Тёмный
No video :(

ወንጀለኛው ዳኛ መጨረሻ ክፍል 22 Wenjelegnaw Dagna Part 22  

የኛ ነገር YEGNA NEGER.
Подписаться 1,9 тыс.
Просмотров 3,1 тыс.
50% 1

#𝐖𝐞𝐧𝐣𝐞𝐥𝐞𝐠𝐧𝐚𝐰_𝐃𝐚𝐠𝐧𝐚_𝐒𝐭𝐨𝐫𝐲_𝐓𝐞𝐥𝐥𝐞𝐫_𝐍𝐚𝐫𝐫𝐚𝐭𝐞𝐝_𝐁𝐲_𝐇𝐚𝐲𝐦𝐚𝐧𝐨𝐭_𝐀𝐥𝐞𝐦𝐮
ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።
የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።
ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።
ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።
ከዚህ ባሻገር:
የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት
ተረት ተረት የመሰረት
ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።
ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Опубликовано:

 

27 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 13   
@Keder_Ahmed
@Keder_Ahmed 2 года назад
ከልብ እናመሰግናለን የሚገርም የሚደንቅ ትረካ 🙏
@fasikafiseha7958
@fasikafiseha7958 3 месяца назад
ዋው ምርጥ አጨራረስ ምርጥ ትረካ እና ምርጥ አተራረክ
@user-bm2fd8fl6v
@user-bm2fd8fl6v 2 месяца назад
የሚገርም ነው
@user-gl5bb2qg3i
@user-gl5bb2qg3i Год назад
እጅግ በጣም ድንቅ ድርሰት ከግሩም አተራረክ እንደዚህ ዘመን ተሻጋሪ መፅሀፎችን አቅርቡልን በርቱ ከልብ እናመሰግናለን!!!!🙏🙏📚📖🙏🙏🇨🇬🇨🇬
@fasikafiseha7958
@fasikafiseha7958 3 месяца назад
እናመሰግናለን 🙏
@poppingshewa10
@poppingshewa10 Год назад
በጣም አሪፍ ድርሰት እና ትረካ ነብር, ለመጀምራ ግዚ ትርካ ይሂን ያክል የረዘም ተመስጨ ሳዳምጥ ❤ 👌
@fasikafiseha7958
@fasikafiseha7958 3 месяца назад
የመጨረሻው መጀመሪያ.....
@selamserawu3125
@selamserawu3125 2 года назад
እናመሰግናለን ክበርት ይስጥልን ቃል የለኝም እጂግ ጥሩ ትርካ አሰተማሪ መፅሐፍ ነው ታሪካዊ መፀሐፍ ነው ተባርኩ።
@Peace-dv3ud
@Peace-dv3ud Год назад
እናመሰግናለን !!!
@duoa8816
@duoa8816 2 месяца назад
Thanks it is great performance 👏
@emebetgezhagne1094
@emebetgezhagne1094 2 года назад
Thank u very much . It was very fantastic
@mesaydiriba-hh7ic
@mesaydiriba-hh7ic Год назад
አሪፍ ነዉ: ግን የወንድይራድ መጨረሻስ?
@elsinadinberu4653
@elsinadinberu4653 2 года назад
ድንቅ መጽሐፍ ድንቅ አተራረክ ድንቅ አጨራረስ እውነት ብትቀጥን እንጂ አትበጠስም የኛ ነገር ትዩብ ከልብ አመስግኛለሁ ይልመድባችሁ ይልመድባችሁ። ካልተተረከ የልምዣትን ጀባ ብትሉን
Далее