Тёмный
No video :(

Ethiopia 

Ethioemma Tube
Подписаться 11 тыс.
Просмотров 4,8 тыс.
50% 1

ደራሲ በአሉ ግርማ ካበረከተልን መፅሀፍት "ደራሲው" የተሰኘውን በተከታታይ እናቀርባለን።
ተራኪዎች አንተነህ አስረስ፣ብሌን ሳሙኤል፣ቤርሳቤህ ፈረደና ሌሎችም።
የደራሲ በአሉ ግርማ ክህሎት በእኛ የሚለካ ባይሆንም በተቻለን አቅም ክብር ሰተን ለመተረክ ሞክርነዋል።
አንተ የጥበብ ልጅ ሆይ ነብስህ በሰላም ትረፍ
Ethioemma tube march 2022.
/ musicbyscottb

Опубликовано:

 

28 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 23   
@merongedlu8929
@merongedlu8929 2 года назад
ሰላም ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው ።ስብሀት እና በአሉን የመሳሰሉትን እንቁ ደራሲያን የስሜት ስቃይያቸውን እየተጋራሁ፣ የልጅነቴን ድባብ እያስታወስኩ ፣በተራኪያኑ ቅንብር እና ብቃት እየተደመምኩ፣በጀርባ ሙዚቃዎቹ እየተዝናናሁ እና ሌላም ብዙ ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማኝ።በወጣትነት ዘመኔ ያነበብኩት መፅሀፍ ቢሆንም ግን እንደአዲስ ቀልቤን ሰጥቼ እያደመጥኩ ነው። አንተነህ ባጋጣሚ ለኔ በአንደኛ ደረጃ ከማስቀምጣቸው ተዋንያን መሀል ነህ በዚ መልኩ ሳገኝህ ደሞ በጣም ደስ አለኝ።የልዮ ሰርሳሪ ድምፅ ባለቤት ነህ። ስማቸውን አሁን በደንብ አልያዝኩትም እንጂ የሁለቱ ሴቶች ድምፅ እና ብቃት ከየት ነው የመጡት አስብሎኛል። ሰብለን የምትርከዋ እህቴ መረቅን ስትተርክ አድምጬ ልቤ ውስጥ ቀርታለች። ሁላችሁም ጎበዞች ናችሁ በርቱ እናመሰግናለን በበኩሌ ሰብስክራይብ አድርጌያለሁ።
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
መልካም አድማጭ ባገኘን ቁጥር ጉልበታችን ይጨምራል ።ክብረት ይስጥልን
@ambaw1004
@ambaw1004 2 года назад
እንባ እንባ ይለኛል ፣ ይተናነቀኛል ••••• እንባ የትአባቱ ፣ ደርቋል ከረጢቱ፤ ሳቅ ሣቅም ይለኛል ሥቆ ላይስቅ ጥርሴ፤ ስቃ እየነደደች መከረኛ ነፍሤ ፤ ✍🏿 በዓሉ ግርማ የመጨረሻዎቹ ቃሎች በመጽሐፉ የከተባቸው ፤ ድንቅ የኪነት ሠዉ ፤ አቤት ገጸ ባህሪን መዉለድ መፍጠር ሢችልበት
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
አምብሼ ቅነትህ ሁሌም ከእኔ ጋር ነው ለዚህ ስራ የማእዘን ራሱ ነህ።ክበርልኝ
@ambaw1004
@ambaw1004 2 года назад
@@ethioemmatube አመሰግናለሁ ወዳጄ ልቤ፤ እናንተ ሥለተረካችሁት የበዓሉ ግርማ ነፍሥ ተደስታለች እኔንም ጨምሮ
@solomonhailu8131
@solomonhailu8131 2 года назад
Konjo tireka tanks
@fasikafiseha7958
@fasikafiseha7958 7 дней назад
እየገሰገስኩ ነው
@meazabeza2806
@meazabeza2806 2 года назад
ደስ የሚል አተራረክ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ 🙏
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
ክብረት ይስጥልን
@thegestthegest6080
@thegestthegest6080 2 года назад
Waw Tnx
@etshuncho2673
@etshuncho2673 Год назад
bea ethiopia tarik endazih ayneat atrarke aychea alawkem betam ymgemi new endazih onachiew lelochem mtsehaft trkulen
@ethioemmatube
@ethioemmatube Год назад
thankyou
@chagnimediaoffical
@chagnimediaoffical 2 года назад
ደራሲው ክፍል 5 እጅግ ከፍ ብሎ ተሰርቶና ተቀምሞ ደርሷል፡፡ እነ አንትሽ ዛሬ ደግሞ ገራሚ ሁናችሁ እና ተክተክ ብላችሁ መጣችኋል፡፡ “ወይ አራዳ…አራዳ….!” የድሮ የኢትቪ ቆየት ያሉ አርካይቭማ አላችሁ ሆ….. አቤት የድምጽ ግብዓት ብዛት፣ጥራት እና ተገቢ ስፍራ ሲሆን ይጥማል! እንደተከታታይ ድራሚ(ፊልም) እኮመኩም ጀምሬአለሁ! አስተያት ለመስጠት አይደለም የምመጣው የምሬን ደስ ብሎኝ ሰምቼ እና ተደንቄ እከታተላለሁ! እረ ተራኪያን ተሰብሰቡና እንደ ደራሲው ያለ ድንቅ ስራ እንስራ…ወይኔ ትወና እና በወኔ መስራት…..የእናት ሃገር ወይ ሞት…..የጦርነቱ ድባብ ገራሚ ነው….. “ይህ ስራ የጋሽ ስብሃትን ህይወት ነው የጻፈው የሚል በርካታ ቅብብሎሽ ቢኖርም ግን ሲራክ ግን የስብሃትና የበዓሉ ድብልቅ ነው…በአመዛኙ እንደውም በዓሉ ነው ባይ ነኝ!....
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
ወዳጄ ሰውዬው በአሉ ነዋ።እኛ ከተረክንበት ሽራፊ ጥበብ ይልቅ የእሱ ብአር ትገርማለች ፣ከቆሻሻ መሀል ውበት የምታይበት መለኮታዊ ብሌን አላት።ክህሎቱ ኖሮን ከዚህም በላይ በኳልነው
@ambaw1004
@ambaw1004 2 года назад
አማኑዬ ፤ መውደድ አሞራ ነዉ ያርፋል የትም ቦታ እንዲሉ፤ ይህ ደራሲው የተሰኘውን የበዓሉ ግርማ ሥራ እና የነ አንትሽ ወኔ የተመላበት ትወና ወ ትረካ አስደምሞኛል ( ወድጄዋለሁ ) ፤ አማኑዬ ልክ ብለሀል እኔም መጽሐፉን በማደምጥበት ግዜ ሢራክ ( ጋሽ ስብሀት ገ / እግዚአብሔር ) ን ሣይሆን ፤ እንደዉም የበዓሉ ግርማ አሥተሳሰብ እና ዕይታ ሚዛኑ ይደፋብኛል፤ ጋሽ ስብሐት እኮ ሲከትብ እንጂ ሲያወራ አንድ አረፍተ ነገርን ለመግልጽ ሲያሽሞነሙን ሰዓታት ያልፋሉ፤ እና እኔ ከ 10 % ውስጥ 4% ለ ጋሽ ስብሀት ብሰጥ 6% የሲራክ ዕሳቤ እና ምልከታ የራሱ የከያኒዉ የበዓሉ ግርማ ይመስለኛል
@khalidosman3894
@khalidosman3894 2 года назад
Part 6🙏
@thegestthegest6080
@thegestthegest6080 2 года назад
Part 6 please
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
Soon
@keludifamilyshow
@keludifamilyshow 2 года назад
የማይዋጥልኝ ሀቅ!!ነበር ከታሪክነት በዘለለ ለዛሬና ለነገ ቅንጣት ለውጥ አያመጣም የሚባል ብሂልን የሚከተል ሠው የመሠጠኝ ፅሁፍ……………… ከበእውቀቱ ስዩም ድሮና ዘንድሮ ጋዜጠኛ፦ቁርስህን ምን በላህ? ወጋየሁ ንጋቱ፦ዱለት ጋዜጠኛ፦የልብስ ምርጫህ? ወጋየሁ፦ቢትልስ ሹራብ ጋዜጠኛ፦በትርፍ ጊዜህ ምን ያዝናናሃል? ወጋየሁ፦ካርታ ጨዋታ … ተፈፀመ… ዘንድሮ ጋዜጠኛ፦ቁርስህን ምን በላህ? አርቲስት፦ ያው እንግዲህ ሠው ሆነን ስንፈጠር ሰውነታችን እንደ ሰውነት ምግብ መጠየቁ አይቀርም አርቲስት ደግሞ እንደ ማንኛውም ሠው ምግብ ያስፈልገዋል ምን ልልህ ፈልጌ ነውለኔ ቁም ነገሩ ለምግብ መኖር ሳይሆንለህዝብ መኖር ነው ህዝቡ የሚጠብቅብህን ነገር ካበረከትክ ቀኑን ሙሉ ባትበላ እንኳን የረሃብ ስሜት አይሠማህም ወደ ጥያቄህ ስመጣ ቁርሴን የበላሁትበቅርቡ የሚዳሰስና የሚቀመስ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ጨጨብሳ ነው። ጋዜጠኛ፦የልብስ ምርጫህ? አርቲስት፦እንግዲህ ሁላችንም ወደዚህ ምድር ራቁታችንን ነው የመጣነው ራቁታችንን ሆነን ይህችን ምድር እንለቃለን……እያለ ይቀጥላል🤔 📌 ዘመን ያዘምናል ለሚሉ ትልቅ ማሳያ በድሮ በሬ ማን አረሠ ዝማኔ፣በአሁንና ፣በነገ ውስጥ ብቻ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ለደረሡት ትልቅ ምስክር ትናንት ለዛሬ ምሶሶ መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳየን ዛሬም ላይ ሆነን ሳንፈጠር የነበረውን መስታወት ሆኖ ያስቃኘን ድባብ ብዙ በመደመም ውስጥ ትርጉም ያለው እውቀት እንዲኖረን የሆንበት ወርቃማ ጥበብ በዓሉ ግርማ እና የሞያ አጋሮቹ በድሮ ውስጥ ትልቅ ዝማኔን ተሰጥኦን የተጎናፀፉ እውነት ቃል የለኝም። አንተነህ ወንድሜ ሁሌም ሀሳቤን ለማስፈር ስገባ ካላመሠገንኩህ ጥበብ ትወቅሠኛለች።ክፍል አራትን በሠብለና በሲራክ ምልሠትና ኩነት በክፍል አምስት ድባቧን በምወዳት የነሲራክ ሠፈር የሼኩና የሲራክ የፅግሽ ጥቁር ዶሮ😂የጦርሜዳው ድባብ ኸረ ስንቱ የጉድ ነው መሳጭ እናም ለኔ ድሮ ነበር ብቻ አይደለም ነገም ነው።
@ethioemmatube
@ethioemmatube 2 года назад
ጥኡም ኮመንት ነው የበእውቀቱ የምር ነው ያሳቀኝ በድጋሚ ክብረት ይስጥልን ።እንዲህ የነጠረ አድማጭ ማግኘት እንዴት ነብስ ያለመልማል መሰለሽ በድጋሚ እጅ እንነሳለን
@ambaw1004
@ambaw1004 2 года назад
ከሉዲአችን የኛ የሁላችን ፤ ንግግርሽ መጽሐፍ ነው አይጠገብም፤ ጥሩ ወግ አቅምሰሽናል ፤ በነገራችን ላይ ታውቂ ይሆን አላውቅም ? ደራሲዉ የተሰኘዉ መጽሐፍ ሥለ ጋሽ ስብሐት ገ/ እግዚአብሔር ( ደራሲ ) እንዲያጠነጥን አድርጎ በዓሉ ግርማ የከተበዉ ነበር፤ ቢሆንም በዉስጡ ያለው ሀሳብ ግን የስብአት ስብዕና በከፊል የበዓሉንም አሳይቶኛል ፤
@keludifamilyshow
@keludifamilyshow 2 года назад
@@ambaw1004 አዎ አምብዬ ፍንጭአለኝ እንዳልከውም ስስለው የጋሽ ስብሀት ስብእና ይታያል የገረመኝ የሲራክ የጥበብ ዛር ቁንጥንጥነት ከጋሽ ስብሀት ስብእና ጋር ይጣመራል ሌላው ደግሞ አዛኝና ሩህሩህ ልብ ያለው ቸር መሆኑ ነው ከዛ ውጪ ግን ብዙ የበአሉን እምቅ አመለካከት የያዘ ይመስለኛል
@ambaw1004
@ambaw1004 2 года назад
@@keludifamilyshow ልክክ ያለዉን ልክ ብለሻል ከሉዲአችን ፤ መዉደድ አሞራ ነው ያርፋል የትም ቦታ እንዲሉ ይህንን መጽሐፍ አለመውደድ አይቻልም ፤ ድንቅ ነው ሥለዕውነት፤
Далее
ዶን ኪቮቴ  ክፍል1 Don Quixote Part1
2:54:28
Просмотров 10 тыс.
New Dyna Skin is OP🥵🔥 | Brawl Stars
00:16
Просмотров 303 тыс.