማንነት እኛ ምንም ተሳትፎ ወይም ምርጫ ሳናደርግበት በተፈጥሮ ያገኘነው ማንነት ሲሆን ይህም ወላጆቻችንን፣ ብሔራችን፣ የቤተሰቦቻችን ቋንቋ፣ ዜግነት፣ ሃይማኖት፣ ጾታ፣የተወለድንበት ቦታና ቀን፣ አገር፣ መልካችን፣ ቁመናችን፣ ባህላችንን የሚያጠቃልል ሲሆን
እኛ ስለራሳችን ማንነት በራሳችን ፈቃድ የምናደርገው ምርጫ ነው ለምሳሌ ሙያችን፣ የምንኖርበትን ቦታ፣ ዜግነት፣ ሃይማኖት፣ የህይወት ዘይቤ የመሳሰሉትን መምረጥ አንችላለን፡፡
ሁለት አይነት እራስን የመቀበል አይነቶች
ከፍተኛ እራስን የመቀበል ባህርይ/High self-esteem/፣ ከሰዎች ጋር በቀላሉ ይግባባሉ፣ ሌሎች ስለእነሱ የሚያስቡት፣ አያስጨንቃቸውም፣ እራሰቸውን በማንኛውም ቦታ ለመግለጽ አይቸገሩም፣ ምንም ነገር ላደርግ እችላለሁ ብለው ያምናሉ፣ተግባቢ ስለሆኑ ሰዎች ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ይፈልጋሉ ፣ሰዎችን የማሳመን ችሎታ አላቸው፣ ሌሎችን ለመምሰልና ለመኮረጅ አይሞክርም እራሳቸውን ይሆናሉ እንዲሁም በጣም የሚወዱት ቃል እችላለሁ የሚለውን ነው፡፡
ዝቅተኛ እራስን የመቀበል ባህርይ /Low self-esteem/
ከሰዎች ጋር አይቀላቀሉም ቢቀላቀሉም ሃሳባቸውን በሚገባ አይገልጹም ፣ በሌሎች ሰዎች ሃሳብና ተጽኖ የወደቁ ናቸው፣ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ውድቀቱ ወይም አለመሳካቱን ያስባሉ፣ ሁሌም የማይሳካላቸው ይመስላቸዋል፣ድምጻቸው አይሰማም፣ በህይወታቸው ደስተኞች አይደሉም፣ በህይወታቸው ማማረርን ያበዛሉ ነገር ግን ምሬታቸውን ለማረም ምንም እርምጃ አይወስዱም እንዲሁም የሚወዱት ቃል አልችልም የሚለውን ነው፡፡

Опубликовано:

 

1 окт 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 8   
Далее
🛑самое главное в жизни!
00:11
Просмотров 67 тыс.
Вопрос Ребром - Серго
43:16
Просмотров 738 тыс.
🛑самое главное в жизни!
00:11
Просмотров 67 тыс.