Тёмный

💐ክፍል አራት  

Maedot @tube ማዕዶት ቲዩብ
Подписаться 766
Просмотров 236
50% 1

• ሙሉውን ነገ ሦስት ሰአት ይጠብቁን ...
💐ክፍል አራት #የት_ተወለደ የመጨረሻው ክፍል አራት #subscribe #comment ‎@Maedottube2730 #ማዕዶት_ቲዩብ #maedot_@tube
• ሙሉውን ነገ ሦስት ሰአት ይጠብቁን ...
🔴የት ተወለደ??
ክፍል አራት(፬)
የመጨረሻው ክፍል።
በከብቶቹ ጋጣ የተኛው ንጉስ
የት ተወለደ እኛን ሊፈውስ
የሐጢያትን ቁስል ደምስሶ ሰላምን ሲያለብስ
ሰው ሆኖ ተገኘ ክርስቶስ እየሱስ
ጌታ ሲሆን ንጉስ
ማረፊያ አላገኘም በምድር ሲመላለስ
በፈጠረው ምድር ነፈጉት ማረፊያ
በከብቶቹ ግርግም በፍቅር የተኛ
አዳምን ሊመልስ መልካሙ እረኛ
የነገስታት ንጉስ የሁሉ ፈጣሪ
የት ተወለደ ሠውን በጁ ሰሪ
ቃል ሥጋን ሲለብስ ሰው ሆነው አባራሪ
የእውነትን ጌታ በማለት ሀሰት ተናጋሪ
አቤት ደግነት አቤት ርህሬሄ
በፈጠረው ምድር ማረፊያ ያጣው ጌታዬ
የት ተወለደ ተብዬ
ጥያቄውን ስመልስ ተሰዶ የሆነኝ መሸሸጊያዬ
ሄሮድስ ያሳደደው ፈጣሪ ነው አምላኬ
ማረፊያ ያላገኘው ከድንግል ተወለደ
ሁሉን የፈጠረ ማረፊያ አጥቶ ተሰደደ
በበረሃ ንዳድ ወደግብፅ ሄደ
ዓለምን በመዳፉ ይዞ በእግሩ ተራመደ
የፍቅር የሰላም ንጉስ ይሄ ጌታ የት ተወለደ???
እስራኤል ቢወለድ ኢትዮጵያ
ኢሲያ ቢሆን አውሮፓ
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ምን አለው መለኪያ
የአዳምን ልጅ በእጁ የሰራ የለውም አምሳያ
ጠበን ያጠበብነው የሁሉን መጋቢ
የት ተወለደ እያልን መስለን የእውነት አሳቢ
እሱ የሌለበት አይገኝም ስፍራ
ረቂቅ አምላክ ነው ሁሉንም የሰራ
የሁሉ ገዢ ለፈጠረው የሚራራ
በዚህ ፍቅር ተሰርተን ተከተትን በጎጠኞች ጎተራ
የት ተወለደ ተባለ በሥጋ ተገልጦ ቢመጣ
በጎቹን ሰብስቦ ሊመልስ ወደ ጋጣ
በምህረት ወደኛ ሲመጣ
በብሔር ልንከፍለው እውነት እንዲጠፋ
ለምን ለምን ተጣደፍን በምድራዊ ተስፋ
በቋንቋ ልንከፍለው ጠበን ስንሰፋ
ክፋታችን በዝቶ እኛን ሳያጠፋ
ምህረት የሚሰጥ ማነው እየተገፋ
ይቅር የሚል ተሰቅሎ እየጠፋ
በፈጠረው እጅ በጥፊ ተመቶ
ምራቅ ተተፍቶበት ብረሃን አብርቶ
ይቅር ባይ አይኖርም እንደ ጌታ ከቶ
የት ተወለደ ተብሎ ስሙን በብሄር አንስቶ
የተማረ ሙሁር ያልተማረን በልቶ
ወንጌልን ሊበርዝ በዘር ቋንቋ ከቶ
ምን አይነት ፍጡር ነው የጠፋ
ምህረት የሚሸጥ በጨለማ ተስፋ
ብረሃን አጦፍቶ ጨለማ ሚያሰፋ
ክርስቶስ ረቂቅ የሁሉ ፈጣሪ
ሁሉንም በጊዜ ውብ አድርጎ ሰሪ
ሰው እውነት ቀባሪ
አምላክ ብረሃንን አብሪ
የት ተወለደ ተባለ ሁሉንም ሰሪ
🌹ግንቦት 13/2016
🇨🇬"ተፃፈ በትንሹ ብላቴና መምህር ገብረፃዲቅ።

Опубликовано:

 

2 июн 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 13   
@Zemarittadelche
@Zemarittadelche 7 дней назад
አሜን
@user-yr8gw8hq4b
@user-yr8gw8hq4b 24 дня назад
አሜን አሜን አሜን
@user-zt6qs6qw1w
@user-zt6qs6qw1w 23 дня назад
አሜን አሜን መምህር እግዚሀብሆር ይታረቀን
@Hannah-fs8xv
@Hannah-fs8xv 24 дня назад
አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤
@sahayEtho
@sahayEtho 24 дня назад
ቃለ ሕይዎት ያሰማልን መምህር እሰግድልሃለሁ አመሰግንሃለሁ💚💛💝💞
@zinashgedamu1223
@zinashgedamu1223 23 дня назад
እግዚአብሔር ይመሥገን መምህር ፀጋዉን ያብዛልህ❤❤❤
@mkedesethiopianttc9157
@mkedesethiopianttc9157 25 дней назад
🙏🙏🙏🙏🙏🙏 አሜን አሜን አሜን
@ABdulAziz-rn3kf
@ABdulAziz-rn3kf 24 дня назад
ሰላም ሰላም መምህር ሰላምህ ብዝት ትርፍ ይበል አገራችንን ሰላም ያርግልን
@slmonLima
@slmonLima 25 дней назад
እሰግድልሃለው እሰግድልሃለው ዝማሬ መላእክት ያሰማልን 🇨🇬✍️🌹💚💚💚☑️🇨🇬 የትተወለደ የሚለውን ግጥም ላቀረበልን ለወንድማችን ለመምህራችን ቃለህይወት ያሰማልን ያገልግሎት ዘመኑን አምላከ ቅዱሳን ይባርክልን💚☑️🇨🇬🌹💚💚✍️🌹💚☑️🇨🇬🇨🇬🇨🇬🇨🇬
@hao90
@hao90 25 дней назад
ሰላም እግዚአብሔር ይሰገን ለሁላችንም በእውነት መምህር ቃለ ሕይወት ቃለ በረከት ያሰማን እህታችን በእውነት ዝማሬ መላእክት ያሰማልን በረከታቸው ይደረሰን አሜን አሜን አሜን 🌹🕊🌹🕊🌹🕊🌹🕊🌹❤ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪ 🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
@Hannah-fs8xv
@Hannah-fs8xv 24 дня назад
አሜን
@user-lk9nx3qj6y
@user-lk9nx3qj6y 24 дня назад
አሜን አሜን አሜን❤❤❤❤
@user-jr3hg4ck7m
@user-jr3hg4ck7m 24 дня назад
አሜን አሜን አሜን❤❤❤
Далее