Тёмный

Hama Tuma: Finote Democracy "ኢሕአፓ" ከአቶ ኢያሱ ዓለማየሁ የኢሕአፓ መስራችና የከፍተኛ አመራር አባል ጋር የተደረገ ውይይት ክፍል ሁለት 

Finote Democracy ፍኖተ ርዕይ
Подписаться 5 тыс.
Просмотров 5 тыс.
50% 1

👉👉👉Ethiopia:❤️💛💚 www.finote.org
www.eprp.com

Опубликовано:

 

27 сен 2018

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 14   
@nadewumekonnenteklearegawi2540
የኢሕአፓ አባላት ሆነው በቀይ ሽብር ለሞቱት ሁል ግዜም አዝናለሁ!ኢህአፓም ቃታ ስቦ ለገደላቸውም እንደዚሁ!ከሁለቱም ወገን የተገደሉትን የኢትዮጵያዊያን ሬሳ በወቅቱ አየተረማመድኩ ለመማር በመገደዴም ያ ግዜ ለእኔ የማይረሳ ዘግናኝ ወቅት ነው። የምወዳቸውን ዘመዶቼንና የአደግሁበትን የሰፈሬን ወጣቶች ሬሳ እንደ ውሻ ሬሳ ጎዳና ላይ ወድቆ በማየቴ።ለምን ይህ ሀሉ አሰቃቂ ነገር እንደተፈጠረ ለእኔ ግልጽ አይደለም። የሚገርመው ነገር በጠላትነት ተፈራርጀው ሰይፍ ተማዘው የተጨራረሱት ወገኖች የሚያስቡት የሚመሩበት ideology ተመሳሳይ ነበር።ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ተናገሩት እንጂ እኛም ድሮ የምንለውና የምንገረምበት ነገር ነበር። ምሳሌ ለመጥቀስ ደርግ እናሸንፋለንና ወዝአደር ሲል ኢህአፓ ደግሞ እናቸንፋለን እና ላብአደር ይል ነበር።ህወአቶች ዛሬም ድረስ ላብአደር ነው የሚሉት።ሌላው ጸብ Ideologicaly ይስማሙና አንደኛው ቡድን ትግሉ ከከተማ ወደ ገጠር መጀመር አለበት ሲል አንደኛው ትግሉ ከገጠር ወደ ከተማ መሆን አለበት በማለቱ ነፍጥ አንስተው ተጨራርሰዋል።በቀላል ምሳሌ ለመጥቀስ አንድ ሰው እንዲሞት ተስማምተው መሞት ያለበት በጠብመንጃ ነው አይደለም በገመድ ታንቆ ነው መሞት ያለበት ብለው በአፈጻጸም ላይ ተጣልተው ገዳዮቹ እራሳቸው እርስ በእርስ እንደመጨራረስ ማለት ነው። የሚያሳዝነው ነገር እነዚህ የተገደሉ ሰዎች መሬት ላራሹ ብለው የጮሁለትም ገበሬ ከድህነት ላይወጣ የእነርሱ ሕይወት በከንቱ መጥፋቱ ነው።በተቃራኒው ስራ የሚፈጥረውን ሀብታም አውድሞ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ አደኸየው እንጂ።አሁንም ያለፈበት፣ለብዙ ንጹሃን ዜጎች ባልገባቸው ጉዳይ ለሕይወታቸው መጥፋት ምክንያት የሆነውን አብዮት የሚል ስም ያካተተ የፓርቲ መጠርያ ይዞ ሌሎች ተመሳሳይ አብዮተኞችን መውቀስ ለእኔ አድካሚ ነገር ነው።በእነዚህ አርባ አመታት ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል።ኮሚዩኒዝም ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ላይነሳ ወደ መቃብር ሄዷል።አሁን አቶ እያሱ የኮሚዩኒዝምን ተዝካርና ሙት አመት በግሎ እያከበሩ እንደ እርሶ የሚያስቡትን እየተቹ እኔ ከእነርሱ የተለየሁ ነኝ ብለው የሚያስቡ ከሆነ የተሳሳቱ ይመስለኛል።ሌላው ቢያንስ እንደ ልብዎ እንዲናገሩ ሕይወቶትንም እንደ እርስዎ ተመሳሳይ አስተሳስብ ካላቸው ነገር ግን ሊገድልዎት ከሚፈልጉት ጠላቶቾ ታድጋ ያኖረቾትን አሜሪካን ምክንያት በማያቀርቡበት መንገድ በጣላቻ መመልከት ከሞራል አኳያ ተገቢም አይመስለኝ።
@user-ne6zj5gj2e
@user-ne6zj5gj2e 9 месяцев назад
ታሪክ ተደብቆ አይቀርም።ለኢህአፓ ልጆችና ለፓርቲው መውደቅ እንዲህም መክሸፍና ለብዙዎች ሞት ተጠያቂዎቹ ሁለቱ ምስጦች ዘሩ ክህሽንና ኢያሱ አለማየኹ ናቸው።ሌሎቹ በእነዚህ ሁለት ሰዎች ሴራ የተታለሉ ናቸው።ከመሞቱ በፊት እውነቱን ይፅፈዋል ብዬ እገምታለሁ።
@herokeabusheher4415
@herokeabusheher4415 5 лет назад
ጋሽ አለማየው እወዶታለው
@Tefera-hf8fw
@Tefera-hf8fw 5 лет назад
Pls can u explain the use of ch and sh ? What is the secrecy??
@herokeabusheher4415
@herokeabusheher4415 5 лет назад
ይመስለኛል ኢሕአፓዎች "እናቸንፋለን" ሲሉ መኢሶን ደግሞ "እናሸንፋለን" ነው የሚሉት ይባላል። ዋናው ነጥብ ግን ጥሉ ቸ እና ሸ አይደለም!!አብይ ደንቆሮ ስለሆነ ለወሬ ማጣፈጫ ሲል በደርግ ጊዜ የሚባለውን ነው ያንጸባረቀው
@JAsperEudaimonia
@JAsperEudaimonia 8 месяцев назад
A good analyst is judged by the success or failure of his predications. Mr Iyasu, is vindicated by what transpired in Ethiopia the last five years.
@aklilunegash2985
@aklilunegash2985 5 лет назад
ጓድ እያሱ ጄግና በተለይ ስለጄግናው በላይ(ኢያሱ አለማያሁ)ያስተማረንን ጥናት ይዘን እንታገላለን
@anteneh41
@anteneh41 5 лет назад
እያሱ ለማየው በምድር ላይ ምንም የማያረካህ ሰው ችግር አለህ አእምሮህ ላይ
@derejedejene9519
@derejedejene9519 5 лет назад
EPRP is the worst political group established by the Name of Ethiopia, even worse than TPLF. 1) Since its establishment EPRP resorted to and adhered to armed struggle using Eretria and Tigray as a base- which is a mechanism of killing as many poor Ethiopian serving in the national army to defend their nation. When become unsuccessful in the rural armed struggle, it launched a campaign of targeted assassinations in Addis Ababa and other major cities and killed a number of intellectuals, working class, students and even poor laborers. Armed struggle is not a means to kill the ruling class. EPRP struggle was not against colonial power, like the rest of African countries, it was initially against the ruling Aristocracy. EPRP struggle with Military (Derg) Government was not over the direction of the revolution, either. It was on the ownership of the revolution; i.e it was a power struggle. Therefore, armed struggle against fellow citizen was unjustified by any means. 2) From the beginning, EPRP programme was not to bring justice to the nation, but primary to dismantle the nation. It formally asks for cessation of Eretria and Ogaden, and self-determination of other nationalities. The cases of Eritrea and Ogaden were not colonization under any circumstances. But, if subjugation of these territories and other nationalities by the ruling Aristocracy was an issue, EPRP should have opted for different forms of government where justice and democracy prevail not asking for session of these territories from outset. 3) EPRP joined Mohamed Siad Barre of Somalia, merely for the sake of collecting firearms to kill their fellow citizens, especially poor Ethiopians serving the military government and the so-called members of MEISON (All Ethiopian Socialist Movement) who were of course their friends and comrades during student movement. 4) Although they pretend too much, EPRP was not inclusive of Nationalities in Ethiopia. Among the 9 Ethiopians participated on the founding congress of EPRP (then called EPRO) in West Berlin 3, were Oromos, but no one were including in the ‘central committee’ formed on the day of its formal establishment (April 1972). But all the Tigres on the meeting and one in absentia, 3 Amharas and one Gurage were named Central Committee. If it had been working on issues of nationalities how it exclude the Oromos from the leadership, why it had not brings in other nationalities, which it claimed as oppressed by ruling Amhara elite? Why not at least has one representative from the then regions (Teklay Gizat)? Moreover, those named themselves (call elected per-se) as members of the Politburo were basically Tigre (Berhan Meskel, Tefaye Debasay, Zeru Khishin and Eyasu Alemayehu). This signal, there is systematic exclusion of the Oromos, Amharas and other nationalities from the top leadership of EPRP from the onset of its formation. Therefore, using the name Ethiopia only as a cover for hidden agenda cannot grantee EPRP as the multi-nationalities party. 5) EPRP have never acknowledged a lot of reforms and progress made by Hailesillasie regime as well as radical policy measures taken by Military (Derg) Government including land reform. They bulkily labeled any one not on their way, including their members, Fascist, ‘Bandas’, enemy of the people and targeted for assassination. As Robert Putinam put it, ‘Development (social Transformation) is path dependent’; thus it cannot be brought about in one night. Therefore, after reading a number of books written in reference of EPRP, I concluded that, quite contrary to its claim, EPRP HAS NEVER STOOD FOR THE TRUTH, FOR JUSTICE, FOR DEMOCRACY. EPRP is a group of mafias, basically from Tigray origin, that consistently and courageously manipulated the innocent youth of Amhara, Gurage and members of other ethnic groups and let them kill their fellow citizens and killed by Cadres and Militia of the Military (Derg) Government. Although I was under 15 at that time, I always feel sad for those, including my close relatives, who lost their lives for hidden objective of EPRP which was unclear to them. I strongly feel that the whole (hidden) purpose of EPRP is to make Ethiopia a weak and vulnerable nation that cannot protect its national territory and eventually fall apart.
@user-iv8iz8fy3t
@user-iv8iz8fy3t 2 месяца назад
ሰማህ ወይ ግድ የለም ህዝብም ዴሞክራሲም መርህ ይሁን ለምን የትምህርት ሚኒስቴርን አርማ ተጠቀማችሁ የትግሬውስ ጦርሰፈር መጀመሪያ ተመረጠ?ውሸትም እውነትም እንደ ተቀቀባዩ ትክክል ነው።ኢህአፓን አንተ ታውቀዋለህ እኛም እናውቀዋለን።
@user-jj3nu9kf5f
@user-jj3nu9kf5f 5 лет назад
1ኛ፣ኢያሱ አለማየሁ በጋጠወጥ አነጋገር ሲናገር፣ በኢህአፓ ላይ፣ "ከአፄው" ጊዜ ጀምሮ ብዙ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ተካሂዶብናል፣ ብሎአል። መጀመሪያ በንጉሱ ዘመን ብዙ ፕሮፓጋንዳ አልነበረም። ፕሮፓጋንዳ የኮሚኒስቶችና (ለምሳሌ የኢህአፓ፣የመኢሶን የሀወሀት ወዘተርፈ ) የፋሺስቶች ዋና መሳሪያ ነበር። ኮሚኒስቶች በንጉሱ ላይ ፕሮፓጋንዳ ካደረጉና ንጉሱን ከጣሉ በሁዋላ፣ እርስ በራሳቸው በእናቸንፋለንና፣ በእናሸንፋለን ማለት ከመኢሶን፣ ከደርግ ጋ በሸና በቸ ተጣሉ። ይሄን ታሪክም ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው።ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሌቦችን የቀንጅቦች ብሎ፣በዛ ጊዜ የተጨራረሱትን ኮሚኒስቶች ምክንያቱ በሸና በቸ መሆኑን እንቀጩን ነገራቸው። ለዚህም ነው አቶ ኢያሱ በእልህ ለመናገር ሲጣጣሩ የሚታዩት። 2ኛ፣ አቶ አያሱ እንደሚሉት ከሆነ ኢህአፓ የሞተችው ለኢትዮጵያ ህዝብ ነው ይላሉ።በተመሳሳዩ አቶ አባይ ፀሀዬም በረሀ የወረድኩት ለህዝቤ ስል ነበር ነው ያሉት።ነገሩ ግን እነዚህ ሰዎች ለህዝባቸው ሳይሆን ለኮሚኒስት አይዲዮሎጂ እና ለዘረፋ ነው የታገሉት። 3ኛ፣አሁንም አቶ ኢያሱ ኢህአፓን ወክለው፣ወያኔንና ሻብያን ፣ደርግን ሲያወግዙ ይታያሉ፣ሁሉም ግን ከኢህአፓ በአይዲዮሎጂ አንድ ናቸው። አሁንም አቶ እያሱ ተመልሶ ቢጤዎቹን ማውገዝ የሸና የቸ ጨዋታ ሊሆን ነው። አንዱ የመደብ ትግል ሲል፣ሌላው ደሞ የብሄር ትግል ማለቱ ብቻ ነው ልዩነቱ። ሁሉም ኢህአፓም፣ ወያኔም፣ ደርግም በመኢሶን በኩል፣ወያኔም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሰለባዎች ነበሩ። የሚለያዩትም በአፈፃፀም ላይ ብቻ ነው። 4ኛ፣ ስለ መደመር ሲጠቅ ኢያሱ አለማየሁ፣ድሮ ብዙም ሂሳብ አልወድም፣የምንደመረው ከወያኔ ጋ ነው? ከደርግ ጋ ነው? ብሎአል። መጀመሪያ ሂሳብ ማወቅና መውደድ ሰው በሎጂክና በኔትዎርክ እንዲያስብ ይረዳዋል፣ አቶ እያሱ የረሳው ነገር ቢኖር፣ከኢህአፓ ጋ መደመርም እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚከብደው ረስቶታል?። መደመር ማለት ትርጉሙ እኔ እንደገባኝ፣ ፣ጥሩውን ነገር ከመጥፎው ጋ አንድ ላይ ከመደምሰስ ፣መጥፎውን በማስወገድ በጥሩው ላይ እየጨመርን እንሂድ፣ እንጂ እነ ኢህአፓ፣እነ መኢሶን እነ ደርግ ሲሉት እንደነበረው " የአረጀውን የአፈጀውን ጎታቹን የፊውዳል ስርአት ደምስሰን አዲሲቱን አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊት እንገነባለን" ተብሎ ሀይማኖትን ማፍረስ፣ሀብታምን መደምሰስ፣መሬት ላራሹ ተብሎ የግል ንብረትን መዝረፍ፣ ይሄ ነበር ሲሰራ የነበረው። በመደመር ሂሳብ ግን አንድ ምሳሌ፣እንደ ደርግ ዘመን ሀብታሙን ፈጅቶ ደሀ መፍጠር ሳይሆን፣በመደመር ሂሳብ ግን ደሀን ወደ ሀብታም መቀየር ነው። ይህ ማለት በህገ ወጥ የተያዙት ንብረቶች አይወረሱ ማለት አይደለም። በዚህ ምክንያት ነው ዶክተር አብይ አህመድ ስለመደመሰስ ብዙ የማያወራው፣ ቀስ ብሎ የተበላሸውን ስለማስተካከል ነው የሚያወራው። ባለፉት 5 ወራት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ያልተጠበቁ ብዙ ስራዎችን ሰርቶአል። አቶ እያሱ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ለምን እከሌን አለደመሰሰም የሚለው አባባል አይሰራም። በሂደት ነው ሁሉም ነገር የሚስተካከለው። 5ኛ፣ ኢያሱ አለማየሁ ሁልጊዜ ስለትግል ነው የሚያወራው፣ ወያኔዎች ተጋዳላይ ነን አንደሚሉት ማለት ነው። ለኔ ይሄ ትግል ሳይሆን ልፍያ ነው የሆነብኝ። ሁለቱም ስለ ጉዋዶቻቸው ያወራሉ።በደርግ ዘመን አንዱ አንዱን ጉዋድ እከሌ ሲለው፣ጉዋድ ተበዩ ተበሳጭቶ ኧረ እዛው ነጎድጉዋድ ያንጉድህ ያለው ትዝ አለኝ። 6ኛ፣ እያሱ አለማየሁ ስለ ኢንቨስትመንት ሲያወራ፣አየር መንገዱን ወይ አሜሪካኖች ናቸው ወይ ወያኔ ወይ ሻቢያ ነው የሚይዘው አለ። ስለቻይና ግን አላወራም። ምክንያቱም ቻይና ለእሱ የኮሚኒዝም ቅዱስ ሀገር ስለሆነች ስሙዋን አላነሳም። አሜሪካ ውስጥ ቁጭ ብሎ ደሞ ስለ አሜሪካ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ ያስጨንቀዋል። ንጉሱ ሊወድቁ አካባቢ እሱና የእሱ ቢጤዎ ፣ያንኪ ጎ ሆም ብለው የአሜሪካን ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ ያደረጉ መሆናቸውን ታሪክ ያስተምረናል። አሜሪካ ግን እሱ ስለተናገረ አላሰረችውም፣ሶሻል ዌልፈር ወይም ጡረታ ውን፣ እያገኘ እድሜ ልኩን በራሱ ወሬና ስራ እየታሸ እንዲኖር ብቻ አድረገዋለች። ቻይና ውስጥ ግን ቁጭ ብሎ ይሄን ቢያወራ፣ማውራቱም ሳይታወቅ ደብዛው ይጠፋ ነበር። ደግሞ የአየር መንገዱን ላይ አሜሪካ ተሳትፎ ቢኖራት ኢትዮጵያ አግኝታ ነው እድለኛ ናት። እንደዚህ አይነቱ የድህነት ሀሳብ ነው ሀገራችንን ደሀ ያደረጋት። 7ኛ፣ ለአቶ እያሱ አለማየሁ የምመክረው ነገር ቢኖር፣ እድሜው በጣም የሄደ ነው። ለሀምሳ አመታት ተመሳሳይ ወሬ ማውራት አሰልቺ ነው። ስለዚህ ለአዲሱ ጀነሬሽን አስተላልፎ፣ድርጅቱን ከግራ አክራሪነት ቢበዛ መተው ቢያንሰ ደሞ ወደ ዘመናዊ ግራ ፖለቲካ እንዲቀየር ማድረግ ለሀገር ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ።
@anteneh41
@anteneh41 5 лет назад
እኔ ሳውቅህ ምንም የማያረካህ ሰው የአአምሮ ችግር አለብህ ያኔ ታግላችሁ ስልጣን ብትይዙ በምድር ላይ እንዳንተ አንባገነን እይኖርም ነበር
@tadhailu
@tadhailu 5 лет назад
Sir, you are left by yourself, Mersha is the leader & he is in to , so it doesn't matter whether you are in or not.
Далее
Despicable Me Fart Blaster
00:51
Просмотров 13 млн
POP CHALLENGE 🎈
00:36
Просмотров 193 тыс.
The UK Election Results Explained
8:17
Просмотров 1,2 млн
EMS የጀነራል ተፈራ ማሞ ጥሪ July 2024
5:30