Featured Singer NATAN DESTA
ክብር ያስመለሱ መሰዊያን ያደሱ
ሁሉም የረሱትን በእድሜያቸው ያነሱ
እግዚአብሔርን ሽተው ታሪክ ያስለወጡ
በየዘመናቸው ለእውነት የተሰጡ
ነበሩ አምላካቸውን ፈገግ ያስደረጉ
ከእጁ ይልቅ ፊቱን ከልብ/ከምር የፈለጉ
በዘመኔ ሁሉ እኔም ሌላ አልሻም
አንተን እንጂ ጌታ ሌላ አላሳድድም
በልቤም ዙፋን ላይ ሌላ አይቀመጥም
ለአንተ እንጂ አምላኬ ለማንም አይሆንም
ብዙዎች ረክተዋል የእጅህን ስራ አይተው
እንጀራን ተርበው ስላበላሃቸው
በከንቱ ፈለጉህ ደግመህ እንድሰጣቸው
በቃኝ በማያውቀው ከንቱ መሻታቸው
እኔ ግን አንዲት ነገር እለምንሃለሁ
ከምትሰጠኝ በላይ አንተኑ እሻለሁ
ወደ ቀኝም ሳልል ወደግራም ሳላይ
የመደበልኝን ተቀብዬ ከላይ
ሩጫዬን እሮጣለሁ እርሱ እየመራኝ
በመጨረሻው ቀን በዕጣ ክፍሌ እንድገኝ
ወሰንኩኝ ላልመለስ እስከመጨረሻ
ከአምላኬ በስተቀር ልቤም ሌላ አይሻ
SEMAYAWI FILM presents SHILIMATEH NEH by MESFIN MAMO
executive producer NAHUSENAY MAMO, KALEB MAMO, EMMANUEL WORSHIP CENTER director WENDWESEN REGASA production manager ASER SEIFU music arrangement DAWIT GETACHEW sound NISTUH YILMMA band SAMUEL WORKNEH, ROBEL TEFERA background choir BINIYAM YONAS, AMANUEL MUSE, LIDYA ANTENEH, MERON ALEMU (JUDY), NATAN DESTA, HANNAH WETENE, SAMUEL SHIFERAW, FENAN BEFEKADU camera ASER SEIFU (AVA), ABENEZER GIRMA, KALEAB TSEGAYE, MOTI TAINA, FIKR ALEX, EYOB TESFAYE, BASLAEL, TADESSE setting designer TIGIST MESHESHA location manager KULENI BIRHANU editing WENDWESEN REGASA, ABENEZER GIRMA co-ordinator REDIET TEREFE assistant co-ordinator SARA PAULOS
13 окт 2024