Тёмный

የታንጉት ምስጢር - ታሪካዊ ልብወለድ ትረካ 🎙️ ክፍል - 4 

አብሪ መፅሐፍት 🪶 Abri Books
Просмотров 99
50% 1

በሀገራችን ከተፃፉ ታሪካዊ ልብወለዶች መሀከል እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች የአማርኛ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ይሉታል።
በሀገራችን በአፄ ቴዎድሮስ ህይወት ዙሪያ ከተፃፉት 2 ታሪካዊ ልብወለዶች አንድ ለናቱ እና የታንጉት ምስጢር የተሻለ ቦታ የሚሰጠውም ይህ መፅሀፍ ነው::
▶ ርዕስ - የታንጉት ምስጢር
📝 ደራሲ - ብርሀኑ ዘሪሁን
📜 ዘውግ - ታሪካዊ ልብወለድ
📅 የህትመት ዘመን - 1979
📖 የገፅ ብዛት - 228
🎙️ተራኪ - ተስፋፂዮን ዳንኤል
በ1926ዓ.ም ጎንደር ከተማ ነው ደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን የተወለደው፡፡
አባቱ ዘሪሁን መርሻ የቤተክህነት ሰው ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያንን በዜማ ከማገልገል በተጨማሪ የብራና መፅሃፍትንም ይገለብጡ ነበር፡፡ እናቱ ወይዘሮ አልጣሽ አግደህ የቤት እመቤት እንደነበሩ መዛግብት ያመላክታሉ፡፡ ብርሃኑ ለቤተሰቦቹ የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ከእርሱ በፊት 5 እህትና ወንድሞች አሉት፡፡
ስድስት አመት ሲሆነው ብርሃኑ በዘመኑ ልማድ ወደአብነት ትምህርት ቤት ገብቶ መማር ጀመረ፡፡ አባቱ የቤተክህነት አገልጋይ ቢሆኑም በዘመኑም ለቤተክህነት ትምህርት ከፍ ያለ ዋጋ ቢሰጥም ብርሃኑ ለትምህርቱ የሰጠው ዋጋ ከፍ ያለ አይመስልም፡፡ በአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ እስከ አስራ ሁለት አመቱ ድረስ ቢዘልቅም እውቀቱ እምብዛም ነበር ይላሉ፡፡ የግእዝ እውቀቱም ወንዝ የሚያሸግር አልሆነም፡፡
የአብነት ትምህርቱን ከመማር ጎን ለጎን ቤተሰቦቹን በስራ ያግዝ ነበር፡፡ ቤት ውስጥ ያሉትን እንስሳት እያገደ ውሎ ሲመለስም እንጨት ለቅሞ ይመጣ ነበር፡፡
ብርሃኑ የአብነት ትምህርቱን እየተማረ ባለበት ጊዜ ንባብን ስለተለማመደ ከስነፅሁፍ መጻህፍት ጋር መተዋወቅ ችሏል፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልቦለድ የሚባለውን የአፈወርቅ ገብረእየሱስ “ጦቢያ” (ልቦለድ ታሪክ) የደብተራ ዘነብ “መፅሃፈ ጨዋታ ስጋዊ ወመንፈሳዊ”ን ማንበብ ችሏል፡፡
እነዚህን መፅሃፎች ብርሃኑ ያነበባቸው ገና በአስራ አንድ አመቱ አካባቢ ነው፡፡ መፅሀፎቹን ያመጣለትም አዲስ አበባ የሚኖር አጎቱ ነው፡፡
የአብነት ትምህርቱን ሊጠቃልል አካባቢ ቀዳማዊ ንጉስ ሃይለስላሴ ወደጎንደር ሄዱ፡፡ በዛን ጊዜም የዘመናዊ ትምህርት (የመንግስት ተማሪዎች) ተማሪዎች ጃንሆይን ለመቀበል አንዳይነት ልብሳቸውን (ዩኒፎርም፤ የደንብ ልብስ) ለብሰው ሲዘምሩ ሲያያቸው ልቡ ለዘመናዊ ትምህርት ጓጓ፡፡ በዘመኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የፈረንጅ ተፅዕኖ ስላለባቸው የሃይማኖት መበረዝን ያመጣሉ “ፀረ-ማርያም ናቸው” ተብሎ ይታመን ስለነበር ቤተሰቦቹ ፈቃደኛ ሆነው ወደትምህርት ቤት ሊልኩት አልቻሉም፡፡ ብርሃኑ ግን ለመንግስት ትምህርት የነበረው ጉጉት ከፍ ያለ ስለነበር በልቡ ሲያሰላስለው ቆይቶ አንድ ቀን በኪሱ 50 ሳንቲም ብቻ ይዞ ጉዞ ጀመረ፡፡ እራሱ ብርሃኑ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ ብሏል
“ምንም እንኳ ቤተሰቦቼ ሃሳቤን እንደተቃወሙት ቢገባኝም የፈለገው ይሁን ብዬ በልጅነቴ መኮብለል አለብኝ አልኩና ወሰንኩ፡፡ ሃምሳ ሳንቲም አጠራቅሜ ወደባህርዳር ከተማ አቀናሁ፡፡ ባህርዳር ከተማ ስደርስም በጉዞ በጣም ተዳክሜ ስለነበር አረፍ አልኩ”
ከጎንደር የተጀመረው የእግር ጉዞ ባህርዳር ሲያደርሰው ብርሃኑ ደክሞት ስለነበር ወደአንድ ቤተክርስቲያን ደጃፍ ተጠግቶ ዕረፍት አደረገ፡፡ በዛም በትውልድ ቀዬው የጀመረውን የአብነት ትምህርት መከታተል ጀመረ፡፡ ለነፍስ መያጃ የምትሆን የዕለት ጉርሱን ፍለጋም ከሌሎች የአብነት ተማሪዎች ጋር እየወጣ “በእንተ ማርያም ተዘከሩኝ” እያለ እየለመነ ያገኝ ጀመር፡፡ በዚህ ሁኔታ በባህርዳር አራት ወር ከቆየ በኋላ ከቤቱ የኮበለለለት ዘመናዊ ትምህትን መቀላቀል አልቻለም፡፡ ጎንደር ያሉት ቤተሰቦቹ ናፍቆትም በልጅነት ልቡ ላይ እየበረታበት ሲመጣ ወደ ጎንደር ተመለሰ፡፡
ጎንደር ሲደርስ እናቱ በፅኑ ታመው አገኛቸው፡፡ የህመማቸውም መነሾ ልጄ ብርሃኑ ሞቷል ከሚል ጭንቀት ነውና ብርሃኑ ተበሳጨ፡፡ እናቱም ብዙም ሳይቆዩ አለፉ፡፡ የብርሃኑ ፀፀትም ተባባሰ፡፡ አባቱም የብርሃኑን ከፍተኛ የዘመናዊ ትምህርት መሻት ለዛም ያለውን ቁርጠኝነት ስላዩ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት እንዲገባ ፈቀዱለት፡፡ ብርሃኑ በዚህን ጊዜ በነጦቢያ የጀመረውን ንባብ ተያያዘው፡፡ በተለይ ወንድሙ የሚያመጣለትን ጋዜጦች በስስት ያነባቸው ጀመር፡፡ በዛን ጊዜም የከበደ ሚካኤል መፅሃፎች ለንባብ መቅረብ ጀምረው ስለነበር እየተከታተለ ያነባቸው ጀመር፤ ወደዳቸውም፡፡
ብርሃኑ በልጅነቱ የገባበት የአብነት ትምህር ቤት ከፊደል ጋር በሚገባ አስተዋውቆት ስለነበር ትምህርቱን የጀመረው ከሁለተኛ ክፍል ነው፡፡ የቀለም አቀባበሉ ጥሩ ስለነበረም በእጥፍ በእጥፍ ከክፍል ክፍል እየተሸገር በአራት አመት የትምህርትር ቆይታው ስምንተኛ ክፍል ደረሰ፡፡
ስድስተኛ ክፍል በነበረበት ጊዜም ስለአንድ አቶ ብሩ ስለሚባሉ ሙሰኛ ሰው ግጥም ፃፈ፡፡ ግጥሙም በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ለአንባቢ በቃችለት፡፡ በዚህ ብርሃኑ በጣም ተነቃቅቶ ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን እየተንተራሰ ግጥሞችን መፃፍ ጀመረ፡፡
ብርሃኑ በጎንደር የትምህርት ቆይታው ባሳየው ከፍተኛ የቀለም አቀባበል ተመርጦ በነፃ የትምህርት አድል ወደ አዲስ አበባ መጣ፡፡ ይህ የሆነውም በ1945 ዓ/ም ነው፡፡ በዚህን ጊዜም አስቀድሞ ይፅፍበት ከነበረው ማህበራዊ ጉዳይ ጎን ለጎን የፍቅር ግጥሞችን መጻፍ ጀመረ፡፡ እድሜውም ወደ 20ዎቹ እየተጠጋ ነበር፡፡
በአዲስ አበባ የብርሃኑ ፍላጎት የከፍተኛ ትምህርት መከታተል ነበር፡፡ በዚህም የቴክኒክ ትምህርት ቤት እንዲገባ ተፈቀደለት፡፡ ትምህርት ቤቱ ውስጥ በርካታ አሜሪካውያን መምህራን የነበሩበት ሲሆን አልፎ አልፎም ህንዳውያን መምህራንም ይገኙበት ነበር፡፡ በትምህርት ቤቱ ውስጥም ራዲዮ መካኒክ መማሩን ተያያዘው፡፡
የብርሃኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ጥሩ መሆኑን ያስተዋለው አንድ ኢራናዊ መምህሩ ደግሞ ከእንግሊዝና ከአውሮፓ ስነፅሁፍ ጋር አስተዋወቀው፡፡ በዛን ጊዜም እን ሼክስፒርን አሌክሳንደር ዱማስን የመሳሰሉ ፀሃፍያንን ማንበብ ጀመረ፡፡ ፅሁፎቻቸውንም በጣም ወደዳቸው፡፡ ወዲያው በትምህርት ቤቱ ውስጥ “ቴክኒ-ኤኮ” የምትል ወርሃዊ መጽሄት መታተም ጀመረ፡፡ ብርሃኑም የመፅሄቷ ዋና አዘጋጅ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜም በአማርኛም በእንግሊዝኛም እየጻፋ በመፅሄቷ ላይ ፅሁፎችን ያሳትም ጀመር፡፡ (የእንግሊዝኛ ፅሁፎቹን መምህራኑ አርትኦት ይሰሩለት ነበር) ከዚህ በተጨማሪም ለአዲስ ዘመን ለዛሬይቱ ኢትዮጵያና ለኤርትራ ድምጽ ጋዜጦች ፅሁፎችን ይሰጥ ጀመር፡፡ በዛው ትምህርት ቤት ውስጥም ተውኔት ጽፎ ለግቢው ማህበረሰብ ለዕይታ አበቃ፡፡ በዚህ ጊዜ ብርሃኑ ማንም ስለተውኔት አፃፃፍ አላስተማረውም ነበር፡፡
ብርሃኑ በልጅነቱ የተጣባው የስነጽሁፍ ፍቅር ስለነበር ፅሁፎችን በፖስታ ቤት በኩል ለዛሬይቱ ኢትዮጵያና ለአዲስ ዘመን ጋዜጦች ይልክ ነበር፡፡ አንድ ቀን እራሱ ፅሁፉን ይዞ ወደ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ቢሮ ሄደ፡፡ ዋና አዘጋጅ የነበሩትን አሃዱ ሳቡሬን አገኛቸው፡፡ እርሳቸውም በወቅቱ አዲስ ዘመንና ኢትዮጵያን ሄራልድን ዕለታዊ ጋዜጣ ለማድረግ ጎበዝ ፀሃፍያንን እያፈላለጉ ስለነበር ሲያገኙት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ሪፖርተር ሆኖ እንዲሰራ ጠየቁት፡፡ ብርሃኑም ያላንዳች ማወላወል ስራው ተቀበለ፡፡ በ1952 ስራውን ጀመረ፡፡ በዛም ሆኖ 347 ብር እየተከፈለው በጋዜጣው ላይ እየጻፈ የሚወደው ፅሁፍ የሙሉ ጊዜ ስራው ሆነ፡፡
ብርሃኑ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቀጥሮ የሙሉ ጊዜ ስራው ፅሁፍ ብቻ ሲሆን ጎን ለጎን ሌሎች መጽሃፎችን ለመፃፍ ጊዜ አገኘ፡፡ በዚህም በርካታ መጽሃፎችን ጽፎ ለህትመት አበቃ፡፡ በዚህም የእንባ ደብዳቤዎች፣ ድል ከሞት በኋላ (1955)፣ የበደል ፍጻሜ(1956)፣ አማኑኤል ደርሶ መልስ (1956)፣ የቴዎድሮስ እንባ (1958)፣ ጨረቃ ስትወጣ (1959)፣ ብር አምባ ሰበረልዎ (1960)፣ ማእበል የአብዮት ዋዜማ፣ ማእበል የአብዮት መባቻ (1973)፣ ማዕበል የአቢዮት ማግስት (1974)፣ የታንጉት ሚስጢር (1978) ስራዎቹ ናቸው፡፡
ብርሃኑ የታንጉት ሚስጢር የታተመ ሰሞን ታሞ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ገባ፡፡ አንድ ወር ከግማሽ አካባቢ ከተኛ በኋላ ከሆስፒታል ወጣ፡፡ ከሆስፒታል እንደወጣ “መንታ መንገድ” የሚል መፅሃፍ መፃፍ ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መፅሃፉ ለህትመት ሳይበቃ ድጋሚ ታመመና ሆስፒታል ገባ፡፡
እለተ አርብ ሚያዝያ 17/1979 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡
ለዚህ ጽሁፍ ግብአት መረጃ የተሰበሰበባቸው
ማዕቀብ፤ እንዳለጌታ ከበደ (2006)
Black lion; ሬዱልፍ ኬ. ሞልቬር
በፋና ራዲዮ የተተላለፈ ስለደራሲው ህይወት ታሪክ የሚያጠነጥን ዝግጅት (በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ የተዘጋጀ)
****************************************************************************************************
የማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ ቦታዎን ይምረጡ!
Choose your right social media niche!
#አብሪመፅሐፍት #Abribooks #AmharicAudioBook

Опубликовано:

 

30 сен 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии    
Далее
Почему?
00:22
Просмотров 344 тыс.
I Took An iPhone 16 From A POSTER! 😱📱 #shorts
00:18
እመጓ emegwa ሙሉ ትረካ
8:05:21
Просмотров 186 тыс.
Почему?
00:22
Просмотров 344 тыс.