Тёмный

የትውልዶች እንቆቅልሽ - ሁሉም የሰው ልጅ ሊያየው የሚገባ - ልብህ ምን ይላል? - Impact Documentary - Ashenafi Taye 

Impact Seminars
Подписаться 123 тыс.
Просмотров 38 тыс.
50% 1

ይህንን ቪድዮ ላይክ፣ ሼር ማድረግ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አይርሱ። Thank you for Watching, Please Subscribe for more!
Facebook: / impactseminarsofficial
Telegram: t.me/RippleImpact
Tiktok: .www.tiktok.com/@impactseminarsofficial
Instagram: / impactseminars
Podcaster: podcasters.spotify.com/pod/sh...
Join our Discord community: / discord
Books By Ashenafi Taye:
www.amazon.com/s?i=digital-te...
Also Featured on
ETV - Dagu - ዳጉ - • ዳጉ - አዲስ ዓመት፣አዲስ መንፈስE...
EBS TV :- Dagi Show - • "በእኔና ሞት መካከል ትንሽ ቀዳዳ ...
እሁድን በ ኢቢስ - • "የአሜሪካ ሚስጥር በአንድ የኬንያ ...
Abay Tv:- Sekela Talkshow - • ባለቤቴም አይረዳኝም .. ልጆቼም አ...
RiseUp Ethiopia - • ለ36 አመት ያህል ምን እንደምፈልግ...
Dawit Dreams - • አለማውቄን ያወኩት በ 36 ዓመቴ ነ...
Manyazewal Eshetu - • ህይወት ቀያሪ የአቶ አሸናፊ ታዬ ት...
- • የአሸናፊ ታዬ ቃለመጠይቅ |Manya...
ለበለጠ መረጃ: +251988068511 #selfimprovement #impact #impactseminars #ethiopia

Опубликовано:

 

20 фев 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 378   
@ImpactSeminars
@ImpactSeminars 4 месяца назад
የተወደዳችሁ የኢምፓክት ሴሚናርስ ቤተሰቦች፣ ይህ ዶክመንተሪ ይጠቅማቸዋል ብላችሁ ለምታስቧቸው ሰዎች ማጋራት እንዳትረሱ! ዋናው ዓላማችን እናንተ ህይወታችሁን እንድታሻሽሉ መርዳት ነው።እናመሰግናችኋለን!
@FasikaLemma-vu8bm
@FasikaLemma-vu8bm 4 месяца назад
@SalimSalim-nc1mp
@SalimSalim-nc1mp 4 месяца назад
እሽ
@AbdurahmanMohammed-qz8wq
@AbdurahmanMohammed-qz8wq 4 месяца назад
እኛም ከልብ አድርገን እናመሰግናቿለን ዶክመንተሪውን እያጋራነው ነው ሰዎች ዘንድ መድረስ አለበት።
@munahassan
@munahassan 4 месяца назад
Okay I will try to share
@engdaworktsegawu
@engdaworktsegawu 4 месяца назад
እሽ እያጋራን ነው እናመሰግናለን
@kalidotubeselman
@kalidotubeselman 4 месяца назад
አሼ እጅግ ልብ የሚነካ ታሪክ ነው 🤔በነዚህ ቤተሰብ ውስጥ የብዙሃን ኢትዮጵያዊን ቤተቦችን ህይወት ቁልጭ አርገህ አሳይተህናል ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባኻል ፈጣሪ እድሜ ከጤና ና ያድልህ🙏🙏🙏
@azebclark120
@azebclark120 4 месяца назад
አሼ ምን እንደምልህ አላውቅም ቃላት ነዉ ያጣሁት የልጆችህ አባት ያርግህ እድሜና ጤና ይስጥህ ከነቤተሰቦችህ የረገጥከዉ የነካኃዉ ሁሉ ይለምልም ሞገሱን መድሀኒዓለም ይስጥህ
@fierbelachew2175
@fierbelachew2175 4 месяца назад
የሰፈሬ ሰዎች 24 ቀበሌ በእውነት በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ይመስገን❤❤❤።
@mediSmart8090
@mediSmart8090 4 месяца назад
ሰወቹም በፍቃደኝነት ይህን በግልፅ ስላቀረባችሁ ሁልግዜም ደስተኛ ሁኑ አላህ ይስጣችሁ
@medtaff7545
@medtaff7545 4 месяца назад
አገራችን እደዚህ አይነት ውጥንቅጥ ውስጥ የገባችው እያንዳዳችን ወደ ውስጣችን ማየት ስለማንፈልግ ሌላው እየኮነንን እያስመሰልን ስለምንኖር ነው። ተወደደም ተጠላም ይሄ ፕሮግራም የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳ ነው ምንም መሸፋፈን አያስፈልግም። አገር የሚለወጠው መጀመሪያ በየቤታችን ያለው ችግሮቻችንን ጉዳችንን እንደነዚህ ቤተሰቦች መፍታት ስንችል ብቻ ነው። አሼ ቁልጭ አድርገህ ስላሳየኸን እናመሰግናለን ባሁን ሰአት በጣም በጣም ጠቃሚ ፕሮግራም ነው ቀጥሉበት
@user-gj1jy1fw8g
@user-gj1jy1fw8g 4 месяца назад
በስመ አብ ከመጀመሪያዉ አሰስከመጨረሻዉ በጉጉት እና በእንባ ነዉ ያዳመጥኩት ምክንያቱም የኔ ሂወትም እሄን ይመስል ነበር እናትና አባቴ እኔ ተረግዠ ነዉ የተፋቱ ስወለድም መቶ አልጠየቃትም ሳድግም እዬተሰደብኩ እዬተረገምኩ ነዉ ያደኩት አሁን ድረስ ጆሮዬ ላይ ያቃጭሉብኛል ለዛም ነዉ ያስለቀሰኝ 😢የብዙ ኢትዮጵያዊያን ችግሩ ነዉ በጣም እናመሰግናለን አቶ አሸናፊ
@rodasasefa4048
@rodasasefa4048 4 месяца назад
አሁን ለዚህ ነገር ምን ይባላል? እዉነትስ ከ ሀ እስከ ፐ ድረስ ያሉት ፊደላት ለዚህ Miracle power ቃል ይፈጥሩ ይሆን? ..... አንድ ነገር ገረመኝ የአባትዬዉ ግርማ ሞገስ የእናትዬዋ ደርባባነት የእህትማማቾች በእሳት የተፈተነ ማንነትና ከእጃቸዉ ያመለጣቸዉ የመሰላቸዉ ሒወትና በተስፋ መቁረጥ የተሰበረ የዋህ ማንነት።።።።።።።።።።።።።።። መምህር እሼ ደማቅ ታሪክ ነዉ የፃፍከዉ🙏🙏🙏 ይሔን ቤተሰብ የልባችሁን ንፅህና አይቶ በዚህ መልኩ እግዚአብሔር ጎብኝቶታል። ፈጣሪ መጨረሻዉን ያሳምረዉ። ብዙ አስተምራችሁኛል አመሰግናለሁ
@abelt3792
@abelt3792 4 месяца назад
በመጀመርያ ከእግዛብሔር በታች የህይወት መምህር ለአሼ ላመሰግነው እወዳለው በመቀጠልም በዚ ቨድዬ ያለምንም መወላወል በህይወታቸው ያጋጠማቸው ተግዳሮት በማጋራት እንደ መሰተዋት በዚ ቨድዬ ራሳችንን ላሳዬን ለመላው ቤተሰብ አመሰግናለው
@mosh-3974
@mosh-3974 4 месяца назад
ይህ ቤተሰብ እኛን ለማስተማር በዚህ ደረጃ ሚስጥራቸውን ማካፈላቸው እኛን ለማስተማር ትልቅ ዋጋ እንደከፈሉ ነው የሚሰማኝ በጣም አመሰግናችኋለሁ። አቶ አሸናፊ በጣም ነው የማከብርክ!!!!🙏
@user-wy3id9wg2m
@user-wy3id9wg2m 4 месяца назад
እራሴንና አሰተዳደጌን ያየሁበት ልብ የሚነካ የራሴን ታሪክ ያየሁበት ቤተሰብ አቶ አሸናፊ ሰላንተ ምንም ብል ልቤዉሰጥ ያለህን የክብር ቦታ አይገልጸዉም ፈጣሪ ረጅም እድሜና ጤና ይሰጥህ ለኔ ሰዉ መሆን ያሰተማርከኝ ሰዉነህ አከብርሀለዉ
@Famousamanuelwithnovideo
@Famousamanuelwithnovideo 4 месяца назад
ኦው በጣም የሚደንቅ ነው እራሳቸውን በዚ ልክ exposed አድርገው ለኛም ስለተረፉን በጣም አናመሰግናለን አሹዬ ይመቸኛል እኮ ሆነስት ነው ነገረየው በጣም ስለገባው ማስመሰል እሚባል ነገር አለባብሶ ማለፍ የሚባል ነገር የለም ያቀዋል ማን እንደምናገር ego አሹዬ ፊት ሲቆም ይሽኮረመማል በርታልን አሹዬ
@adanetesfaye8048
@adanetesfaye8048 4 месяца назад
እስከዛሬ ድረስ ትምህርት ነበር ስንማር የነበረው አሁን ደግሞ በተግባር ከአሁን በኃላ ቃል እገባለሁኝ እራሴን ለማከም ደግሞም አደርገዋለሁኝ እንደዚሁ አይነት ታሪክ እኛ ቤትም አለ።
@royaedsfkkfjdrujr161
@royaedsfkkfjdrujr161 4 месяца назад
በርታ ብሮ ፈጣሪ ይርዳህ
@Rehobottalu
@Rehobottalu 25 дней назад
ምን አይነት ድንቅ ስራ ነው!!በእውነት አሸናፊ የአገር ብቻ ሳይሆን የአለም ሀብት ነው ❤
@yeshibeyene3530
@yeshibeyene3530 4 месяца назад
ትልቅ አስተማሪ የሆነ ታሪክ ነዉ በሰዉ እንዳንፈርድእና ፍቅር ሁሉንም እንደሚ ቀይር ተምሬበታለሁ እሼ እግዚያብሄር እድሜናጤና ይስጥህ
@moke4925
@moke4925 4 месяца назад
እግዚአብሄር ይባርክህ!!! ምን አይነት ተአምር ነው!!! ሳስበው እኔ እህቶቼ ብዙ አሉታዊም አውንታዊም ነገር ከቤተሰብ መውረሳችን እኛ ብለን የምንኖረው ማንነት የኛ እንዳሎነ ገባኝ!!! ትልቅ የማንቂያ ደውል ነው!!
@gelayeguta
@gelayeguta 4 месяца назад
የቤታችን ታሪክ ተነክቼበታለው ለማስተካከል ጥረት አረጋለው እግዚአብሔር ይስጥልኝ ❤❤❤
@omabdhellaham2722
@omabdhellaham2722 4 месяца назад
ወላሂ እውነት እውነት እላለሁ ይሄነገር እኛቤት ውስጥ እየተካሄደ ያለነገር ነው በዚህም ምክኘት በስደት እራሴን ደብቄ ያለሁ ሰውነኝ ሁሉንም ብሮግራም ሳይ እያነባሁ ወደውስጥ አራሴን እያየሁ ነው ወንድማች ዘመንህ ሁሉ አላህ ብርሃን ያድርግልህ እኔንም በርቀትም ቢሆን አድነኝ አድነኝ አድነኝ ውለታውን አላህ ይከፍልካል
@addisyibewoldemeskel5034
@addisyibewoldemeskel5034 4 месяца назад
ሰላም አቶ አሸናፊ ይህንን ዶክመንትምሪ በፅሞና ተከታተልኩት በጣም አስተማሪ እና ሁላችንም ልጅነቴችን እና ቤተሰቦቻችን ላይ ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናል እናመሰግናለን።
@meskeremdaba375
@meskeremdaba375 4 месяца назад
በእውነት ይሄን ቤተሰብ ግልፅነቱን ወድጄዋለው ተባረኩ የብዙ ቤተሰብ ታሪክ ተመሳሳይ ነው ሁላችንም የራሳችንን ታሪክ እንድንመረምር ያደርጋል እናመሰግናለን አሼ
@tesfayeethiopia
@tesfayeethiopia 4 месяца назад
በጣም ትልቅ ስራ ነው አሹ የኢትዮጵያ መድሀኒት ነው ይህ
@berasalembelete6266
@berasalembelete6266 4 месяца назад
አሼ በጣም ጥልቅ የሆነ ሙያዊ እገዛ ነው ያየሁት ገና ብዙ ነገሮች ከአንተ እጠብቃለሁ ፈጣሪ ይባርክህ።
@yitbarekadane4332
@yitbarekadane4332 4 месяца назад
የ ይህ ታሪክ የብዙ ኢትዮጽያውያን ታሪክ ነው ስንክሳራችንን ለማስወገድ ብዙ እሹዎች ለተፈጠሩለት አላማ የሚኖሩ ያስፈልጉናል። ረጅም እድሜ ለአሹ
@PeacefromJesus
@PeacefromJesus 4 месяца назад
ዮሐንስ 10:27፤ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ ዮሐንስ 10:28፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
@belcon3141
@belcon3141 4 месяца назад
አለም እንኳን ደስ አለሽ ወደዚህ ሰላማዊ ደማቅ የፍቅር ብርሃን ሒወት መመለስ በመቻልሽ።ፈጣሪ በሰው ተመስሎ ቤታችሁ በአሼ በኩል ገባ ድሕነትም ሆነ። እናንተ ቤት የበራው ብርሃን ለብዙዎቻችን የሗላችንን እንድናይና አሑናችንን መርምረን ሒወታችንን እንድናስተካክል ረድቶናል እናመሰግናለን ።ረጅም እድሜና ጤና ለቤተሰባችሁ እና ለአቶ አሸናፊ።
@zeharaalemu5877
@zeharaalemu5877 4 месяца назад
አሸናፊ ላንተ የተለየ ክብር አለኝ እድሚ ይስጥህ ኑርልን እንደዚህ አይነት ህክምና የሚያሰፈልገን አንተን በአካል ማግኘት እፈልጋለሁ ከአፋር ክልል ነው የምፀፍልህ
@baslielgirma342
@baslielgirma342 4 месяца назад
እጅግ የሚገርም ታሪክ ነው ለብዙ ሰው ትምህርት ይሆናል ፡፡
@eyobaf
@eyobaf 4 месяца назад
እድሜ እና ጤና ይስጥልን አሽየ ትልቅ ስራ ነዉ የሰራህ የኘን ደስታ የኛን ይቅር ባይነት የማይፈልግ ጠላታችን በሰራኸዉ ስራ ተሸንፏል እግዚአብሔር ይመስገን
@rozarozaroza5022
@rozarozaroza5022 4 месяца назад
እግዛብሄር ይመስገን ለሁላችንም እሰከ ዘላለም ፋቅር ይስጠን
@alemzeleke2231
@alemzeleke2231 4 месяца назад
በጣም ነው ደስ ያለኝ የብዙዎች ቤት በዚህ ታሪክ ይሰራል አሼ ተባረክ!!
@kesisAnanya3373
@kesisAnanya3373 2 месяца назад
ምርጥ አስተማሪ ታሪክ ነው ይህ የዕድገትና የከፍታ ዘመን ይሁንላችሁ❤❤❤
@munahassan
@munahassan 4 месяца назад
ለረጅም ጊዜ ትምህርትህን እከታተላለሁ ብዙ ተጠቅሜያለው ፡ እናም ሁልጊዜ ገና ብዙ መሬት ላይ የወረደ ስራ እንሰራለን ስትል ይገርመኝ ነበር ፡ ከዚህ በላይ ምን ሊሰራ ይሆን ብዬ አስብ ነበረ ፡ ቃላት የለኝም ለአንተ አቶ አሸናፊ ፡ ለቤተሰቡም ምስጋናዬ ከፋ ያለ ነው እነድንማርበት ፈቅደው ስለወጡ ፡ በሚገርም ሁኔታ ተመሳሳይ ከሚመስል ቤተሰብ ነው የተፈጠርኩት ከነሱ የሚለየው የኔ እናትና አባት ወደማይቀርበት ሄደዋል፡ ልጆቹም እነደዛው እንደዞረበን ግማሾቻችን በስደት ግማሾቹ በ ሃገርቤት እየገፋን ነው ፡ ሌላው እኛም እኛቤት የሆነ ነገር አለ ብለን እናስባለን ፡ ወይ የሆነ ነገር ፡ ሁላቹንም በጣም እናመሰግናለን
@abentekelly9387
@abentekelly9387 4 месяца назад
እኔም ቤት ተመበሳይ ታሪክ አለ ፣፣ አባቴ ግን ችግሩ ማንም ሳያውቅለት በቅርብ ወራት በፋት ወደ ማይቀርበት ሄደ አሁን የቀረነው እየተነቆቁርን አለን፣፣
@munahassan
@munahassan 4 месяца назад
@@abentekelly9387 እንደዚህ አይነት ችግር በየቤቱ ያለ ይመስለኛል፡ ማወቁ በራሱ ትልቅ ነገር በራሳችን አንዳንድ ነገር ለመረዳት ይጠቅመናል፡ በተለይ በሚፈጠሩት ነገሮች ላለመበሳጨት እና ተረጋግቶ ለማየት ይጠቅመናል
@nahombirhanu7639
@nahombirhanu7639 4 месяца назад
እግዚያብሔር አሁንም ትልቅ ነገር ያድርግለት ለዚ ቤተሰብ በእውነት ጀግኖች ናቹ እራሳችሁን አሳልፉቹ ሰታቹዋል ስንት ቤተሰብ እንደሚድንበት እርግጠኛ ነኝ። በጣም የገረመኝ ግን ይሔን የመሰለ docmuntery የያንዳንዳችንን ህይወት ሊቀይር የሚችልን ነገር ሁለት ሺ ሰው ነው ያየው ሳስበው ሌላ አለም ውስጥ ነው ያለነው።
@user-ud1iz8ql2b
@user-ud1iz8ql2b 4 месяца назад
Ename betame emigeremenge negere sente emayereba negere b million eyetaye ehane yemesele hiwote emikeyere....yegeremale
@surafelhaile476
@surafelhaile476 4 месяца назад
No words can express my feelings but joy with tearful eyes. This is a wonderful documentary that broke the chain of this generational curse from these lovely family. I wish all the blessings to each family members. Ashe … I may pray that God gives you more grace to use you and change more lives. God bless!
@surafelhaile476
@surafelhaile476 4 месяца назад
Love always wins!
@yoditreta8923
@yoditreta8923 4 месяца назад
እግዚአብሔር ምስክሬነው በጣም ነው ያለቀስኩት የሁላችንም ችግር ነው በጣም ምስጋና አቀርባለሁ
@seadamohammed-tb1ie
@seadamohammed-tb1ie 4 месяца назад
የህይወት ትምህርት ስለተማርኩ አመሰግናለሁ፡፡ ኑርልን መምህር አሸናፊ
@ermiasalex5244
@ermiasalex5244 4 месяца назад
የሚገርም ህክምና ነው። መቼም ይህ ለአንድ ሰፊ ቤተሰብ ከፈጣሪ የተላከ ሽረት/ፈውስ ነው። አቶ አሸናፊ የሰምህን ትርጉም እየኖርክ ያለህ ጀግና ሰው ነህ፤ ለደሀ ሀገር መዳኒት እንዳንተ ያለ ሰው ሲበረክት ነው፤ ጤናህን ከረጅም እድሜ ጋር እመኛለሁ።
@abebesolomon6519
@abebesolomon6519 4 месяца назад
በእውነት እግዚያብሄር ይህን ቤተሰብ ባርኮታል ደስ የሚል ታሪክ ደስ በሚል አቀራረብ አሼ ትውልድ ነው ያዳንከው እግዚያብሄር ዕድሜ ከጤንነት ጋር ያድልህ
@SalimSalim-nc1mp
@SalimSalim-nc1mp 4 месяца назад
ስለዉነት በጣም የተማርኩበት ነዉ በመጀመርያ እህታችን ለመለወጥ ያላትን ፈላጎት አይቸበታለኩ በመቀጠል አቶ አሼ ያደረከዉ ነገር በቃላት የሚገለፅ አይደለም እኔ ስለዉነት ደስ ብሎኛል እረጅም እድሜ ከጤናጋር ይስጥልን
@banchizeki
@banchizeki 4 месяца назад
በጣም ነው ምናመሰግነው ህይወታችሁን እኛ እንድንማርበት ስላካፈላችሁን 3 ጊዜ ነው ደግሜ ያየሁት አብሬችሁ አለቀስኩ መጨረሻ ላይም አብሬችሁ ሳኩኝ እግዚአብሔር ይመስገን እናት እና አባታችሁ በህይወት እያሉ ይህ አንድነት ስለሆነ በጣም እድለኞች ናችሁ ስለእናንተ በማወቄ አከበርኳችሁ በእናንተ ምክንያት ብዙ ቤቶች ስለሚሰሩ እግዚአብሔር ይስጣችሁ ጋሽ አሼ እግዚአብሔር ይባርክህ እናመሰግናለን ❤❤
@seifedemissie4675
@seifedemissie4675 4 месяца назад
ይህ የብዙ የማህበረሰባችን ህይወት ነው! ችግሩ በግልፅ በዚህ ደረጃ ከመወያየትና የችግሩን መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ እሱ ነው፣ እነሱ ናቸው በማለት ከመነጋገር ይልቅ በመቆሳሰል ህይወት በህይወት እያለፈች ችግሮችም encapsulated ሆኖ ይኖራል! Thank you for sharing these painful history for the community!
@aziye
@aziye 3 месяца назад
ሰዎች ዛሬ ለሆኑት ማንነት የትናንት ስሪት ውጤቶች ናቸው ። አንዳንድ ሰዎች መጥፎ የሚሆኑት በተፈጥሮ አቸው መጥፎ ሁነው ሳይሆን ትላንትናቸው በአዕምሮ ወይም በአካል የስነልቦና ጉዳት ስለ ደረሰባቸው ነው ለመፍረድ ከመቸኮል ይልቅ ጀርባቸውን ለመመርመር እንሞክር!አቶ አሸናፊ እናመሰግናለን !💚😍
@negestqueen
@negestqueen 2 месяца назад
አቶ አቨናፊ እኔ የምታቀርባቸዉ ን ፕሮግራሞች በጣም ከማድነቄ የተነሳ ደጋግሜ አያቸዋለሁ! የዛሬዉ ደሞ በጣም የተለይ ነዉ ! ልዩ ሰጦታ አለህ ! በጣም profficinal የሆነ ዝግጅት🙏🏻 ቀጥልበት
@AlphaDream-gb5zq
@AlphaDream-gb5zq 4 месяца назад
የምርም ያስተምራል፤ እናመሰግናለን ምሳሌዎቻችን። ወደፊት ቁጥር ሁለትን ፕሮግራም እንጠብቃለን። ፖተርኑን አሸንፋቹ ለልጆቻቹ የተሻለ አለም ፈጥራቹ ማየት እናፍቃለሁ። ሁላችሁም ደግ ናቹ። በግሌ አመሰግናለሁ እናም መልካም ምኞቴን አልሰስታችሁም።
@user-js6mr1wy3v
@user-js6mr1wy3v 4 месяца назад
እግዚአብሔር ይባርክህ አብ! በእንባ ነው የተከታተልኩት። ይህ በሽታ በዚህ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የሚበዛው ቤተሰብ ውስጥ ያለ በመሆኑ ትምህርቱ ዓለም አቀፍ ነው። የሃገራችንም ፓለቲካ ይኸው ነው!!
@terhashagos9261
@terhashagos9261 4 месяца назад
አሼ ምን እንደምልህ አላውቅም ቃላት ይጣሁት የልጆችህ አባት ያርግህ እድሜና ጤና ይስጥህ ከነቤተሰቦችህ የረገጥከው የነካከው ሁሉ ይለምልም ሞገሱን መድሀኒ ሀለም ይስጥክ❤❤❤
@nahombirhanu7639
@nahombirhanu7639 4 месяца назад
አሼ አሁን የዚን ቤተሰብ ታሪክ አየተከታተልኩ የራሴን ቤተሰብ pattern ለማየት አየሞከርኩ ነው ግን ባንድም ይሁን በሌላ እኔም ብዙም የራቀ አይደለም ግን የራሴን ፓተርን መስራት አለብኝ I will have do it!
@eliasaddis2049
@eliasaddis2049 4 месяца назад
አሼ የህይዎት መምህሬ ትልቁን የፈጣሪ ህንፃ በዓላማው እንዲኖር በማደርገው ጉዞዬ ሜንቶር ስለምታደርገኝ አመሰግንሃለሁ ፈጣሪ ፀጋውን ያብዛልህ ።
@ethopialove3488
@ethopialove3488 Месяц назад
ብእውነት እያለቀስኩነው የጨረስኩት😢 አንተሰውየ እድሜዘመንህ የተባረከ የተቀደሰ ይሁንልህ በእውነት ላንተ ቃላት የለኝም ❤አንተንመከታተል ከጀመርኩ ጀምሬ ልክእደአባቴ ለእድሜህ መሳሳት ጀምሬለሁ ፈጣሪ እረጅምእድሜ ከጤናጋ አብዝቶ ይስጥህ❤ የነአለምፀሀይ ህልምም ተሳክቶ ዳግም ይሄንታሪክ ለማየት ያብቃኝ እኔንም
@fasikahailu1400
@fasikahailu1400 4 месяца назад
❤❤❤❤❤❤❤❤❤እጅግ የሚገርም እግዚአብሔር የሚወደውን ስራነው የሰራኸው አሼ።
@abrhameden1447
@abrhameden1447 2 месяца назад
በጣም በጣም ነው የምናመሰግነው አሼ እግዚአብሄር ከዚህ በላይ ያብዛህ ሂወታችሁን ለሰዎች መማሪያ ይሆናል ብላችሁ ስላስተላለፍችሁልን ክልብ አመሰግናለሁ ብዙ ነገር እንዳስተው እንዳስብና የኔ እንድመረምር ለቀሪው ሂወቴ ምን አይነት ዘር መዝራት እንዳለብኝ አስተምራችሁኛል እንደዚህ አይነት ዶክመንተሪ ቢቀጥል ደስ ይለናል አሼ ሰዎችን የምታወራበት መንገድ እያንዳንዱን ነገር እምትገልጽበት እንድናስተውል የምታረግበት ነገር በጣም ደስ ይላል እንደዚ አይነት ኢንተርቪ በጣም ደስ ይላል ይቀጥልልን ዶክመንተሪው 🙏🙏🙏🙏
@mekdesadane263
@mekdesadane263 4 месяца назад
አሹ🙏 ቃለ ህይወት ያሰማልን! መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን!🙏
@alemuberta6264
@alemuberta6264 4 месяца назад
የአንድ ቤተሰብ ሦስት ትዉልድ ሲቀባበለዉ የመጣ የሠላምና የፍቅር እጦት በስተመጨረሻ በጣም በሚገርም ሁኔታ በእርቅናና በይቅርታ በፍቅር በመተቃቀፍ የቤተሰቡ ታሪክ ሲቀየር በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል። በእዉነትና በእዉቀት፣በፍቅር በብርሃን ዉጤት የታየ በዚህ ቤተሰብ ዙሩያ ጥልቅ የማማከር ዙርያ በመስራትህ በእዉነት አሼ የአንበሳዉ ድርሻ ምትወስደዉ አንተነህ። እጅ ነስቼ አጨብጭቤያለሁ፣ እንድንቄሀለዉ። ስላገልግሎትህ እግዚአብሔር ይስጥህ ከሙሉ ጤና ከረጅም እድሜ ጋር ኑርልን🙏❤
@alphamedia1786
@alphamedia1786 4 месяца назад
አሸ ሁሌም የምታስደምመን ድንቅ ሰው ነህ እግዚአብሔር በዚህ ሰዓት የላከህ! ለትልቅ ነገር እንደሆነ እራሱ ጊዜው ይናገራል። አምላክ ዘመንህን ይባርክልን ኑርልን
@ShetayTurki
@ShetayTurki 4 месяца назад
ይሄ ታሪክ ሳይቀነስ ሳይጨምር የኛ ቤት ታሪክ ነው እነሱ እድለኛ ናቸው በጣም ከቁጥር ሳይጎሉ ታረቁ እኛን ግን ሞት ነጣጠለን አባቴን ወንድሜን እህቴን ሞት ነጠቃቸው እና በርቱ አምላክንም አመስግኑ ❤❤❤❤
@genilove5414
@genilove5414 3 месяца назад
በእንባ ነው የተከታተልኩት የኔን ቤተሰብ ነው ያየሁት አቶ አሸናፊ በጣም ነው የምናመሰግነው
@TsinatKassahun
@TsinatKassahun 15 дней назад
በጣም በጣም አስተማሪ ለብዙ ሰዎች ትምህርት የሚሆን ነው
@TigistBekele-vb9tm
@TigistBekele-vb9tm 4 месяца назад
በጣም ጥሩ ስራነው ብዙ ተምሪበታለሁ እራሴን አየሁበት እድሜ ይስጥህ እውነት አብዛኞኛችን ሳናቀው ምን ያህል እንደተጎዳን ነው የተረዳሁት እራሴን ለማከም ጥረት አደርጋለሁ
@alem7785
@alem7785 4 месяца назад
ሌሎች ሞትቬሽን ብለው አዳራሽ ሙሉ ሰው ሰብስበው ገንዘብ ይለቅማሉ አንተ ቤተሰብ ድረስ ሄደህ ግዜህን ጉልበትህን እውቀትህን ስለምትሰጥ በጣም አደንቅሃለሁ ዋጋው እጅግ ብዙ ነው በገንዘብ ማይተመን ። I hope to see this families bright future 🎉❤ thank you thank you thank you ashe 🙏🏾🙏🏾🙏🏾🙏🏾
@user-lh3tc1gg9h
@user-lh3tc1gg9h 4 месяца назад
በጣም አሪፍ ትምህርት ማሻ አላህ ደሲላል ብዙ ሠወችን ያስተምራል እኔ እናመሠገግናለን
@suzy1523
@suzy1523 4 месяца назад
እያንዳንዳችን ግዋዳ ስንት እማይታውቀ ይዘነው እምንዞረው ችግሮች አሉ እንዲ በቀላሉ ሊፈታ እግዚአብሔርን ፍቅራቹን ሰላማቹን ያብዛላቹ እናመሰግናለን ስላካፈላቹን በግልጽ ሚስጥራቹን ገልጻቹ ስላሳያቹን እናመሰግናለን ጋሽ አሸናፊ 😊❤
@addisushimeles7697
@addisushimeles7697 4 месяца назад
This is so powerful.Ashe as himself described he is not motivational speaker he is a teacher. And today I witnessed he perfectly know what he is teaching.This documentary proved that he can walk the talk. This is one of a kind to teach everything about paradigm shift in Ethiopian way. We the students now can't complain about not be able to read and understand the books of great scholars in the field of personal development. This is like መስማትን የሚፈልግ ይስማ። ክብር ለአቶ አሼ ና ይህ ለውጥ ይመጣል ብለው በማመን ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸውን ለዚህ ሙከራ አሳልፈው ለሰጡ🙏🙏🙏 Mission Accomplished 🎉🎉🎉
@akaluatnafu3675
@akaluatnafu3675 4 месяца назад
አሹ እኔ የአንተና የዳዊት ድሪም ተከታታይ ነኘ በህይወቴም ላይ ትልቅ ለዉጥ አያመጣሁ ነዉ አንድቀን አንተገረ እና ዳዊት መጥቼ መሰክረለሁ እረገጠኛ ነኝ። ከሰራቸዉ አትጥፋ እቺ ኮሜን እደማሰታወሻ ትቀመጥልኝ እመጣለሁ። በዚጉደይ የምሰሩሰዋች እግዚአብሔር ያብዛችሁ።
@semiraweleyewa3586
@semiraweleyewa3586 4 месяца назад
ዋዉ ወሏሂ በጣም ነዉ ያለቀስኩት በጣም ደስ እሚል ህክምና ነዉ
@SurprisedIsoscelesTriang-me9vb
@SurprisedIsoscelesTriang-me9vb 4 месяца назад
አሼ ምን እንደምልህ አላቅም በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል ፈጣሪ ብቻ ዕድሜ ጤና ይስጥህ!! የምትረዳኝ እንድ ችግር አለ ከለጋነቱ የሚፈታ የሀገር ጉዳይ ስልክህን ማግኘት ለኔ እጅጉን አስፈላጊው ቁልፍ ነው
@banchizeki
@banchizeki 4 месяца назад
ሁላችንም ብዙ ሰው አይቶ እንዲማርበት sher አናርግ
@tgnegn3879
@tgnegn3879 4 месяца назад
እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
@nebiatdebesay245
@nebiatdebesay245 4 месяца назад
እግዚአብሔር ይባርካቹ መላዉ ቤተሰብ ብዙ ነው የተማርነዉ ከናንተ ሁላችን ቤት ይለዉን ችግር ነው ያየነው ተባረኩ ጀግናዎች ናቹ በጣም አመሰግናለሁ ❤❤❤ AShu good job
@ybogale
@ybogale 4 месяца назад
ከራሳችን ኢጎ ወጥተን በሌሎች ጫማ ውስጥ ሆነን ነገሮችን ማየት ስንጀምር ሌሎችን እንዴት መቀየር እንደምንችል በተግባር የሚያሳይ ድንቅ ዶክመንተሪ ነው!! ከልብ እናመሰግናለን አቶ አሸናፊ!!
@onlinemarket5573
@onlinemarket5573 4 месяца назад
አሸ ዘመንህ ይባርክ
@sarajosh7261
@sarajosh7261 4 месяца назад
Wowww,, I really appreciate this family . It really is the pattern. I am deeply sorry for this family. Yes most of us. Most Ethiopian households go through similar pattern .
@Carmp1227
@Carmp1227 4 месяца назад
አሼ thankyou ትምህርቶችህ ሕይወትን ይለዉጣሉ
@endaleteshome5550
@endaleteshome5550 4 месяца назад
በመጀመሪያ እቶ እሼን እና ፍቃደኛ ሆነው ታሪካቸውን ላካፋሉን ቤተሰብ እጂግ በጣም እመሰግናለሁ !ታሪኩ በጣም አስተማሪ ነው የኔንም ቤተሰብ ወደሆላ ሄጄ አይቼበታለሁ በጣም ውስጤ ገብቶ የሚርብሽኝን ነገር መልስ አግኜቸበት በይቅርታ የውስጥ ሰላሜን አግኝቸበታለሁ ። እግዚአብሔር ይስጥልን ! ለሌሎችም ስለሚጠቅም የዚህ አይነት የተግባር ማማከሩ ቢቀጥል እላለሁ
@SelamSemaw
@SelamSemaw 4 месяца назад
በእውነት አዋቂ ነህ ብዙዎች ፀበል እየተንከራተቱ ነው አንተግን በአጭሩ ቀጨኀው
@kinamule8062
@kinamule8062 4 месяца назад
እግዚአብሔር ይመስገን። ተባረኩ
@melkamethiopiawit6584
@melkamethiopiawit6584 4 месяца назад
Am Ethiopian from canada. Dear Ashenafi Taye, you changed my life completely ! Hope you reach out and touch many people ! God sent you to do this and only this ! When I come to addis definitely will attend your seminar all my stay in addis. Am trying to make my Mom to watches your videos too. We all need to heal together. I I can’t thank you enough!!!!!
@genetfeleke4366
@genetfeleke4366 4 месяца назад
አቶ አሸናፊ ጣም የተለየ ሰዉ ነህ ድንቅ ሰዉ ነህ 🎉እንደዚህ ያሉ ችግሮች አለ። ግን የተለያየ ሥም እየሰጠ ነዉ ባለ ማወቅ ተሸክመን ኖሮላን አሁን ግን ብዙተረድቼለሁ አመስግናለሁ። 🙏❤️
@fentaneshereta842
@fentaneshereta842 3 месяца назад
አስተማሪ እና ልብ ነኪ ታሪክ
@Ritta_Ritta
@Ritta_Ritta 4 месяца назад
እግዚአብሄር ይባርክህ አቶ አሸናፊ ከዚህ በላይ ለብዙዎች መፍትሄ ያድርግህ❤❤❤❤
@Davidsoftware1943
@Davidsoftware1943 4 месяца назад
ትልቅ ሰው Respect🙏
@eshetetube8790
@eshetetube8790 4 месяца назад
ዋው አሼ እግዚአብሔር ይስጥህ ከዚህ በበለጠ እንድትሰራ እግዚአብሔር ይስጥህ በጣም ደስ የሚል ውጤታማ እግዚአብሔርን የሚወደው እና የሚፈልገው ሥራነው እየሠራህነው አመሰግናለሁ አከብርሃለሁ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🍇🍇🍇🏕🏕🇪🇷🇪🇷🍐🏕🇪🇹
@Lukulogy.
@Lukulogy. 4 месяца назад
አሼ እግዚአብሔር ይባርክ! ሁሉም ሴሚናሮችህን እከታተላለሁ በወስጡ ሁሌም እራሴን አያለሁ በዚም የተነሳ ሕልምንም አግንቻለሁ 🤏 (projecte) ጀምሪያለሁ ዛሬ ግን የተለየ ስሜት በውስጤ ተፈጠረ የራሴን ቤተሰብ ታሪክ የማይ መሰለኝ አናቴንና አባቴን ብትሸመግልልኝ ብዬ ተመኘሁ አንድ ቀን መጥቼ ታረኬ እንደማገራ እርግጠኛ ነኝ I wanna to say Thanks for your special seminar and amazing documentary
@abrihamsime2437
@abrihamsime2437 4 месяца назад
በጣም በጣም የሚደንቅ ተግባር ነው የሰራኸው አሼ ለእኛም ጥሩ ትምህርትና ተሞክሮ ነው የሚሠጠው እናመሰግናለን በረታ!!!
@user-qn3gm4pv5m
@user-qn3gm4pv5m 4 месяца назад
ይገርማል አብት ብቻ ሳይሆን ትዳርም ከቤተሰብ ይወረሳል ለካ 😢😢 አሼ በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው ተባረም ረዝም እድሜ ይጥክ❤❤
@itcanbe2114
@itcanbe2114 4 месяца назад
I can't stop my tears... Allah bless you and your family our herooo ashe 🙏🙏🙏
@abebeAmero
@abebeAmero 4 месяца назад
አሸ እግዚያብሄ ጤና ሰላም ፍቅር በረከት እረጅም እድሜ ይስጥህ
@addisabebayehu9918
@addisabebayehu9918 4 месяца назад
ትልቅ አክብሮት አለኝ ላንተ አቶ አሸናፊ! ነገሮችን ከሀ-ፐ እንድናያቸው ነው ያደረከው። ሰው ፕሮግራሙን እንደሚኖር ሳውቅ ሰዎችን መቀየም ትቻለሁ። ያንን በተግባር ስላሳየኸን እናመሰግናለን።
@user-qo5ys1td4m
@user-qo5ys1td4m 4 месяца назад
Eseyý Ekuan Des Alachihu Ato Ashe Ate Betam Diq Memiherechin Nek FETARI Bestegalay Stega Mogosinim Yederebilik Ameeen 🎉🎉🎉❤❤❤❤
@betyzmelos4657
@betyzmelos4657 4 месяца назад
አለም ጸሃይ እንዲ አይጻፍምx ዓለም ፀሐይ 👍
@OrthodoxTewahedoForever
@OrthodoxTewahedoForever 4 месяца назад
እግዚአብሔር እረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን።
@samuelmenkir7181
@samuelmenkir7181 4 месяца назад
እጅግ በጣም የሚገርም ታሪክ ነውና በጣም ብዙ ተምረንበታል
@wondyetariku
@wondyetariku 4 месяца назад
በጣም ጥልቅ የሆነ ትንታኔ ነው አሼ በእውነት ገራሚ ነው ብቻ መፍረድ እንዴት ቀላል እንደሆነና ከመፍቴሄ ይልቅ ፍረጃ እንዴት እንዴት እንደሚቀል ከዚህ ስለ መሻሻል ከማሰብ ይልቅ የሚያግባቡንን ከማሰብ ብይን ላይ እንዴት እንደምናተኩር አይቼበታለሁ
@semiragursha9330
@semiragursha9330 4 месяца назад
I wish hulum shimgelinawocachin endi kusil tefewawso bihon.... betam amesegnalew ato ashenafi rejim edmena tena emegilehalew...betesbochunm enamesegnalen
@habeshamitad
@habeshamitad 4 месяца назад
አሼ እግዛብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ።
@fikertbiruke4293
@fikertbiruke4293 4 месяца назад
ምን እንደምል አላቅም ግን ስሰማዉ በጣም ደንግጭለሁ የራሴ ዉስብስብ ታሪክ ይታየኛል የራሴ ፓተርን ለመስራት እ/ር ይርዳኝ!! አቶ አሼ ፈጣሪ ይስጥህ ተባረክ ሌላ ምንም አላልም!!
@tritiism
@tritiism 4 месяца назад
በጣም ቅን ቤተሰብ ናችሁ። ችግሩ ሲነገረው defensive ሳይሆን ልቡን ከፍቶ ለመፍትሔ ተባባሪ መሆን ለብዙ ሰው እና ቤተሰብ ቀላል የሚሆን አይመስለኝም። እግዚአብሔር በፍቅር ያቆያቸሁ።
@roberatube_6922
@roberatube_6922 4 месяца назад
እጅግ እጅግ በጣም የሚገርም😭😭😭😭ይህን ሁሉም ሰው ማየት ብችል ጥሩ ነው❤ Looonnngggg life❤
@yohannesdegarege4339
@yohannesdegarege4339 4 месяца назад
መምህር አሸናፊ : ገና ነው : ብዙ ስራ አለብህ። እናመሰግናለን🙏🙏🙏
@mesfingetachew2012
@mesfingetachew2012 4 месяца назад
🎉በእውነት አስደሳች ፈውስ ነው ለሰው ሁሉ የሚሰራ ይሁን!
@semiraweleyewa3586
@semiraweleyewa3586 4 месяца назад
በጣም እሚገርምና በጣም ግንዛቤያችንን እሚጨምር አሪፍ ና አሥተማሪ ታሪክ ነዉ መፍቻዉ መንድ ደግሞ ጥልቅ እዉቀት ይሰጣል። አመሰግናለሁ
Далее
Спецэффекты в Симс 4
00:36
Просмотров 35 тыс.
Gere emun part 185 | ገሬ እሙን ክፋል 185
38:28