Тёмный

Reyot Kin, Reminiscing Tesfaye Kasa ተስፋዬ ካሳ ሲተዘት፡፡ ቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡ 

Reyot
Подписаться 261 тыс.
Просмотров 38 тыс.
50% 1

ለተስፋዬ እንደካሳ፣ ተስፋዬ ካሳ ሲተዘት፡፡
ቴዎድሮስ ጸጋዬ፡፡
በጠራራ ቀትር፣ ከሞቃታማው ነፋስ ጋር እየታገልኩ፣ የጠዋቱን ብርድ ለማምለጥ የደረብኩትን ጃኬት መጣያ አጥቼ እየተጨነቅሁ፣ በእግረኛው መረማመጃ ላይ ጥጉን ይዤ አዘግማለሁ፡፡ ደክሞኛል፣ ታክቶኛል፡፡ ከትምህርት ቤት የጠዋት ፈረቃ ትምህርቴን ጨርሼ ወደቤት እየሄድኩ ነው፡፡
እንዲያ በመታከት ስጓዝ የመንገዱን ዳር ይዤ የተከፈቱትን የልብስ መሸጫዎች፣ ካፌዎች፣ የጌጣጌጥ መደብሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሱቆች፣ ጭማቂ ቤቶች ወዘተ አልፌ ከ፣ አንድ ሙዚቃ ቤት አጠገብ ደረስኩ፡፡ ያኔ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነኝ፡፡ ድንገት እሙዚቃ ቤቱ በር ላይ ከተቀመጠው ትልቅ ማጉያ SPEAKER የሚወጣ፣ ከነበርኩበት ድካም መንጭቆ የሚያወጣ ድምጽ ሰማሁ፡፡
ይህ በማጉያው ደመቅ ብሎ የተሰማኝ ድምጽ አዋጅ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም እምብዛም የማልሰማው ወይም ያልሰማሁት አይነት አዋጅ፡፡ እሙዚቃ ቤቱ በር ላይ ለ5 ደቂቃ ያህል የቆምኩ ይመስለኛል፡፡ በሰማሁት ስለተደሰትኩም ስለተገረምኩም ወደውስጥ ዘለቅሁና ከመስታወቱ ባንኮኒ ጀርባ የቆመውን ሰው ጠየቅሁት፡፡ “ይኼ የምሰማው ነገር ምንድነው?” ብዬ፡፡ እርሱም የተስፋዬ ካሳ አዲስ የቀልድ ክር መሆኑን ነገረኝ፡፡
ወጥቼ፣ ወበቁን እየሰነጠቅሁ ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ ወደቤቴ፡፡ በማግስቱ፣ ከወንድሜ 7 ብር ተበድሬ፣ እዚያችው ሙዚቃ ቤት ሄጄ ቅጂ ካሴት ገዛሁ፡፡ ቅጂ ስል ኦሪጅናል ያይደለ ማለቴ ነው፡፡ ያቺም ካሴት ከወንድሜ ተበድሬም ቢሆን እኔው እራሴ የገዛኋት፣ በእኔ ንብረትነት የተመዘገበች የመጀመሪያዋ ካሴት ሆነች፡፡
ነገሩን ጥቂት አስፈጋጊ የሚያደርገው ግን ካሴቱን የገዛሁት ቴፕ ሳይኖረኝ መሆኑ ነው፡፡ ያኔ ግን ይኼ አስቂኝም አሳሳቢም አልነበረም፡፡ ምክንያቱም፣ ሙዚቃ ማዳመጥ ባሰኘኝ ጊዜ ከቤታችን 2 ግቢ ብቻ አልፌ፣ እትዬ መብራት ቤት ገብቼ፣ በእርሳቸው ቴፕ ከልጆቻቸው ጋር መስማት እችል ስለነበር ነው፡፡ ከወራት በኋላ የግል ማጫወቻዬን እስክገዛ ድረስ የሆነው እንዲያ ነው፡፡ በእኔ የካሴት፣ በእነርሱ የቴፕ መዋጮ ፍላጎታችን ይሰምራል፡፡ ሳንነጋገር፣ ሳንወያይ የምንተዳደርበት ማህበራዊ ውል ሳይሆን ይቀራል? እናማ ኮሜዲያን ተስፋዬ ካሳን…
በርእዮት ኪን ተስፋዬ ካሳን እንተዝታለን፡፡
ተስፋዬካሳ ኮሜዲያንተስፋዬካሳ #TESFAYEKASA #Ethiopiancomedy

Развлечения

Опубликовано:

 

11 мар 2017

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 33   
@danielamha8072
@danielamha8072 4 года назад
አምላካችን ሆይ የተሰፋዬን ነፍስ በአፀደ ገነት አኑራት!!!
@samueladal3847
@samueladal3847 4 года назад
ሁሉም ነገሩ የሚጣፍጥ ለዛ ያለው ሰው እናመሰግናለን ቴዲያችን
@monaysuf4658
@monaysuf4658 3 года назад
ነፍስክን ይማር በጣም ታሳዝናለክ
@ambayewondie8244
@ambayewondie8244 6 лет назад
ነብስ ይማር ለተስፋዬ ካሳ ቴዲ እናመሰግናለን
@amanuelhailu3992
@amanuelhailu3992 7 лет назад
ቴዲ ተስፋዬን የተዘትክበት መንገድ በጣም በጣም ደስ ይላል በደምብ ነው የገለፅከው ። የኣተራረክህ ፍሰትም ተመችተኛል ።
@madinahfaris9013
@madinahfaris9013 7 лет назад
ነብስህን ይማርው ተስፍሽ ተዲ እናመሰግናለን በምያምር አተራርክህ አቀራርብህ በሁሉ ዝግጅትህ ሁሌም ደስ ይለኛል ቴዶ እንኳን ሀበሻ ሆንክ።
@sarasarah4679
@sarasarah4679 4 года назад
ተስፋዬ ነብስክን በገነት ያኑረው
@abebeyibeyin664
@abebeyibeyin664 3 года назад
ጀግናዬ
@lordjesuscomingsoon4730
@lordjesuscomingsoon4730 6 лет назад
በጣም ደስ የሚል አቀራረብነው ተባረክ ወንድማችን አዝናናህን እኮ 😃😃😃😃😃🙌🏻🙌🏻🙌🏻🙌🏻🙌🏻መሞት የማይገባው ሰው ሞተ 💔💔💔💔
@genetamare9847
@genetamare9847 4 года назад
በጣም ደስ የሚል ትዝታ ነው እናመሰግናለን
@musiewedey1196
@musiewedey1196 6 лет назад
ቴዲ በአውነት ምርጥ ኢትዮጽያዊ ነህ እድሜና ጤና ይስጥህ::
@firstbornnet
@firstbornnet 5 лет назад
ቴዲዬ ተስፋዬን የማቀው ደዴሳ ብሄራዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ጣቢያ አንደኛው ዙር አብረን ሰልጥነን እዛው ተመድብን ሁለታችንም ካድሬ ሆነን ነው እጅግ የሚያዝናናን ሰውና ወዳጄም ነበር በተለይ የካሳ ተሰማን በክራራ ይጫወትልን ነበር ያኔ ታዲይ የአድዋ ልጅ የለ የሲዳሞ ልጅ የለ የአዲሳባ ልጅ የሉ የአንቦ ልጅ የለ ሁላችን የኢትዮጲያ ልጅ ነበርን በሗላ ነው ቤተሰቦቹ ከአዱአ እርሱ ግን ከአዲስ አባ መሆኑን ስሰማ ግርም አለኝ ቀለሙ ጠይም ጥቁር ቀይ ነው እንጂ እርሱ ምንድነው ብለን አናውቅም ነበር አይ ጊዜ ጊዜ ዘልዛላው በዝች አጭር እድሜዬ ይህን ሁሉ ህብረት አንድነትና አሁን ደግሞ ግለኝነትን አሳየኝ አምናለሁ የተሻለውና የሚወደደው አንድነታችን ተመልሶ ይመጣል አምናለሁ ::
@wdebela
@wdebela 7 лет назад
ውብ ነው ቴዲዬ! ነፍስህን ደስ ይበላት አቦ! ተስፋዬንም ነፍስ ይማርልን!
@abe7478
@abe7478 7 лет назад
i am prawed of you Tedi
@TheBayout
@TheBayout 7 лет назад
R.I.P. Tesfaye and Thank you Tedi for the tribute
@woldu100
@woldu100 7 лет назад
ቴዲ: ዋው ልበል እንጂ ከዚያ በላይ ለማለት የሚያስችል የቋንቋ አቅም ስለሌለኝ። በዚህ መልክ አንድን የጥበብ ሰው ፣ ድንቅ በሆነ የቋንቋ ከህሎትህና ትንታኔህ ተስፋዬን መስማት፣ ለኔ እንደ መታደል ነው። ለተስፈሰዬ የነበረኝን አድናቆት ይበልጥ አገዘፍክብኝ። አቦ ተበረክ!!!
@haimanotmerdass9369
@haimanotmerdass9369 7 лет назад
ነፍስህን ይማረው ውድ ወንድሜ !!!
@jamalkader1020
@jamalkader1020 7 лет назад
ቀልድ ድሮ ቀረ ዛሬዛሬ እነ ፍልፍሉ በጊዜያችን ይቀልዱበታል
@abduyimer7900
@abduyimer7900 5 лет назад
Very good job Tedo!
@seni905
@seni905 6 лет назад
Thxs tadi lezgjet kefulu betame des yemile .program NAW temscha nber yemsemawu weza lezawu arfi nber ;:👏 Lemotute nbes yemare
@berhanegebreselassie6962
@berhanegebreselassie6962 5 лет назад
Think you Tade ,Tasfay is amazing Artest
@alemweyguuudamlakhoyasiben1446
Bravo tedysha tebarek
@hamdudawud1213
@hamdudawud1213 5 лет назад
ቴዶ ትችላለህ
@sebletemesgen567
@sebletemesgen567 7 лет назад
REST IN PEACE
@sarasarah4679
@sarasarah4679 4 года назад
ተስፋዬ ቀልድ ባንተ ግዜ ቀረ ቀረ ገና ሳጀምር ነበር የምታስቀው
@abebeyibeyin664
@abebeyibeyin664 3 года назад
እኔስ ብዬ ነበር ቀበሌ መረጠኝ እድሜ ለስካሬ ከእድርም አስወጡኝ
@caddesignworks1
@caddesignworks1 6 лет назад
I LIKE THIS CHANNAL WHAT I MEAN REYOT.
@user-vi4sj7st5l
@user-vi4sj7st5l 5 лет назад
ተስፋዬ ካሳ ልጅነቴን ያስታውሰኛል ቤተሰቦቼ ይወዱት ነበር 😥😥😥ነፍስ ይማረው
@taegiray4826
@taegiray4826 4 года назад
ቴዲ እናመስግናለን ተስፋዬ ካሳ ተሰማ ነው የተወለደበት ኣዲስ ኣበባ በኣምስት ኣመቱ ወደ ኣድግራት የሄዴበት ኣባቱ ኣድግራት ነው እናቱ ስንቃጣ ነች በኣድግራት በኣግኣዚ ትምርት ቤት እየተማረ እያለ ኣባቱ በሞት ከኣለም ሲለዩ ወደ እናቱ ተመልሶ ወደ ኣዲስ ኣበባ ሄዴ እኔ የሚገርመን ቡዙ ሰው ትግሬ መሆኑ ኣይያቅም የተስፋዬ እህቶቹ ወንድሞቹ በኣድግራት ነው ምነሩ ሁለት ሴቶች ልጆች ኣሉት ተስፋዬ ካሳ ነብሱ ይማሮው በገነት ያንሮው
@abrahamt2356
@abrahamt2356 7 лет назад
you are a wonderful journalist but you made me angry commenting Somme shameful phrases on Tedy's new Albem.,but you have the right to do that
@abezademu
@abezademu 4 года назад
Ted manem ayaklehme edmena tena yebzalke
@micaelgebre9330
@micaelgebre9330 Год назад
ቴዲ ተስፍሽ ከቁም ነገር ቀልዱ ዘመን ተሻጋሪው አንድ ልበልህ ሻቢያ አንኳን መአቀብ እቁብ ቢጥሉልለት ሰው አይሆንም ብሎ ነበር እኮ አይገርምም
@emebetgirma1506
@emebetgirma1506 Год назад
Ewent newu 🤣🤣
Далее
Comedy|ቀልድ ድሮ ቀረ
50:19
Просмотров 267 тыс.
Limenh Tadesse & Alebachew Teka Comedy Clips
4:54
Просмотров 162 тыс.