Тёмный

የሥራ ስንብት/የአገልግሎት ክፍያ የሚገባው ሠራተኛ How to calculate Severance payment የክፍያ መጠንና የታክስ ስሌት  

Beko Tube
Подписаться 863
Просмотров 9 тыс.
50% 1

የስንብት ክፍያ የሚገባው ሠራተኛ
የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ (60 የስራ ቀናት) እና የጡረታ አበል ለመቀበል ብቁ ካልሆነ (አስከብሮ)
ድርጅቱ በመክሰሩ /በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው በመዘጋቱ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
ሠራተኛው ከሥራ ሲቀነስ(አንቀጽ 29)፣
የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ሥራ፣ ምርታማነት መቀነስና ምርታማነትን ለማሳደግ አድስ አሰራር/ቴክኖሎጂ (አንቀጽ 28/3)
በአሠሪ /በሥራ መሪ ወሲባዊ ጥቃት /ትንኮሳ የተፈፀመበት እንደሆነ ወይም ድርጊቱ በሌላ ሠራተኛ እንደተፈፀመ ሪፖርት ተደርጎለት አሠሪው ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዱ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ካቋረጠ፤
አሠሪው በሠራተኛው ላይ ሰብአዊ ክብሩንና ሞራሉን የሚነካ ወይም በወንጀል ሕጉ መሠረት የሚያስቀጣ አድራጎት በመፈጸሙ የተነሣ ሠራተኛው የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ፤
አሠሪው ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት የሚያሰጋ አደጋ እንዳይደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት እርምጃ ባለመውሰዱ የተነሳ ሠራተኛው የስራ ውሉን ሲያቆርጥ፤
ሙሉ ወይም ዘላቂ የአካል ጉዳት በመድረሱ ሠራተኛው ሥራ ለመሥራት አለመቻሉ በሕክምና ተረጋግጦ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
ቢያንስ 5 ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በህመም ወይም በሞት የሥራ ውሉ ሲቋረጥ
ቢያንስ 5 ዓመት በአሠሪው ዘንድ የሥራ አገልግሎት ኖሮት በሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ ለአሠሪው የውል ግዴታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ፤
በኤችአይቪ/በኤድስ ህመም ምክንያት በራሱ አነሳሽነት የሥራ ውሉን ያቋረጠ እንደሆነ
በሕግ ከተደነገገው ምክንያት ውጭ በአሠሪው አነሳሽነት (አንቀጽ28) የሥራ ውሉ ሲቋረጥ፤
በአሰሪው አነሳሽንት በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ (አንቀጽ28)
የሠራተኛው ችሎታው ቀንሶ ሲገኝ
ሠራተኛው በጤንነት መታወክ /በአካል ጉዳት ምክንያት ግዴታውን ለመፈጸም ለዘለቄታው የማይችል ሲሆን፤
ድርጅቱ ወደሌላ ቦታ ሲዛወር ሠራተኛው ወደአዲሱ ቦታ ተዛውሮ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆነ፤
ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሲሰረዝና ሠራተኛውን ወደሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሲሆን፡፡
አሠሪው ምርቶች / አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ፤
የአሰራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ፡፡
በአሰሪ አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ስለማቋረጥ (አንቀጽ27)
ሀ) ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ባለማክበር፡- የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ6 ወር ውስጥ በጠቅላላው ለ8 ጊዜ የስራ ሰዓት ካላከበረ፤
ለ) በህግ ከተሰጡት እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ፡- የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በ6 ወር ውስጥ ለ5 ቀናት ከስራ ከቀረ፤
ሐ) በሥራው ላይ የማታለል ተግባር ከፈፀመ፤
መ) የራሱን /የሌላ ሰው ብልጽግናን በመሻት የአሠሪውን ንብረት /ገንዘብ አለአግባብ ከተጠቀመ፤
ሠ) ሠራተኛው ሥራውን የመሥራት ችሎታ እያለው የሥራ ውጤቱ ባለማቋረጥ የምርት ጥራትና መጠን በታች ሲሆን፤
ረ) በሥራው ቦታ አምባጓሮ /ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ ከሆነ፤
ሰ) በወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ ፤
ሸ) በአሠሪው ንብረት ላይ ሆነ ብሎ /በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
ቀ) በሠራተኛው ላይ ከ30 ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእሥራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር፤
የሥራ ውል ሲቋረጥ ደመወዝና ተያያዥ ክፍያዎችን ስለመክፈል
(አንቀጽ 36)
የሥራ ውል ሲቋረጥ የሠራተኛው ደመወዝና ከውሉ መቋረጥ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ሁሉ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ መከፈል አለባቸው፡፡
የክፍያው ጊዜ ሊራዘም የሚችለው ሠራተኛው ከአሠሪው የተረከበውን ንብረት በማስረከብ ወይም የሚፈለግበትን ማናቸውም ሂሣብ በማወራረድ ረገድ በራሱ ጥፋት ያዘገየ እንደሆነ ነው፡፡
ሠራተኛው የጠየቀው ክፍያ አስመልክቶ አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ አሠሪው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለሠራተኛው ያመነውን ያህል መክፈል ይኖርበታል፡፡ (አንቀጽ 37)
ከአሠሪው ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በ7 የስራ ቀናት ውስጥ አሠሪው ለሠራተኛው መክፈል የሚገባውን መጠን ካልከፈለ ክፍያው ለዘገየበት ጊዜ አሠሪው ለሠራተኛው እስከ 3ወር የሚደርስ ደመወዙን እንዲከፍል ሊወስን ይችላል፡፡(አንቀጽ 38)
የሥራ ስንብት የክፍያ መጠን
ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡፡
ከአንድ ዓመት በታች ያገለገለ ሠራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡
ከአንድ ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ተጨማሪ ክፍያ ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዓመት የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ 1/3 እየታከለ ይከፈለዋል፡፡
ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡ እና የታክስ ስሌት
Example
Employee Bereket
Hiring date Feb 15, 2013
Termination date April 20, 2020
Salary 30,000
Note12 months salary
30,000*12= 360,000
1st yr service 30,oo0
30,000*1/3*6=60,000
30,000*1/3*65/365=1,780.82
30,000+60,000+1,780.82
=91,780.82
Total severance = 91,780.82
Months (91,780.82/30,000) = 3.059360731 ~3.06months
For 1 month tax 30,000*0.35-1,500=9,000
For 3months tax 9,000*3=27,000
0.06 month salary 30,000*0.06=1,800
0.06 month tax 1,800*0.15-142.5=127.5
Total tax=27,000+127.5= 27,127.5
Net severance 91,780.82-27,127.5=64,653.32
Entry
severance pay………91,780.82
tax…………………………….……….27,127.5
cash………………………….………..64,653.32
Tax liab…………27,127.32
cash………………………..27,127.32
#severancepay
#Exceltutorial
#annualleave
#incometax
#BonusPay
#Bonus
#PENSION
#NETSALARY
#OVERTIME
#TransportationAllowance
#BedAllowance
#Perdiem
#MicrosoftWord
#MicrosoftExcel
#MicrosoftAccess
#MicrosoftPowerPoint
ETHIOPIA

Опубликовано:

 

1 окт 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 44   
@skillbishoftu
@skillbishoftu 4 месяца назад
እናመሰግናለን ለተሰጠን ትምህርት ነገር ግን ህጉ ሚለዉ ለመጀመሪያ አመት ሙሉ ደሞዝ ሳይሆን የመጨረሻ ሳምንት አማካይ የቀን ደሞዝ በ30 ተባዝቶ ነዉ ሌላ ትክክል ነዉ አንድ 3ኛ
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
ልክ ነህ usually የመጨረሻ ሳምንት የቀን ደመወዝ በ30 ሲባዛ ከወር ደመወዙ ጋር በአብዛኛው ተመሳሳይ ስለሚሆን በቀላሉ እንድትረዱት ስለፈለኩኝ ነው፡፡ ደመወዙ ላይ variance ካለው ግን ልዩነት ስለሚኖረው የመጨረሻ ሳምንት የቀን ደመወዝ በ30 ተባዝቶ ነው የመጣው ዋጋ ነው የሚሆ ነው፡፡
@yerookoomisgee6681
@yerookoomisgee6681 4 месяца назад
5 amet serchalew bagaza fekade sera belak Severance payment alagegnm?
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
ታገኛለ! በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 በአንቀጽ 39 ንዕስ 1/ሸ መሰረት ታገኛለ! የስራ ውሉ በተቁአረጠ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ነው የመጠየቅ መብት ያለህ፤ ስለዚህ ቶሎ መብትህን አስከብር
@enyewmenelik8683
@enyewmenelik8683 3 месяца назад
Batame takmogale enamasegnalene
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
አመሰግናለሁ
@vision-t1e
@vision-t1e Месяц назад
Excellent explanation Question: Be kesara mekeneyat and dereget seratega sekenes/seyasenabet ke 5 amet betach le seru serategoch deregetu severance pay mekefel alebet wey???? Thank you
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-IH0VM2bXytI.html
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
Thank u so much!
@AzmerawBayih
@AzmerawBayih 3 месяца назад
በእናትሽ እህቴ መልሽልኝ በጦርነት ምክናየት መንገድ ተዘግቶብኝ በሰአቱ መገኘት አልቻልሁም 4አመት ከ8 ወር በመምህርነት ከግል ትምህርት ቤት ሰርቻለሁ ነገር ግን ደብዳቤ ባስገባም ምንም አይነት መልስ የለም የስራ ልምድ ስጡኝ ስላቸዉም ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም አግዥኝ ከህግ አንፃር እንዴት ነዉ!
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
የስራ ልምድ የስራ ውል ከተቋረጠበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ እስከ 10 አመት ድረስ የመጠየቅ መብት አለህ፡፡ ደመወዝ እና ሌሎች ክፍያዎችን መጠየቅ የሚቻለው የስራ ውል ከተቋረጠበት ቀን ቀጥሎ ካለው ቀን ጀምሮ እስከ 6ወር ብቻ ነው መጠየቅ የሚቻለው ነገር ግን በጦርነት ምክንያት መብትህን የመጠየቂያ ጊዜ ካለፈብህ ከአቅም በላይ ስለመሆኑ ማስረዳት ያስፈልጋል (በአሰሪና ሰራተኛ ህግ አንቀጽ 167)፡፡ ስለዚህ በፅሑፍ የጠየቅህበትን ደብዳቤ እና ሌሎች ከስራ ቅጥር ጋር የተገናኙ ማናቸውም ማስረጃዎችህን ይዘ መክሰስ ትችላለ፡፡ እኔ ግን የህግ ባለሙያ አይደለውም ነገር ግን ከፋይናንስ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ህጎች ስራው በህጉ መሰረት መሰራት ስላለበት ህጉንም አብሬ አቀርባለው፡፡
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-IH0VM2bXytI.html
@JossaBen
@JossaBen 14 дней назад
በስራ ላይ ላለ ሰራተኛ የ2 ወር notification period ሲሰጠው ena demoz eyebela 2 weru alko severance pay sewesed, does the 2 months notification pay added with severance pay or not???
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 12 дней назад
@@JossaBen yes it should be added plus 2months salary should be given if the employer gives him a notice bcoz of permanently ceased it's operation or reduction of workforce
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 12 дней назад
@@JossaBen ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-IH0VM2bXytI.htmlsi=ZCuD5WZRgU61etgX
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 12 дней назад
@@JossaBen ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-2uzRWA--0Ew.htmlsi=Q4zoHswvCWu94gud
@yosephbolanko8475
@yosephbolanko8475 Месяц назад
ደሞዝ ብለን የምናስበው ግሮስ ሳላሪ ነው ወይስ የተጣራ ደሞዝ መጠንን ነው ?
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
@@yosephbolanko8475 ደመወዝ የሚባለው ታክስ ሳይቆረጥ በፊት ያለዉ መጠን ሆኖ የትራንስፖርት እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች አይካተቱም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀጽ 53
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
@@yosephbolanko8475 ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-IH0VM2bXytI.htmlsi=R-EE0o2BlYy_Vs4j
@Diamond21192
@Diamond21192 4 месяца назад
WOW በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነው።።በጥሩ አገላለፅ።።❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
Thank u
@vision-t1e
@vision-t1e Месяц назад
Question: be kisara mekeneyat dereget sesega ke 5 amet betach yeseru serategoch severance pay endekefel hegu yasegededal wey????
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
አዎን ያገኛሉ፡፡ የስራ ስንብት ክፍያ ለማግኘት ከ5 አመት በላይ አገልግሎት የሚጠበቅባቸው ሰራተኞቹ እራሳቸው በገዛ ፈቃዳቸው የስራ ውላቸውን ሲያፈርሱ ነው ከስልጠና ጋር የተገናኘ ግዴታ የሌለባቸው ከሆነ የስንብት ይከፈላቸዋል፡፡ በሞትና በህመም ምክንያት ከሆነ የስራ ውሉ የፈረሰው 5 አመት ካገለገለ የስልጠና ግዴታ ቢኖርበትም የስራ ስንብት ያገኛል፡፡ አንተ ባልከው ምክንያት ድርጅቱ በመክሰሩ ወይም በሌላ ምክንያት ለዘለቄታው ከተዘጋ የስራ ስንብት ሊከፈለው ይገባል ምክንያቱም ሰራተኛው በራሱ ፈቃድ አይደለም ስራውን የለቀቀው፡፡ ለተጨማሪ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 39/1 በደንብ አንብብ
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM Месяц назад
ru-vid.com/video/%D0%B2%D0%B8%D0%B4%D0%B5%D0%BE-2uzRWA--0Ew.html
@bekakidane6060
@bekakidane6060 2 месяца назад
እግዚአብሔር ይስጥሽ ፤ ጥሩ አርገሽ ስለገልጸሽው
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 2 месяца назад
ክብረት ይስጥልኝ🙏
@firdowsayuzarsif1643
@firdowsayuzarsif1643 3 месяца назад
እህት ምርት ሲቀንስ ማለት ለተማሪዎች ብቃት ማነስ ብለን መውሰድ እንችላለን? ሚኒስትሪ የሚያልፉት ተማሪዎች 0% ሲሆን በዚህ ምርት ቀነሰ ማለት አንችልም?
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
የምርት መቀነስ መጠን ከሆነ የቁጥር መቀነስ ነዉ። የምርት ጥራት ከሆነ ብቃት ነው።
@getechewtuba2897
@getechewtuba2897 3 месяца назад
ተመቸኘኝ
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
Thank u for watching
@zemenmatiwos9579
@zemenmatiwos9579 4 месяца назад
Ye contract seraregna siraw aliko ke site siweta yikefelewal?? Site yekoyew 2 amet new.
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
le contract seratena severance aykefelew. but anden sira lemesrat ke aseriw gar tewawelachu siraw sayalk or ye welu gize kemaleku befit aseriw be higewet menged (labor law article 26/2) kabarere compensation/ kasa yikefelale.
@enyewmenelik8683
@enyewmenelik8683 3 месяца назад
0.06 endate endamata gene algabageme 1month yans nawe belash nawe yalfshwe
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
Total severance ሲካፈል ለወር ደመወዙ(91,780.82/30,000 )= 3.06ወራት ይሆናል። ስለዚህ 3ሙሉ ወራት እና 0.06 ደግሞ ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ ነዉ
@mulugetashewa4948
@mulugetashewa4948 3 месяца назад
እናመሰግናለን ቀለል ያለ አቀራረብ ነወ።
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
ክብረት ይስጥልኝ
@abrhamtensay2906
@abrhamtensay2906 4 месяца назад
የካሳ ክፍያ እና ክፍያ የዘገየበት ክፍያ tax ይቆረጣል??
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
ካሳው የተከፈለው በሥራ ላይ በሚመጣ ጉዳት ለደረሰበት ሠራተኛ ከሆነ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 112 መሰረት ታክስ አይቆረጥበትም::
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 4 месяца назад
በገቢ ግብር አዋጅ 979/2009 አንቀጽ 12 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነቶች ውስጥ አንዱ የስራ ውል በሚቁአረጥበት ጊዜ ለሰራተኛው የሚከፈል ካሳ እንዲሁም በዳኝነት ውሳኔ መሰረት የተቀበለው ገንዘብ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ገቢዎች በአዋጁ አንቀጽ 65 ንዑስ አንቀጽ 1ሀ ከገቢግብር ነፃ የሆኑ የተቀጣሪ ገቢዎች ውስጥ ስላልተጠቀሱ እና ከግብር ነፃ የተደረጉ የተቀጣሪ ገቢዎች የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2011 ላይ አንተ ያልካቸው ገቢዎች ስላልተጠቀሱ ታክስ ሊከፈልባቸዋል ይገባል፡፡ practically ግን ብዙ ጊዜ ድርጅቶች አይከፍሉም
@tayewakuma8882
@tayewakuma8882 3 месяца назад
you explain VVV Clear ! Great !!
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
Thank u so much🙏
@berhanukebede5763
@berhanukebede5763 3 месяца назад
Add other
@BekoTube-BM
@BekoTube-BM 3 месяца назад
Okay
Далее
Лучше одной, чем с такими
00:54
Просмотров 341 тыс.
Severance payment
12:57
Просмотров 1,1 тыс.