Тёмный
No video :(

ኪራላይሶን ፣ ኪራላይሶን ፣ ኪራላይሶን - ሰሙነ ህማማት+++ Kiralayson - By Kesis Dawit Fantaye 

Gere3025
Подписаться 198 тыс.
Просмотров 724
50% 1

ኪራላይሶን - ሰሙነ ህማማት+++ Kiralayson - By Kesis Dawit Fantaye
« ሰሙነ ሕማማት» ሰሙነ ሕማማት የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ነው፡፡ «ሰሙን» የሚለው ቃል «ሰመነ»ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ስምንት ቀኖች ወይም ሳምንት ማለት ነው፡፡ «ሕማማት»የሚለው ቃልም እንደዚሁ «ሐመመ»ወይም «ሐመ»ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን መከራዎች ማለት ነው፡፡ «ሕማማት» የምንለው ለብዙ ሲሆን ነው፡፡ ለአንድ ወይም ለነጠላ ሲሆን ደግሞ «ሕማም»እንላለን፡፡ እንግዲህ ሁለቱን ቃላት በማናበብ «ሰሙነ ሕማማት»ስንል «የመከራዎች ሳምንት» ማለታችን ነው፡፡ ሕማማት ስንል ምን ዓይነት ሕማም ወይም ምን ዓይነት መከራ? በማን ላይ? የሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት አለባቸው፡፡ ሰዎች ልዩ ልዩ አደጋ ሲደርስባቸው መከራ አገኛቸው ይባላል፡፡ በሽታ ሲይዛቸውና በደዌ ሲሰቃዩ መከራቸውን አዩ እንላለን፡፡ ያላቸውን ሲያጡና ኪሣራ ሲደርስባቸው ሌላው ቀርቶ ሲርባቸውና ሥራ ሲበዛባቸው እንኳን ተሰቃዩ መከራቸውን አዩ ይባላል፡፡ በሰሙነ ሕማማት የምናስበው የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ከላይ ለሰው ልጆች ከጠቀስነውና ከተለመደው ዓይነት መከራ ይለያል፡፡ የተለየ ጊዜ ተወስኖለት ሰሙነ ሕማማት፣ ሕማማተ መስቀል፣ ሕማማተ ክርስቶስ ወዘተ እያልን በተለየ መንገድና ሥርዓት የምንገልጽውም ልዩ መከራ ስለሆነ ነው፡፡ ሕማማት የምንለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ አይሁድ የተቀበለው የሐሰት ክስ፣ ፍርድ፣ መጎተት፣ መገረፍ፣ መገፈፍ፣ እርግጫ፣ ጥፊ፣ ጡጫ፣ ችንካር በአጠቃላይ በበርካታ ድርሳናት የተገለጠው አይሁድ የፈጸሙበትን ግፍ ሁሉ ነው፡፡ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራ በዓላማው፣ በአፈጻጸሙ፣ በመጠኑ፣ በምክንያቱ በአጠቃላይ በሁሉም መልኩ ከሰው ልጆች መከራ ጋር አይመሳሰልም፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን “የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፡፡”ይለዋል፡፡ (ኢሳ53፥3) አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ የተቀበለው ስለእኛ ሲል ነው፡፡ በእኛ ላይ መድረስ የነበረበትን መከራ ሁሉ እርሱ ተሸከመልን፡፡ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን፡፡ ይህን ሲያስረዳን ነቢዩ ኢሳይያስ “ሕመማችንንም ተሸክሞአል፡፡” በማለት ጻፈልን፡፡ (ኢሳ53፥4) አቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን፣ራራልን ፣ይቅር በለን፣ ኪራላይሶን፣ኪራላይሶን፣ኪራላይሶን።

Опубликовано:

 

19 апр 2022

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 3   
@user-vf8iz9yd1m
@user-vf8iz9yd1m 2 года назад
ኪራላይሶ ኪራላይሶ ኪራላይሶ አቤቱ ጌታ ሆይ ማረን ይቅር በለን እንደቸርነትህ አቤቱ እኔ በደለኛዋል ልጅህን ማረኝ እጅህ ይዳብሰኝ በጸሎታችሁ አስብኝ
@lnatesematstarsemaljkaryaa4308
@lnatesematstarsemaljkaryaa4308 2 года назад
🙏🙏🙏የመላእክት ዝማሬ ያሰማልን😭😭😭⛪💒🏥
Далее
Symmetrical face⁉️🤔 #beauty
00:15
Просмотров 2,3 млн
ሁሉ ባንተ ነው
13:21
Просмотров 7 млн
Symmetrical face⁉️🤔 #beauty
00:15
Просмотров 2,3 млн