Тёмный

የአዲስ ዓመት መልዕክት "መዞር ይበቃችኋል!" 

Evangelist Yared Tilahun
Подписаться 48 тыс.
Просмотров 25 тыс.
50% 1

ይህ ቪዲዮ የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት (2014 ዓ.ም) በማስመልከት ወንጌላዊ ያሬድ ያስተላለፈው አገራዊ መልዕክት ነው። የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ በኋላ ከኤርትራ ባሕር እስከ ከነዓን ለመድረስ የፈጀባቸው ብዙዎቻችን እንደምናስበው 40 ዓመት ሳይሆን 2 ዓመት ብቻ ነበር። በሁለት ዓመት የተስፋይቱ ምድር በር የነበረው ቃዴስ በርኔ ከደረሱ በኋላ እግዚአብሔርን ባለማመናቸው ምክንያት እግዚአብሔር በቁጣው ማለባቸው። መሐላውም ከእነዚህ ከናቁኝ አንድስ እንኳን አያይዋትም በሚል ነበር። ስለዚህ ይህ የማያምን ትውልድ ሞቶ እስኪያልቅ የእስራኤል ልጆች የሴይርን ቅጥልጥል ተራሮች ለ32 ዓመታት መዞር ነበረባቸው። አንድን ስፍራ ለ32 ዓመታት መዞር አድካሚ፣ አሰልቺ፣ አታካች ጉዞ ነው። ያ የማያምን ጠማማ ትውልድ ሞቶ ሲያልቅ እና አዲስ "የኢያሱ ትውልድ" ሲነሳ እግዚአብሔር "አሁን ይህንን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር ውጡ አለ።
የኢትዮጵያም ሁኔታ እንዲሁ ነው። በ1960ዎቹ የተነሳው የመማርና የመሰልጠን ዕድል ያገኘው ትውልድ ታበየ፣ እግዚአብሔርን ናቀ፣ "አምላክ የሚባል የለም!" አለ። ከዚያም በየዩኒቨርስቲዎቹ በባዕድ ፍልስፍና ተሞልቶ ሕ.ወ.ሃ.ት፣ ኢ.ህ.አ.ፓ፣ ኦ.ነ.ግ፣ ፣ ወታደራዊ ደርግ፣ ሜ.ኤ.ሶ.ን፣ ወዝሊግ፣ ኢ.ጫ.ት፣ ኢ.ማ.ዴ.ሊ … ወ.ዘ.ተ በሚል ተደራጅተው 47 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን የማትወጣበት አዙሪት ውስጥ ከተዋታል።
ኢትዮጵያ የተስፋ አገር ናት! ተስፋዋም እውነተኛ አንድነት ነው። አንድነት ልዩነትን የማይረግጥበት፣ ልዩነትም አንድነትን የማይውጥበት የመከባበርና በጋራ የመኖር እሴት ርስቷ ነው። ተስፋዋ፣ እውነተኛ ፍትሕ ነው። የሕግ የበላይነት የሰፈነበት፣ ብዙሃኑን የሚሰማ፣ ለትናንሾችንና ለደካሞች የሚፈርድ ፍትሕ ርስቷ ነው። ተስፋዋ፣ በተለወጠ አስተሳሰብ፣ በታደሰ አእምሮ በመልካም የሥራ ፈጠራ ባሕል፣ የትጋት ባሕል፣ የጊዜ አጠቃቀም ባሕል፣ የንባብና የምርምር ባሕል፣ የተግባቦት ባሕል ርስቷ ነው። በእነዚህ ርስቶች አጠገብ ናት፣ ነገር ግን መግባትና መውረስ አልቻለችም።
እነዚህን ምድራዊ ተስፋዎቿን ለመውረስ ግን አንድ ነገር መሆን አለበት። የቀደሙት የ60ዎቹ የክህደት ትውልድ እርሾ ከዚህ ትውልድ ወጥቶ ማለቅ አለበት። ያ የክፋት፣ የተንኮል፣ የሴረኝነት፣ የጦረኝነት፣ የዘራፊነት፣ የዘረኝነትና የመለያየት እርሾ ዛሬም የመውደቅና የመውደምን ተራሮች እንድንዞር ዳርጎናል። ያ እርሾ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ኢትዮጵያ ሥልጣን በጠመንጃ አፈ-ሙዝ የሚያዝባት፣ በጉልበት ያሸነፈ የወደደውን ሕግ የሚጭንባት፣ ሁሌ እንደ አዲስ የምትመሠረት ኋላ ቀር አገር ከመሆን አትወጣም። የአንድነት፣ የፍትሕና የዕድገት ተስፋዋን አትወርስም።
ይህ ትውልድ ፈጥኖ መንቃት አለበት። የቀደሙቱ አስተሳስብ በዚህ ትውልድ ውስጥ መሞት፣ መጥፋትና መክሰም አለበት። በምድረ በዳሊሞት የሚገባውን በእግዚአብሔር የተጠላ አስተሳሰብ አንግቦ የሚሰዋና የሚሞት ትውልድ መኖር የለበትም። ትውልዱ ወደ ኋላ ዘር እየቆጠረ፣ የ60ዎቹን ትርክት እየቀመረ መሠዋት የለበትም። ይልቅ ያንን ድሪቶ ከላዩ አሽቀንጥሮ ጥሎ ተስፋውን ለመውረስ በእምነት መገስገስ አለበት።
ያኔ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማማ፣ የምድር ጌጥ ትሆናለች። ያላት የተፈጥሮ ጸጋ ይገለጣል። ሕዝቧ በነጻነት ተዋዶና ተከባብሮ ይኖራል። ሕጻናት በደስታ የሚቦርቁባት፣ የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምጽ የሚያስተጋባባት፣ አዛውንትና አረጋውያን ዕድሜ ጠግበው፣ ጥሪታቸውን ለልጆቻቸው አውርሰው፣ ትውልዳቸውን መርቀው፣ በልጅ፣ ልጆቻቸው ተከበው የሚያሽልቡባት ምድር ትሆናለች። መዞር ይብቃን! በቃችሁ ይበለን! አዎን እግዚአብሔር በቃችሁ እያለን ነው። እኛም የ60ዎቹን የክህደት ትውልድ አስተሳሰብ አውልቀን እንጣል።
መልካም አዲስ ዓመት
2014 ዓ.ም

Опубликовано:

 

22 авг 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 204   
@amsalenegash6936
@amsalenegash6936 2 года назад
አሜን እሜን !!!!!! ወንጌላዊ ያሬድ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ 🙏🏻
@bisratyohannse9439
@bisratyohannse9439 2 года назад
ብዙ ነብያቶች ከተነበዩት ትንቢት የተለየ በእውነት ላይ የተመሰረተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምድራችን የተላከ መልእክት ነው ጌታ ይባርክህ ወንድሜ ያሬድ
@alexkefale5892
@alexkefale5892 2 года назад
በዚህ በጨለማ ዘመን ተስፋ ስለአሳየሀን ጌታ ከዚህም ጨምሮ ፀጋ ያብዛልህ ወንድሜ ያሬድ! ጌታን የበለጠ እንዳውቀው እና ወደ ጌታ የበለጠ እንድቀርብ ረድተህኛል! ጌታ ያብዛልህ! ትምህርቶችህን ማስታወሻ ይዤ ነው የምቀጣጠለው! በልበ ሙሉነት የእሱን ትምህርት ተቀጣጠሉ ማለት ከምችላቸው ጥቂት ሰዎች የመጀመሪያው አንተ ነህ! ለአንተ እና ለቤተሰብህ መልካም አዲስ አመት!
@Gelane1
@Gelane1 2 года назад
አሜን አሜን አሜን 🙏እግዛብሔር ዘመንህን ይባረክ ይሆናል ደርሷል እድሜ ይስጠን እናያለን ጌታችን ታማኝ ነው በእውነት መጠበቅ ብቻ ነው።
@beraeyassefa7400
@beraeyassefa7400 2 года назад
የ66ቶቹ ትውለደ ኢትዮጵያውያን ጌታን በሚያመልኩ በሚያገለግሉ ተተኩ። ሀሌሉያ ሀሌሉያ ሀሌሉያ
@bisratyohannse9439
@bisratyohannse9439 2 года назад
ያሬድ አንተና ቤተሰቦች በዚህ ዘመን እግዚአብሔርን በእውነት ለሚፈልጉት ሰዎች እንዲያገኙትና እንዲያውቁት የተሰጠኽን ስጦታችን ነህ ጌታ ዘመንህን ይባርክ!!!
@bereketmelkamu8762
@bereketmelkamu8762 2 года назад
ያሬዶ እንኳን አብሮ አደረሰን፡፡ ሁል ጊዜ ሳስብ በዚህ ዘመን አንተን የሰጠንን ጌታ አመሰግናለዉ፡፡ ላለፉት አመታት በ ኦንላይን የምታስተላልፋቸዉ ከኤፌሲዮን፣ ሮሜ ፤ ዮሴፍ፤ ዕብራዊያን እና የተለያ ትምህርቶችህ ለመንፈሳዊ እድገቴ ጠቀሙኝ ከምላቸዉ ነዉ፡፡ በሚመጣዉ አመት አንተም ምታብብበት አመት ይሁን ለቤተሰቦህ ሁሉ መልካም በዓል ይሁን፡፡ በጣም እወድሐለዉ፡፡
@teshaleminda2556
@teshaleminda2556 2 года назад
ከጌታ ዘንድ የተቸርከን የተወደድክ ወንድማችን ያሬድ ከሁሉ በላይ የጊዜው የሆነውን መልዕክት የሰጠህን የቃሉን ባለቤት እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ለምትወዳት ሀገርህ መዋጋት ያለብህን ክፉውን አስተሳሰብ የሚገድለውን መንፈሳዊውን ጦርነት እየተዋጋህ ስለሆነ አንተንም ከልቤ በብዙ ተባረክ እላለሁ. በርታ!!
@enatleenat7764
@enatleenat7764 2 года назад
በአንት መቼም እንዴት እደምባረክ:: ጌታ እየሱስን እንድናውቅ የምታስተምር ተባረክ::ይሄንንም ወረቀት እስኪርብቶ ይዤ ነው የማየው🙏🙏🙏
@Haymanotsavedbygrace
@Haymanotsavedbygrace 2 года назад
🙏🙏
@zerubabelmamo
@zerubabelmamo 2 года назад
አንተ ከጌታ የተሰጠህን ውዱ ስጦታችን ነህ ከ ጌታ የተሰጠህንም መልካም አደራ በአግባቡ እየተወጣህ እና እውነተኛውን ንፁህ የእገዚአብሄር ወንጌል እያገለገልክ ስላለህ እርሱ በማይጠፋው እና በከበረው የሕይወት አክሊለል ጌታ በአባቱ እና በመላእክቱ ደግሞም በቅዱሳን ፊት ያከብርሃል እኔ በአስተምህሮህ በጣም ነው ህይወቴ የተለወጠው እናም እነዴት ማገልገል እና መኖር እናዳለብኝ በደምብ አውቂያለው ወንድማችን ያሬድ እግዚአብሄር አሁንም ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱንም ያብራልህ !
@betelhemgirma9736
@betelhemgirma9736 2 года назад
አሜን አሜን አሜን 🙏🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
@romangetachewgebremariam5472
@romangetachewgebremariam5472 2 года назад
አውነትም ዙረት አውነትም ድግግሞሽ የሚያሰለች የሚያሳዝን አንድ አይነት ስንሰማና ስናይ የኖርነው አሰቃቂ ነገር ብቻ ጌታ ሆይ እኛንም እንደ እስራኤላውያን በቃችሁ በለን።
@allpraisestothemosthigh4671
@allpraisestothemosthigh4671 2 года назад
እስራኤላው አይደለንም ያለ አለ? እነዚህ ፈረንጆቹ ምድራችን ላይ ተቀምጠው እስራኤል ነን ይላሉ... አብዛኛው የሰሜን ሕዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ original እስራኤላውያን ናቸው:: የእውነት እስራኤላውያን እንደኛ ሜሊነን ወይም የስውነታችን የቀለም ኢንዛይም ነው:: ክርስቶስ ራሱ ጥቁር እንደሆነ ይናገራል
@seblewodajo5164
@seblewodajo5164 2 года назад
አሜን አሜን ጌታ በቃ ይበለን ጌታ ይባርክህ
@betelhemasefa8762
@betelhemasefa8762 2 года назад
ጌታ እየሱስ ይባርክህ ...እግዚአብሔር በቃቹ ይበለን
@nebertali9708
@nebertali9708 2 года назад
አሜን!!! መዞር ያብቃ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ
@user-nm6vv2im4r
@user-nm6vv2im4r 2 года назад
የተወደድክ ውድ ወንድሜ ወንጌላዊ ያሪድ በዘመናት ሁሉ የከበረው የአምላከችን የእግዚአብሔር ታማኝ ባሪያ ዘመንህ ይባረክ አይኖችህን በልጅነትህ የከፈተ ማምለጥ ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን በሽህ እና በአስር ሽህ የሚቆጠሩትን እድታሰመልጥ እቃ ያደረገህ አገልጋይ ምንም የምለው ነገር በይኖረኝም ግን ተክክለኛ እይታ ብቻ ሳይሁን እውነታው ስለሆነ እግዚአብሔርን የናቁ ይናቃሉ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሕዝብ እንደ ቃሉ እግዚአብሔርም አያውቃቸውም። ባንተ እደተላለፈው መልዕክት ተሰፋችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን የሚያስብብበት ዘመን መጥቶል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችንና መዳህገኘኒታችን ኢየሱሱ ክርቶስ ስም ትናንትናም ዛሬም ነገም ለዘለአለም በሰማይ በምድር በፍትረታት በጉዝም ይክበር ይባረክ። አንተም የእግዚአብሔር ባሪያ ዘመንህ ውድ ባለቤት ልጆችህ አግልግሎትህ በእጥፍ የምትዘረጉበት ዘመብ ይሁንለህ። በእርግጥ 25 አመታት የከበረውን እንቁ በአንተ ላይ አምላኬ የተከለው እያወራ ስለሆነ ከላፍክ በኋላ ሳይሁን አሁን በጣም እንደ ምንወድህና እንደመናከብርህ መመሰከር በእግዚአብሔር ፊት ክብር ነው። ተባረክ የማታሳፍር የእግዚአብሔር ባሪያ
@alem7149
@alem7149 2 года назад
በእውነት የዘላለም አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ሁል ግዜ ከእውነት ጋር ስለምትቆም ዘመንህ ይባረክ ተባረክ
@sebeleg7835
@sebeleg7835 2 года назад
በእውነት ይህንን ትምህርት በመላው ኢትዮጵያ ምድር ሁሉም በአንድነት ቁጭ ብሎ እቤት ውስጥ ፣ ወይ በሬዲዮ፣ ወይ በቲቪ ሳይሆን በቃ ከቤቱ ውጪ ወጥቶ በአንድነት ሰጥ ረጭ ብለው ይህንን ቢሰሙና በአንድነት ንስሀ ብንገባ እሱ ይቅር ባይ ነውና ይቅር ይለን ነበር ። ወገኔ ንቃ ለዚህች ለምታልፍ አለም የማያልፈውን ለልጆቻችን አናውርስ ። እረ ጌታ በቃችሁ ይላል😭😭😭😭😭😭እንስማው እንመለስ 🙏🙏🙏🙏ያሬዶ እግዚአብሔር ይባርክህ በድጋሚ
@zo-ma6557
@zo-ma6557 2 года назад
ተባረክ ያሬዴ! ትምህርትህ ሁሌም ይባርከኛል! የሚጣል ቃል የለውም. ተባረክ!
@betelhemgirma9736
@betelhemgirma9736 2 года назад
የተወደክ እግዚአብሔር ሰው ያሬዶ እንክዋን አደረሰህ መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇መዞር ይብቃን ። ኢትዮጵያ ማረፍን ትሻለች በቃን መዞር በቃን ዘረኝነት አንድ እንሁን ወደእግዚአብሔር እና ወደ ቃሉ እንመለስ 🙏🙏🙏የፍሬ ዘመን ዮሁንላቹ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
@tigist3038
@tigist3038 2 года назад
አሜን አሜን ! አምላካችን ይችላል ሲልይሆናል አምናለሁ እናያለን ጸሎታችንን የሚሰማ በዙፋኑ አለ። ወንድሜ አንተም ቤትህም ተባረኩ ይብዛልህ።
@mihretasrat8500
@mihretasrat8500 2 года назад
This is the most powerful message regarding my Ethiopia. Thank you Evangelist Yared!
@melenabekalu1762
@melenabekalu1762 2 года назад
አሜን ይብቃ ወንጌላዊ ያሪድ በአንተ ብዙ ተምሬአለሁ እባክህን በአዲስ ኪዳን አማኞች በእግዚአብሔር መልአክት ይጠበቃሉ ወይስ ራሱ እግዚአብሔር ነው የሚጠብቃቸው ምክንያቱም አንድ ሰው እብራዊያን 1÷14ን ጠቅሶ የመልአክት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው መዳንን ሊወርሱ ያሉት ናቸው እንጂ እኛ ድነናል ወርሰናል የሚል ስላስተማረ ነው አደራ በዚህ ጉዳይ አስተምረን።
@EvangelistYaredTilahun
@EvangelistYaredTilahun 2 года назад
በመላዕክትም ጠበቀን፣ በሰውም ጠበቀን ያው የሚጠብቀን እግዚአብሔር ነው። ዕብ. 1፥14 የሚናገረው ስለ አመንነው ስለ ሁላችን ነው። እኛ ድነናል፣ እየዳንን ነው፣ እንድንማለን። ክፍሉ የሚናገረው ወደፊት በጌታ መምጣት በሥጋ ትንሳኤ ስለ ምንድነው መዳን ነው። የጠቀስከው አስተምህሮ ስህተት ይመስለኛል።
@melenabekalu1762
@melenabekalu1762 2 года назад
@@EvangelistYaredTilahun አመሠግናለሁ ወንጌላዊ ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ በደንብ በዚህ ክፍል ላይ ብታስተምር ጥሩ ነው ብዙዎችም መረዳት ያገኛሉ።
@abebaseyiume8949
@abebaseyiume8949 2 года назад
ወንጌላዊ ያሬድ ተባረክልን
@mekedesmezmur4057
@mekedesmezmur4057 2 года назад
እጅግ በጣም እናመሰግናለን እንኳን አንተንም ከነቤተስብ በስላም አደርስህ መልካም አዲስ አመት ። እግዚአብሔር ሆይ ይህን አስተሳሰብ የምታመጣ አንተ ብቻ ስለሆንክ የሀገራችንን መሪዎች በፊትህ እናቀርባለን 🙏🙏
@litahaile6749
@litahaile6749 2 года назад
ወንድሜየ ያሬዶ, ጌታ ጸጋ ያብዛልህ ።
@edenhailemariam2240
@edenhailemariam2240 2 года назад
ኦሪት ዘዳግም 2 3፤ ነዚ ኸረንዚ ምዛር ይኣኽለኩም፡ ንሰሜን ገጽኩም ተመለሱ። Amen 🙏🏽. Stay blessed Evangelist Yarde. Thank you
@waynaphonetastic9887
@waynaphonetastic9887 2 года назад
ዋው ሥላንተ ጌታን እባርካለው ተባረክ መልካም አዲስ አመት ለመላው ቤተሠብህ
@teshalewondimu1861
@teshalewondimu1861 2 года назад
አሜን መዞር ይብቃን ጌታ ኢየሱስ ፀጋውን ያብዛልን ወንድሜ ያሬድ የጌታ ፀጋ ይብዛልክ
@zmack1830
@zmack1830 2 года назад
ውድ ወንድማችን ያሬድ የዘላለም አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ___ ኢይጵያውያን ወገኖቼ ይህ ዙረት እንዲቆም ለውጥ ክራሳችን መጀመር አለበት __ በውአጣችን የተደበቀን ማንኛውንም አይነት የጨለማ ባህሪ ዛሬ እንቅበር __ ሁሉንም ዚጋ እናክብር እንውደድ ፤ መናናቅ አናቁም __ የዚያን ጊዜ የዘላለም አምላክ ይባርከናል ፤ ምድራችንንም በሰላም ያጥለቀልቃታል !!!
@alem8640
@alem8640 2 года назад
Amen Tebare
@eristiabekele7293
@eristiabekele7293 2 года назад
እሜን ይብቃን ክፉ የማንሰማበትን ማዳኑን ብቻ የምናይበትን ዘመን ይሁንልን የመዞራችንን ሚስጥር ቁልጭ አድርገህ አሳይተህሕናል ጌታ እገልግሎትህን ዘመንህን ይባርክልህ ወንጌላዊ ያሬድ!
@selamzewdu7991
@selamzewdu7991 2 года назад
Omg wonderful message. ጌታ እየሱስ በአንተ ተጠቅሞ እንዴት እንደሚያስገርመኝ። በእኔ መንፈሳዊ ሂወት ትልቅ ቦታ አለህ ያሬድ መንፈሳዊ አባቴ። አሜን የተረገመውአስተሳሰብ ከሁላችን ውስጥ የሞተ ይሁን። መዞሩንም እግዚአብሔር አምላክ በቃችሁ ይበለን።
@esa972
@esa972 2 года назад
አሜን አሜን
@tamirumathewos5
@tamirumathewos5 2 года назад
ጌታ ይባርክ ወንጌላዊ ያሬድ አሜን እግዚአብሔር ይብቃ ይበለን
@serguttilahun2443
@serguttilahun2443 2 года назад
ወንድማችን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ የመልካም አዲስ አመት ከነቤተስብህ ይሁንልህ ይህን አፅናኝ ቃሉን የላከልን አምላካችን ይመስገን ቃሉ ሺህ ፍሬ እንዲያፈራ ወገኖቼ ላምላካችን እረፍት አንስጠው እንፀልይ እንጩህ እናልቅስ መልካም አዲስ አመት ለመላው ኢትዬጵያውያንእና ኤርትራውያን በሙሉ
@betelhemgirma9736
@betelhemgirma9736 2 года назад
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
@bitsitasefa7971
@bitsitasefa7971 2 года назад
E/r yibarkh wendim yared
@geteneshdebebe1505
@geteneshdebebe1505 2 года назад
A touching and True message of God's time & Blessed is the Ture servant of God !!!
@netsahonkubeeyesus1667
@netsahonkubeeyesus1667 2 года назад
በአሜሪካ ያለከው የተወደድከው ወንድማችን ያሬዳ እንኩዋን አብሮ አደረሰን አሜን ይበቃኛል ጌታ እየሱስ ከነቤተሰብክ ይባርክህ
@rosemare8314
@rosemare8314 2 года назад
Tebark tsegawen yabezaleh
@honeyb4984
@honeyb4984 2 года назад
አሜን ጌታ ይርዳን:: እንኳን ለአዲስ አመት በሰላም አደረሰህ ከቤተብህ ጋር ወንደም ያሬድ.ተባረክ.🙏🏽💕
@asterbelay540
@asterbelay540 2 года назад
ኦ አምላኬ በእየሱስ ስም ከኔ ትውልድ መዞር ይቁም እውነት ነው ዘመንህ ይባረክ ትምህርቶቹ ብዙ እማራለሁ፡፡
@abiymengesha1708
@abiymengesha1708 2 года назад
BLESS U. AMAZING MESSAGE.
@alexbuta4958
@alexbuta4958 2 года назад
Very wonderful, powerful, timely and earnest message ,Thank you pastor, God bless you
@danielhailu4365
@danielhailu4365 2 года назад
አሜን ይብቃ !ጌታ ይባርክህ የተወደደክ ወንድማችን ያሬድዬ
@amsalegizaw8829
@amsalegizaw8829 2 года назад
Tebarek wendme yehe tiyakye never zare temleseling abzito Egiz5 ybarkih
@eliasayele8587
@eliasayele8587 2 года назад
ይህ መልዕክት መስከረም 2-1-2014 ዓ.ም. በሰሜን አዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክርስትያን ተተላልፏል፡፡ የምስራች፡- እግዚአብሔር በወንጌል ምደሪቷን የሚያጥለቀልቅ ተውልድ አስነስቷል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ፡፡
@ethioupdatedinfo.
@ethioupdatedinfo. 2 года назад
Amen amen
@teshale2746
@teshale2746 2 года назад
Ameen Amen Amen
@kidistyigletu2209
@kidistyigletu2209 2 года назад
God Bless U !!!!!!!!!
@ruthyohannes4007
@ruthyohannes4007 2 года назад
Wendim yared geta yibarkih.melkam Addis amet ke betesbeh gar
@Mom2023new
@Mom2023new 2 года назад
አዘወትር ምህረቱና ቸርነቱ የማየልቅበት ምለካችን እግዚአብሔር ፣ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልኩኝ፣ ከሁሉም የሚበልጠውን እውነተኛ የእግዚአብሔርን ድምጽ በዚሁ ገጽ ለይ ለቅቄዋለሁና በማስተዋል አንብባችሁ ተጠቀሙበተ፣ ለወገኖችም እንድታደርሱልኝ በጌታ ፍቅር አሳስባለሁ፣ ተባረኩ።
@abiyreda9978
@abiyreda9978 2 года назад
Be Blessed
@helinamckrory4874
@helinamckrory4874 2 года назад
አሜን! እግዚአብሔር አገልግሎትህን አንተን ቤተሰብህን በብዙ ይባርክ!!! መልካም አዲስ አመት!!!!
@selame2713
@selame2713 2 года назад
ዘመንህ ይባረክ ያሬድ
@engidaworkmengesha3157
@engidaworkmengesha3157 2 года назад
እግዚአብሔር ይባርክህ :ዘመንህ ይባረክ በመልእክቱ ተገርሜአለሁ።
@felaweryene3108
@felaweryene3108 2 года назад
አሜን አሜን ጌታ በቃ ይበለን ጌታ ይባርክህ ወ/ያሬድ
@sebleaklilu284
@sebleaklilu284 2 года назад
እግዚአብሔር የምንማልድበትን የምንጸልይበትን አቅጣጫ አሳይቶናል አሜን መዞር ይበቃል! እንኳን አንተንና ቤተሰቦችህን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ!!!❤🌻🌻🌻
@marticool8700
@marticool8700 2 года назад
ወሳኝ ምክር እና ተግሳፅ ነው!! እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ ወንድማችን ያሪ መልካም ዓዲስ ዓመት ለአንተ እና ለመላው ቤተሰብህ።
@Meme-vk8et
@Meme-vk8et 2 года назад
አሜንን አሜንን ጌታ ሆይ ይበቃኛል
@ethiopialemmalegesse6866
@ethiopialemmalegesse6866 2 года назад
Amennnnn yibkan Tebarke 🙌🙌
@rb2782
@rb2782 2 года назад
ክብር ሁሉ ለሉኡል እግዚአብሔር አምላክ ይሁን አሜን፡ በጣም በጣም የተደነኩኝ ነው የሰማሁት እጅግ በጣም ደስ የሚል መሰረቱ ላይ ያለው ችግር ነው እግዚአብሔር የገለጠልህ፡ ግን ደስ የሚለው ነገር ጌታ በቃ ሲል ያበቃል፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንጌላዊ ያሬድ ተባረክልኝ 🙏🏽 እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ከነ ቤተሰቦችህ
@yorgeducherinet6420
@yorgeducherinet6420 2 года назад
ኣምላኬ ኣምላኬ ኣስበን
@neza8166
@neza8166 2 года назад
አሜን አሜን አሜን ዘመነህ ይባረክ ያረዶ
@yohannesteferra6202
@yohannesteferra6202 2 года назад
የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ይባርክህ !! አሁንም አሁንም ፀጋውን ይብዛልህ !! እኔ አንተን ካወቅሁህ ዓመት ጀምሮ እየጨመርክ እንጂ እንደ አንዳንድ አገልጋዮች እየወረድክና እየቀነስክ አልመጣህም፡፡
@EvangelistYaredTilahun
@EvangelistYaredTilahun 2 года назад
ክብር ሁሉ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!!!
@sebeleg7835
@sebeleg7835 2 года назад
አንተንና መላው ቤተሰብህንም ያሬዶዬ 🙏ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ከነቤተሰብህ🙏 አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን። 🙏🙏
@Meme-vk8et
@Meme-vk8et 2 года назад
ተባረክ ለመላው ቤተሰብህ መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ ለምልም
@jo9533
@jo9533 2 года назад
ተባረክ ያሬድ
@aidademoz3304
@aidademoz3304 2 года назад
Amenn Be kerstos Eyesu sim yibkan.!!!
@user-henyheny123gmail
@user-henyheny123gmail 2 года назад
God Bless you brother Yared an excellent message!!Yes Ethiopia’s solution is only from our God!!!Let Him say is Enough!!!
@asterbelay540
@asterbelay540 2 года назад
Amen Amen Beka Yebelne Mastewalen Abezalen
@yorgeducherinet6420
@yorgeducherinet6420 2 года назад
በትክክል
@Samrawit.K
@Samrawit.K 2 года назад
Ewenet new yemitayewun liyunetachinin akbiren yemaytayewun andinetachinin magulat alebin, geta asteway lib yargilin.
@ritaaraya3439
@ritaaraya3439 2 года назад
Amen 🙏 This is the time!!!
@blenberhanmamoye5801
@blenberhanmamoye5801 2 года назад
Tebarek amen
@zewdituabera6520
@zewdituabera6520 2 года назад
ቸር ያሰማህ ጌታ እየሱስ ይባርክህ
@simretwondimu445
@simretwondimu445 2 года назад
Lib yeminka melket new geta yebarkh. Yehen hasb bedfret menger kelal aydelm yemenfeskudeus erdat selalbet new. Tebarek
@fanayetesfaye9142
@fanayetesfaye9142 2 года назад
አሜን ይብቃን እግዚአብሔር ሆይ በቃ በለን! ወንድሜ ያሬድ በብዙ ተባረክ መልካም አዲስ አመት ለአንተና ለቤተሰብህ ይሁን፡፡
@netsanetnoah4015
@netsanetnoah4015 2 года назад
Amen Amen Amen
@zewditudano5897
@zewditudano5897 2 года назад
ወንድሜ ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ መልካም አዲስ ከመላው ቤተሠብህ ጋር ይሁንላችሁ የሰላም የፍቅር የአንድነት የጤና ዘመን ይሁንልን በኢየሱስ ስም ::
@michaelmelaku3749
@michaelmelaku3749 2 года назад
እግዚአብሔር ይስጥልን እጅግ ድንቅ ትምህርት እድሜ ይስጥልን👏👏
@kumsatekelegiorgis1325
@kumsatekelegiorgis1325 2 года назад
Wongelawi Yared, may God bless you to teach us on the subject no one dares to speak on, with the boldness the Lord has given you.
@tadidagne1896
@tadidagne1896 2 года назад
ያሬዶ አንተ የተባረክ ነህ ተባረክልን
@ambawabitew1644
@ambawabitew1644 2 года назад
ጥሩ በጣም ጥሩ ትምህርት ወቅታዊ ትምህርት : ቃለ ህይወት ያሰማን:: እችዚአብሄር ይባርልን::
@ambawabitew1644
@ambawabitew1644 2 года назад
እግዚአብሄር ይባርክልን::
@abebaantewan8821
@abebaantewan8821 2 года назад
አሜን ጌታ በቃ ይበለን
@mimitube270
@mimitube270 2 года назад
እግዚአብሔር አባታችን አብዝቶ ይባርክህ መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
@fuda1000
@fuda1000 2 года назад
Best insight and message. You never failed me in all your ministry. Happy New year to you and your families.
@betslot2366
@betslot2366 2 года назад
ጌታ ኢየሱስ ይባርክ ለዘመናት ጥያቄ የሆነብኝ ነገር መለስ ሰጠኛ ወይ ጉድ ለካ እየዞርን ነው አሜን እንደ እግዚአብሔር ቃል በቃ በቃ ይሁን ...መልካም አዲስ አመት ላንተ እና ለውድ ቤተሰቦችም ይሁን ወ/ጌ ያሬድ ተባረክ.
@emanuelafarina8957
@emanuelafarina8957 2 года назад
እንኳን አብሮ አደረሰን ወገኖች ተባረኩ ❤️🙏🇪🇹
@sebleabebe7042
@sebleabebe7042 2 года назад
አሜን!!! የተወደድህ ወንድማችን። መልካም አዲስ አመት ።
@habatamhabatam8769
@habatamhabatam8769 2 года назад
አሜን ይበቃል ይበለን ጸጋ ይብዛልህ ያሬዶ
@meazalachore9638
@meazalachore9638 2 года назад
Stay blessed
@blessing7936
@blessing7936 Год назад
Amen God bless you Brother.
@zewditugesesse385
@zewditugesesse385 2 года назад
አሜን ተባረክ ።
@ArsemaVlog
@ArsemaVlog 2 года назад
Thank you yaredo ….and happy new year to u and your family Stay blessed
@EvangelistYaredTilahun
@EvangelistYaredTilahun 2 года назад
Thank you too
@maranatha391
@maranatha391 2 года назад
Melkam addis amet lantem le betesbehm enwedehalen
@kalkidanyegeta5025
@kalkidanyegeta5025 2 года назад
አሜን በቃ ይበለን!
@marthawendemu1964
@marthawendemu1964 2 года назад
አሜን
@ephraimanbesaw117
@ephraimanbesaw117 2 года назад
አሜን መዞር ይብቃን አሜን አሜን
@zoenegash8130
@zoenegash8130 2 года назад
Amen Yaredo Geta yebarkeh. Awo yebekal!!!!
@user-rp3gw7ge7w
@user-rp3gw7ge7w 2 года назад
እንኳን አብሮ አደረሰን ያሬዶ
Далее
የቅባቱ ዕቃ
1:29:23
Просмотров 32 тыс.
ተፈጸመ! (ቴቴሌስታይ)
57:21
Просмотров 23 тыс.
Мама приболела😂@kak__oska
00:16
Просмотров 804 тыс.