Dirsan michael dersan gibrael dirsan rufael angle t.me/tegteneentseleye
ዳዊት “ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም መቅሰፍትም ወደቤትህ አይገባም ፡፡ በመንገድህ ኹሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፡፡ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሱኻል” እንዳለው /መዝ.91፡10-12/ እያንዳንዱ ሰው ጠባቂ መላእክት እንዳሉት ያስረዳል፡፡ እስራኤል ዘሥጋን የጠበቃቸው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይኽንንም ለኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ነግሮታል /ኢያ.5፡14-15/፡፡ይሁዳም የመልአኩ ስም ማን እንደኾነ በግልጽ ነግሮናል /ይሁዳቁ.9/፡፡
አስቀድመን እንደተመለከትነው ለእያንዳንዱ ሰው ብቻሳ ይኾን ለእንስሳት፣ ለዕፅዋት፣ለምድር፣ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ለከዋክብት፣ ከምድርም በታች ለተፈጠሩ ፍጥረታት በሙሉ ጠባቂ መላእክት አሏቸው፡፡ለምሳሌ እንስሳትን የሚጠብቀው መልአክ ሰላታኤል ይባላል፡፡አናንኤል የሚባለው ነገደ መላእክት ደግሞ እንደብረት የጸና የእሳት ነጐድጓድን ወደ ምድር የሚወነጭፉ፣ ፀሐይን ጨረቃን ከዋክብትን አዝርዕትን አትክልትን ዕፅዋትን ከምድር በላይከ ሰማይ በታች የተፈጠሩትን የሚጠብቁ ናቸው /ኩፋሌ 2፡6-8/፡፡
ቅዱስ ባሲልዮስ ዘቂሳርያ ሰውን ስለሚጠብቁ መላእክት ሲናገር፡- “ክፉ ሥራ ካልሠራን በቀር ጠባቂ መልአካችን ከእኛ አይለይም፡፡ ጭስ ንብን ከቀፎው እንዲወጣ እንደሚያደርገው ኹሉ የእኛ ኃጢአትም ጠባቂ መልአካችን ከእኛ እንዲለይ ያደርጓል” ብሏል፡፡ memher tesfaye abera
30 авг 2022