Тёмный

🛑 ምስባክ ዘወረደ- ተቀነዩ ለእግዚአብሔር - በአባ ገብርኤል 

ተምሮ ሚዲያ - Temro Media
Подписаться 32 тыс.
Просмотров 325
50% 1

ዘወረደ (፩ኛ ሳምንት)
እንኳን ለተወዳጁ ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችኹ አደረሰን!!!
ዐቢይ ጾም ማለት ፡-የአጿማት ሁሉ የበላይ ወይም ጉልላት ማለት ነው፡፡ ይህም እጸድቅ አይል ጻድቅ እቀደስ አይል ቅዱስ የሆነ አምላክ ሰውን ለማዳን ሰው ከሆነ በኋላ “በበሕቅ ልሕቀ” እንደተባለ በየጥቂቱ አድጎ የገድል ሁሉ መጀመሪያ(ጥንት) የሆነችውን ጾም ስለጾመ ነው፡፡ “ከእኔ ተማሩ” እንዳለም ፈለጉን በመከተል እንጾማለን (ማቴ፲፩፥፳፱/11፥29)፡፡ በዚህ ታላቅ ጾም ውስጥም ፰(ስምንት) ዓበይት ሳምንታት አሉ፡፡ እነዚህም ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ መጻጉዕ፣ ደብረ ዘይት፣ ገብረርኄር፣ ኒቆዲሞስ እና ሆሳዕና በመባል ይታወቃል፡፡
ዘወረደ ፡- ማለት በባሕርዩ ከላይ ያለውን ለማውረድ መንጠራራት፤ ከታች ያለውን ለማንሣት ጎንበስ ማለት የሌለበት እና ሁሉ በመዳፉ የተያዘለት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ዘሩን ሊያድን ከሰማይ ወርዶ ከድንግል ማርያም ስለተወለደ ነው፡፡ እኛም ዘወረደ ብለን ስንጾም ቀጥለን የጌታን ጾም ለመጾም እየተዘጋጀን እንደመሆኑ መጠን፤ ተጠመቀ፣ጾመ፣ተሰቀለ፣መከራ ተቀበለ፣ሞተ፣በመከራውም አዳነን ለሚለው ሁሉ “ወረደ፣ተወለደ” የሚለው ጥንቱ ነውና ከጌታ ጾም በፊት ያለውን ሳምንት ዘወረደ በማለት መወለድንና የተወለደበትን ዓላማ እንዘክራለን ፡፡ በዚህ ሳምንትም የጌታን ሰው መሆን እንማርበታለን፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን በቅዳሴው የሚነበበው ወንጌልም ይህን ያስረዳናል፡፡ ፟፟ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ፥እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡(ዮሐ ፫፥፲፫/3፥13)፡፡
ይህ ቃለ ንባብ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ታላቅ ምስጢርን የያዘ ነው፡፡ ከትርጓሜውም አንዱን ብንመለከት መለኮት ሰውን ለማዳን ትሑት ሆኖ ሰው መሆኑን፤ ትሑት የሆነው(ምንም ያልነበረው) ሰውም የጸጋ አምላክነትን ማግኘቱ፤ይህም ድንቅ ነገር በማኅፀነ ቅድስት ድንግል ማርያም ነው የተጀመረው፡፡
• ዘወረደ የጾሙ መጀመሪያ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ለድኅነተ ዓለም ከልዕልና ወርዶ ትሑት ሆኖል /ምስጢረ ሥጋዌን ፈጽሟል/ ይህች ጾም የሥራ ሁሉ መጀመሪያ ናትና ዘወረደ ተብላ ትጠራለች፡፡
• በዚህ ሳምንትም ምእመናን ራሳቸውን ለጾም ለማዘጋጀት የሚጾሙት ጾም ነው፡፡ ምክንያት ከተባለ ጌታ የጾመው አርባ/፵/ቀን ነው፡፡ ስለ ክብረ ጾመ ጌታ ግን ዘወረደ እና ሰሙነ ሕማማት የተባሉት ሳምንታት እንደ መጋረጃ መክፈቻ እና መዝጊያ ተደርገው በሥርዓት ተሠርተው ተቀምጠዋል፡፡
• ከዚህ ሳምንት ጀምሮም ሰው በመለፍለፍ መውደቅን ስለአመጣ ረብም (ጥቅምም) ስለሌለው የመነኮሳት ክብር የሆነችውን አርምሞ ገንዘብ ያደርጋል፤ ጸናጽሉ ከበሮም ይሰቀላሉ/አይመቱም/ጊዜው የከበሮው እና የጸናጽሉ መጮህ ሳይሆን ሥጋ በጾም መጎሰም የሚጮኸው ጩኸት ስለሆነ ይኸም የልቡና ቃለ እግዚአብሔር ማሰላሰል፣የከነፍር ነቢብ፣የጉልበት ፍሬ ሣርዓት የእጅ ምጽዋት ነው፡፡
ምክረ አበው
• እግዚአብሔርን እንዳይቆጣ ስንፍናን አስወግደን በትጋት ተግባረ ሥጋን ተግባረ ነፍስንም ይዞ መገኘት፡፡
• ሰው ያየውን፣ የሰማውንና የሚያውቀውን በእውነት መመስከር ይገባዋል፡፡
• ከጌታ በስተቀር ከሰማይ የመጣ፣ወደሰማይ በስልጣኑ የሚወጣ የለም፡፡
ምስባክ
ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሀት = ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ
ወተሐሰዩ ሎቱ በርዓድ = እርሱን በማምለክ ደስ ይበላችው
አፅንዕዋ ለጥበብ ከመኢይትመአዕ እግዚአብሔር፡፡ = እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን
አፅንታችው ያዙ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለመ ዓለም አሜን!!!

Развлечения

Опубликовано:

 

8 мар 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 4   
@meazagashuchaksa6514
@meazagashuchaksa6514 3 месяца назад
እንኳን አደረሶት አባታችን ቃለህይወት ያሰማልን
@jhongebre2774
@jhongebre2774 3 месяца назад
ዝማሬ መላእክት ያሰማልን አባታችን🙏🙏🙏
@sisayabebe0912
@sisayabebe0912 27 дней назад
ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን::
@zedishakonjo7985
@zedishakonjo7985 3 месяца назад
🙏🙏🙏
Далее
የሰኔ ጎልጎታ
25:14
Просмотров 2 млн