Тёмный

ስሜትን መግራት  

SAK Training & Consultancy
Подписаться 1,4 тыс.
Просмотров 6 тыс.
50% 1

ስሜትን መግራት ማለት ስሜትን በሚፈታተኑ የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ተረጋግቶ ውሳኔ መስጠት ሲሆን በተጨማሪም ስሜታዊ ሆነው የሚመጡ ሰዎችን በመረዳትና በማረጋጋት ወደቀልባቸው እንዲመለሱ የማድረግ ጥበብ ነው፡፡ ሰዎች ሆነ ብለው ስሜታዊ በመሆን እኛን ስሜታዊ ሊያደርጉን በሚሞክሩበት ሰዓት ሁኔታውን በማጤን የምንመልሰው መልስ ምን ጥቅም ወይም ጉዳት ያደርሳል ብለን በማሰብ በሳል ውሳኔ ማስተላለፍ ነው፡፡
አሁን ባለው የስራ አለም ከእውቀት ባሻገር ስሜትን የሚቆጣጠር እና ማህበራዊ ክህሎት ያለው ሰው በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ እውቀት ያለ ማህበራዊ ክህሎት የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ማህበራዊ ክህሎት ብቻውን ከእውቀት ጋር ካልተቀናጀ የሚፈለገው ውጤት ለያመጣ አይችልም፡፡ ስለዚህ ጭንቅላት ከልብ ጋር ተቀናጅቶ የሚደረገው ውሳኔ ብዙውን ጊዜ ውጤታማ ያደርጋል፡፡
በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስሜታችንን የሚፈታተኑ ነገሮች ሲኖሩ ልብእና ጭንቅላታችንን በማቀናጀት ከስሜት የነጻ ውሳኔ እንድናስተላልፍ ይጠበቃል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ጌዜ፣ ቦታ እና ሁኔታውን ያማከለ ውሳኔ መስትት ይጠበቅብናል፡፡
ስሜትን መግራት አራት ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነሱም
1. እራስን ማወቅ (Self awareness)
2. እራስን መቆጣጠር (Self control)
3. ሌሎችን ማወቅ (Social awareness)
4. ከሌሎች ጋር መኖር (Social Skill)
እራስን ማወቅ (Self awareness) ማለት ስሜታችንን መረዳት፣ የሚያስከፉንን፣ የሚያስደስቱንን ሁኔታዎች ፣ ጸባያችንን እና ማድረግ ያለብን እና የሌለብንን ነገሮች ማወቅ ነው፡፡
እራስን መቆጣጠር (Self control) ማለት ምንም አይነት እና ስሜትን የሚፈታተኑ ነገሮች ሲገጥሙን ቅጽበታዊ መልስ ከመስጠት መቆጠብ ማለት ነው፡፡ መልስ ከመስጠታችን በፊት መልሳችን የሚያመጣውን ውጤት በማጤን ችግሮችን መፍታት ያስፈልጋል፡፡
ሌሎችን ማወቅ (Social awareness) ማለት ከእኛ ጋር የሚኖሩ ወይም የሚሰሩ ሰዎች ምን አይነት ጸባይ፣ ድክመት ወይም ጥንካሬ እንዳላቸው በመረዳት ከእነሱ ጋር አንዴት መኖር እንዳለብን ማወቅ ነው፡፡
ከሌሎች ጋር መኖር (Social Skill) ማለት ከሰዎች ጋር ለመኖር የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የምንፈልገውን ውጤት ማግኘት ነው፡፡ የሰዎችን ባህርይ እና ሁኔታዎችን በመረዳት አብሮ የመኖር፣ የመስራት ጥበብ ነው፡፡

Опубликовано:

 

24 июн 2024

Поделиться:

Ссылка:

Скачать:

Готовим ссылку...

Добавить в:

Мой плейлист
Посмотреть позже
Комментарии : 34   
@abrahamaleme2144
@abrahamaleme2144 3 дня назад
ዶር አንተን አለማመስገን አይቻልም ግሩም ት/ት ነው እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡
@user-oy4nk1ek7v
@user-oy4nk1ek7v 6 дней назад
ዶ.ር አደራ ስለ ገነፈለው ድስት.. በጣም ያስተምራል . ተባረክ
@user-fn5hn3tp4n
@user-fn5hn3tp4n 3 дня назад
ዶ/ር አዴ አብሮ አደጌ ጥሩ ርእስ ነው ያነሳኸው ሁሌ ይቀጥል ይበል ነው የምለው።
@DjhGg-ry7gc
@DjhGg-ry7gc 10 часов назад
ኤረ እናሳድገው ይህ ኣባታችን ለኛ ይጠቅመናል ❤❤❤❤
@gizachewworkineh7006
@gizachewworkineh7006 2 дня назад
It's very good training, thank you.please try to improve sound quality
@user-gj1jy1fw8g
@user-gj1jy1fw8g 5 дней назад
ዶ/ር በእዉነት ትልቅ ትምህርት ነዉ ያገኘሁበት እራሴን እዳይ አድርጎኛል እኔ ብዙ ግዜ በስሞት እወስናለሁ ከዚህ በሗላ እቀይራለሁ እናመሰግናለን በጣም !!!!!
@fasiltamiru776
@fasiltamiru776 2 дня назад
Thank you Dr.Adera, really appreciate this practical life lesson!!keep up the good thoughts and deeds for the society..
@bizualema4339
@bizualema4339 3 часа назад
Its fantastic topic important for all particularly for us working in diversified environment. Thanks Doc! I always remember your training delivered to us in wolkite university!!!!
@user-co3jf6sy9w
@user-co3jf6sy9w День назад
አመሰግናለሁ።
@temesgenergetie7930
@temesgenergetie7930 4 часа назад
great man come now.Thank you!
@user-gt2zv2dn2o
@user-gt2zv2dn2o 2 дня назад
ኣረ ዶ/ር እስካሁን የት ነበር በስመኣብ እናመሰግናለን ኑርልን
@danihoek7341
@danihoek7341 7 часов назад
very very very great
@emmanualealemu8355
@emmanualealemu8355 6 дней назад
Dr adera ትክክል ነው እንወድሀለን
@zewdudechasa7041
@zewdudechasa7041 7 часов назад
it is interesting
@hannateklemariam341
@hannateklemariam341 3 дня назад
Eshi 🎉🎉🎉🎉🎉
@user-zg6bb1wl6f
@user-zg6bb1wl6f 6 дней назад
Thank you Dr
@hannateklemariam341
@hannateklemariam341 3 дня назад
🎉🎉🎉🎉🎉🎉
@hannateklemariam341
@hannateklemariam341 3 дня назад
Waw thanks wondme❤🎉❤🎉❤🎉❤
@User07198
@User07198 2 дня назад
🙏
@yodetdejene6440
@yodetdejene6440 9 часов назад
Thank you
@Teshome157
@Teshome157 6 дней назад
Thank you 100k
@zinayealemu5920
@zinayealemu5920 5 дней назад
Thank you, Dr. Adera
@SAK_Consultancy
@SAK_Consultancy 4 дня назад
You are welcome!
@user-zg6bb1wl6f
@user-zg6bb1wl6f 6 дней назад
That is true 👍
@alemeshetegierefe3588
@alemeshetegierefe3588 5 дней назад
Thank you Doctor
@user-xq7sj7gi2p
@user-xq7sj7gi2p 5 дней назад
Today’s content is wonderful 😮
@fitsumethiotube1791
@fitsumethiotube1791 5 дней назад
Thank you dear
@Winta314
@Winta314 5 дней назад
67k subscribers ያለው YT channel alegn megzat mifelg
@ethiopiahagere2675
@ethiopiahagere2675 6 дней назад
Helpful content. Thank you Adra!
@SAK_Consultancy
@SAK_Consultancy 6 дней назад
Glad it was helpful!
@KewsrMohamed
@KewsrMohamed 3 дня назад
YaLamargagat eko yalamatadel naw
@SAK_Consultancy
@SAK_Consultancy 4 дня назад
Please leave your mobile number.
@Ananya-nd1so
@Ananya-nd1so 6 дней назад
Thank you
Далее
🎙️ПЕСНИ ВЖИВУЮ от КВАШЕНОЙ💖
3:23:13
THE ART OF SELF-LEADERSHIP
20:26
Просмотров 1,5 тыс.
ራስን የመቆጣጠር ታላቅ ጥበብ!
16:40